text
stringlengths
140
24k
summary
stringlengths
13
164
አዲስ አበባ፡ በመተከል ዞን ተከስቶ በነበረው ግጭት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በፓዊ ወረዳ አልሙ በድንኳን ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃይ አርሶ አደሮች በጎርፍና በዝናብ ምክንያት ለወባ ተጋላጭነታችን ጨምሯል ሲሉ አስታወቁ፤ በርካቶችም አካባቢውን ለቀው መሄዳቸው ተመልክቷል። የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሀላፊ በምላሻቸው የውሀ እጥረት እንጂ ሌላ ችግር የለባቸውም። አርሶ አደር ጥጋቡ ገላው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳመለከቱት ክረምቱ እየጨመረ በመምጣት ለጎርፍ፣ ለዝናብና ለውርጭ ተጋላጭ ሆነዋል፤ አካባቢው ወባማ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ የወባ ወረርሽኝ ይከሰታል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው ይገልፃሉ። ህፃናትን ጨምሮ አሁን ላይ በመጠለያው አንድ መቶ አርባ ሶስት ተፈናቃዮች ተጠልለን እንገኛለን፤ በአባወራ ደረጃ ሀምሳ ሁለት ነን ያሉት አርሶ አደሩ እስከ መኝታችን ድረስ ጎርፍ እየሞላ ተቸግረናል፤ በተጨማሪም ከፍተኛ የሆነ የመጠጥ ውሀ ችግር ገጥሞናል ሲሉ ተናግረዋል። የምግብ አቅርቦት ችግርም አለብን የሚሉት ተፈናቃዮቹ አሁን እየተሰጠን ያለው ከፌዴራል አደጋ ስጋት የሚላክ በወር ኪሎ ደረቅ በቆሎ ብቻ ነው። በርበሬ፣ ሽሮና ዘይት ሌሎችም ሲሰጡን ነበር አሁን ላይ ተቋርጠዋል ብለዋል። የምግብ ክፍተቱ ዝናብና ጎርፉ ከሚፈጥረው ቅዝቃዜ ጋር ተዳምሮ ለወባ እንዳረጋለን የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ አርሶ አደር ጥጋቡ ገልፀዋል። መረዳት የሚገባንን ያህል እየተረዳን አይደለም፤ ህፃናት ልጆቻችን በችግር ላይ ናቸው። ያሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ አርሶ አደር መልካሙ ጋሹ የምናድረውም ጭቃ ላይ በመሆኑ ስጋት አድሮብናል ብለዋል። አርሶ አደር መልካሙ እንደገለፁት በአልሙ መጠለያ ውስጥ የሰፈርነው አርሶ አደሮች በአጠቃላይ ሁለትሺ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነበርን፤ የኑሮው ሁኔታ እየከበደና አስቸጋሪ እየሆነ ሲመጣ ሰው እንደወጣ መቅረት ጀመረ። ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል። ተፈናቃዩ የቀን ስራ ፍለጋ በሚል ነው ወደ ተለያየ ቦታ የተበተነው እንጂ አንድም ሰው ተመልሶ በቀየው ላይ እንዲሰፍር አልተደረገም ሲሉም አስታውቀዋል። የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሀላፊ አቶ ታረቀኝ ተሲሳ በበኩላቸው የቧንቧ ውሀ አልፎ አልፎ ስለሚቆራረጥ የውሀ ችግር ነው የነበረባቸው እንጂ ሌላ ችግር የለባቸውም። ሰሞኑን በአካል ተገኝቼ አረጋግጫለሁ የሚሉት ሀላፊው እነሱም ይሄ ችግር አለብን ብለው አላነሱልኝም። እህል ደግሞ ከእነሱ ተርፎ ዳንጉር ወደሚባል ቦታ እየወሰድን ነው። እንደ አቶ ታረቀኝ ገለፃ የህፃናት አልሚ ምግብና ዱቄት፣ በቆሎ ኪሎ፣ ዘይት ከመንግስት በኩል በመደበኛ በወር እየቀረበላቸው ሲሆን ከህብረተሰቡ በኩልም የሚሰጣቸው ነገር አለ። ብዛታቸውም በጣም ትንሽ ስለሆኑ እነሱን ለመንከባከብ አልተቸገርንም ብለዋል። ባለፈው ወር ከመድሀኒት ጋር ተያይዞ ችግሮች ገጥሟቸው ነበር አሁን ላይ ተፈትቶላቸዋል ሲሉም ተናግረዋል። እንደውም እኮ ሰዎቹ የቀን ስራ ላይ ተሰማርተዋል። ሀምሌ አስር በአካል እዚያው ነበርኩ ያሉት አቶ ታረቀኝ ካምፕ ውስጥ ያገኘሁት ሰው ብቻ ነው፤ የት ሂደው ነው ብለን ስናጣራ የቀን ስራ መሄዳቸውን ሰማን። ሀምሌ ደግሞ ተመልሰው አንድ መቶ አርባ አንድ ሆነው በካምፑ ውስጥ አገኘናቸው ሲሉ ተናግረዋል። ቢሆንም ቅሬታዎች ከቀረቡ ተቀብሎ ምላሽ መስጠት ተገቢ እንደሆነም ገልፀዋል። ከጤና ጣቢያዎቻችን ጋር ተነጋግረን በየሳምንቱ የጤና ሁኔታቸውን ክትትል እናደርጋለን፤ ህመም የተሰማቸው ካሉም እናሳክማለን ያሉት የፓዊ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ አሰፋ ናቸው። በሰላም ያለስጋት ወጥተው መግባት እንዲችሉም ጥበቃና ክትትል እያደረግን ነው ብለዋል። ከእነሱ ጋር ተመካክረን ክረምቱ ከመጨመሩ በፊት ለጎርፍ ተጋላጭ ያልሆነና የተሻለ ቦታ መርጠው እንዲቀመጡ ተደርጓል። የሚያፈሱ ድንኳኖች ተለይተው ተጨማሪ ሸራ እንዲያገኙ ተደርጓል። ወቅቱ ለወባ ምቹ ነው፤አካባቢውም በወባ የሚታወቅ በመሆኑ ለህመም አይጋለጡም የሚል እምነት የለንም። ይሄንን ታሳቢ በማድረግ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመነጋገር የነፃ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። ጎርፍና ሌሎች ችግሮች የሚያስቸግሯቸው ከሆነም ወረዳው ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነ ገልፀዋል። በፊት ሰፍረው የነበሩት ተፈናቃዮች ቁጥር ከሁለት ሺህ በላይ እንደነበር የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው አሁን ላይ ያሉት አንድ መቶ አርባ አካባቢ ናቸው ብለዋል። ሌሎቹ አብዛኛዎቹ ወደ ትውልድ ቦታቸው ተመልሰዋል። በመጀመሪያው አንድ ወር ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ተፈናቃዮች ነበሩ። በቀጣዮቹ ጊዜያት ከሁለቱ ክልል አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይቶች እየተካሄዱ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማግባባት ቢሞከርም ፈቃደኛ አልሆኑም። በመሆኑም አብዛኛው ሰው ወጥቶ ሄደ፤ አምስት መቶ ሰማኒያ ብቻ ቀሩ። እነዚህም ሀብት ንብረት ያላቸውና የጠፋው ሀብት ይተካ ይሆን ብለው የሚያስቡ ነበሩ። በኋላ እንደማይሆን ሲረዱ ለቅቀው መሄዳቸውን ተናግረዋል አቶ ብርሀኑ። በአጠቃላይ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው ተመልሰው በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሁሉም አካል እገዛ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ብርሀኑ በተጠለሉባቸው ቦታዎች ደህንነታቸውና ጤንነታቸው እንዲጠበቅ በማድረግ በኩል ወረዳው እየሰራ ነው፤በቀጣይም የተጠናከረ ክትትል ያደርጋል ብለዋል። ግጭቱ ባለፈው ሚያዚያ ጀምሮ መቀስቀሱ ይታወሳል።አዲስ ዘመን ነሀሴ ዘጠኝ ሁለት ሺህ መሀመድ ሁሴን
በጎርፍና በዝናብ ምክንያት ለወባ ተጋልጠናል ተፈናቃይ አርሶ አደሮች የውሀ እጥረት እንጂ ሌላ ችግር የለባቸውም የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
አዲስ አበባ፣ የካቲት ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ መሪ ሀሳብ የአፍሪካን ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ፣ተገቢና በአፍሪካ ሰላም እስከሚሰፍን ድረስ መተግበር ያለበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው አስታወቁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የመሳሪያ ድምፅ የማይሰማባትን አህጉር በመፍጠር ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚለው የህብረቱ መሪ ሀሳብ በአፍሪካ ሰላም እስከሚሰፍን ድረስ መተግበር ያለበት ነው ብለዋል። ስለሆነም በአፍሪካ ግጭትና ጦርነትን ለማስወገድ የግጭቶቹን መሰረታዊ መንስኤ በመለየት እልባት መስጠት እንደሚያስፈልግና ለጊዜው ጦርነትንና ግጭቶችን ለመከላከል መሪ ሀሳቡን ተፈፃሚ ማድረግ ጠቃሚ መሆኑን ኢትዮጵያ ማሳወቋን ገልፀዋል። ከዚህ ባሻገር በጉባኤው ኢትዮጵያ በአህጉራዊና በአለም አቀፍ ደረጃ የምታካሂዳቸው የምርጫ ውድድሮች የተሳኩ እንዲሆኑ ሰፊ የማግባባት እና የማሳመን ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ ለሁለት የህብረቱ ተቋማት፣ ለአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት እና ለአፍሪካ ህብረት የታዋቂ ሰዎች ፓነል መመረጧን ተናግረዋል። አቶ ነቢያት አያይዘውም ኢትዮጵያ አፍሪካን በመወከል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚቴና በድርጅቱ የህፃናት መብት ኮሚቴ መመረጥ መቻሏን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ጎን ለጎን የናይጄሪያውን ፕሬዚዳንት መሀሙዱ ቡሀሪን፣ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማስተናገዷም ተናግረዋል። እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት መካሄዱን አብራርተዋል። ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አንፃርም አንድ መቶ ሀያ ስምንት እስረኞ ከታንዛኒያ እስር ቤቶች ተፈተው በዛሬው እለት ሀገራቸው እንደሚገቡ እንዲሁም በቻይና የሚማሩ ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ እንዳይጠቁ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ እንደሆነም ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት። ቃል አቀባዩ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ከየካቲት ዘጠኝ እስከ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ መግለፃቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የህብረቱ መሪ ሀሳብ የአፍሪካን ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው አቶ ነቢያት ጌታቸው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ መስጊዶች እና ቤተክርስቲያን መቃጠላቸውን ተከትሎ የክልሉ መንግስት አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንደሚያቀርብ ገለፀ።በትናንትናው እለት በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ መስጊዶች እና ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ የክልሉ መንግስት በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው በሰጡት መግለጫ፥ የክልሉን ሰላም የማይሹ ሀይሎች ትናንት ምሽት በመስጊዶች እና በቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልፀዋል።በእነዚህ ጥቃቶችም በአምስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል ያሉት አቶ ጌትነት፥ በሰው ህይወት ላይ ግን የደርሰ ጉዳት እንደሌለም አስረድተዋል።የፀጥታ ሀይሉ ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ተጠርጣሪዎችን ለህገ ለማቅርብ በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።በዚህም እስካሁን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ነው አቶ ጌትነት የገለፁት።በቀጣይም የፀጥታ ሀይሉ ብህረተሰቡን በማስተባበር አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንዲቀርቡ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያስታወቁት።አቶ ጌትነት ይርሳው፥ በትናንትናው እለት በደረሰው ጉዳት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን ይገልፃልም ብለዋል።በምስራቅ ጎጃም ሞጣ ከተማ በእስልምና እና በክርስትና እምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ለዘመናት በፍቅር የኖሩትን ህዝቦች ለማራራቅ ያለመ መሆኑንምዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልፀዋል።ጥቃቱ የሙስሊም እና የክርስቲያን ወንድማማች ህዝቦችን አይወክልም ያሉት አቶ ጌትነት፥ ለዘመናት በፍቅር በመቻቻል እና በመረዳዳት የኖሩት የሁለቱን እምነት ተከታዮች ለማራራቅ የሚጥሩ ሀይሎችም እንደማይሳካላቸው ገልፀዋል።በናትናኤል ጥጋቡ
አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንዲቀርቡ ይደረጋል የአማራ ክልል መንግስት
ከ ወደ በሁለት ወር አድገናል ግን ብዙ ይቀረናልግርማካሳከአንድ ሳምንት በፊት በዳያስፖራ ፈንዱ የተሰበሰበው ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር። ወደ ሶስት ሚሊዮን ዳያስፖራ ይኖራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። ግን ቁጥሩን አሳንሰን አንድ ሚሊዮን ነው ያለው ብንል እንኳን በቀን አንድ ዶላር ሳይሆን በሁለት ወር አምሳ ሳንቲም የማዋጣት ያህል ነበር ። አሁንም በጣም እጅግ በጣም ትንሽ ነበር።ባለፉት አስር ቀናት ግን የተሰበሰበው ገንዘብ ቁጥሩ ወደ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ደርሷል። በሶስት እጥፍ ነው ያደገው። ይሄ ትልቅና አስደሳች ለዉጥና ስኬት ነው።ሆኖም ቁጥሩ አሁንም መሰብሰብ ካለበት በጣም ያነሰ መሆኑን ላሰምርበት እወዳለሁ። በሁለት ወር አምሳ ሳንቲም ከመሰብሰብ በሁለት ወር አንድ ብር ከሀያ ሳንቲም ወደ መሰብሰብ ነው የተሸጋገርነው። በአጠቅላይ አሁን መሰብሰብ ከነበረበት ሰባ ሁለት ሚሊዮን ዶላር አንድ ነጥብ አምስት አካባቢ ብቻ መሰብሰቡ መሰብሰብ ካለበት ሁለት ከመቶ ብቻ መሰብሰቡን የሚያሳይ ነው። አዎን ከግማሽ ሚሊዮን ወደ አንድ ነጥብ ግማሽ ሚሊዮን መድረስ ትልቅ መሻሻል ነው። ግን አሁንም እዚያው ገና እየተንፏቀቅን በመሆናችን እንደ ኢሊ ሳይሆን እንደ ጥንቸል ወደ ፊት ትልቅ እርምጃ የምንራመድበትን አሰራር ማስቀመጥና ተግባራዊ ለማድረግ መነሳት አለብን። ከዚህ በፊት ደጋግሜ ፅፌዋለሁ የትረስት ፈንዱ የቦርድ አባላት በጥቅሉ ገንዘብ አዋጡ ሳይሆን ፕሮጀክቶችን ነድፈው በዚህ አመት እነዚህን ነው የምናደርገው ብለው ያቅርቡልን። ከፈረሱ በፊት ጋሪውን ማስቀደማቸው ለገንዘብ ማሰባሰቡ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል። ኮሚቴው በየከተማው ያሉ የእምነት ተቋሟት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበራት ጋር በጉዳዩ ላይ ይምከሩ። ከነርሱ ጋር አብሮ የሚሰሩበትን ፕሮቶኮል ቢያመቻቹ ጥሩ ነው። አዲስ ቻፕተር መመስረት ጥሩ ሊሆን ይችላል። ግን ኦልሬዲ የተመሰረቱ ተቋማት ካሉ ከነርሱ ጋር መስራቱ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ሌላው አዲስ አምባሳደር በአሜሪካ ስለተሾመ ኤምባሲውም በዚህ ረገድ ማገዝ የሚችልበት ሁኔታ ቢኖር ጥሩ ነው። አንድ ሰው ሲነግረኝ ቮሎንተር ለማድረግ ስሙን አድራሻዉን ኢሚሉን ከሁለት ወር በፊት አሳውቁቆ በዳያስፒራ ትረስት ፈንድ ድህረ ገፅ ላይ የዳያስፒራ ትረስት ፈንዱ ኮሚቴው ግን እስከ አሁን ኮንታክት እንዳላደረገው ነው የነገረኝ። ለመርዳት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን በተቀላጠፈ መልኩ ማስተናገድ ካልተችለ የተፈለገዉን ግብ ማሳካት አይቻልም።ወገኖች አቅም አለን። እንችላለን። ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን በቀን አንድ ዶላር ከመደብን ሶስት መቶ ስድሳ አምስት ሚሊዮን ዶላር ወይንም አስር ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንችላለን።ሁሉንም ነገር የትረስት ፈንዱ ኮሚቴ ላይ መጣል የለብንም። የት ገንዘብ ማዋጣት እንደሚችሉ በመግለፅ ዘመዶቻችንንና ደኞቻችንን እንዳይረሱ እንዲያዋጡ እናበረታታ። እስቲ ቻለንጅ አድርገን እንውሰድና የሚቀጥለው አንድ ወር ቢያንስ አስር ሰዎችን አነጋገረን ራሳቸውንን እንደ ቦርድ አባል አድርገን ቆጥረን ግደታቸውን እንዲወጡ እናድርግ። በቃ የኛው የግላችን ጉዳይ አድርገን እንረባረብበት። ደግሞም የኛው ጉዳይ ነው።
ከ ወደ በሁለት ወር አድገናል ግን ብዙ ይቀረናልግርማካሳ
ኢሳት ዲሲጥር የህዝብና ቤቶች ቆጠራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዳይከናወን የሚያደርግ ስጋት የለም ሲል የማእከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን አስታወቀ።የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሳፊ ገመዴ ለኢሳት እንደገለፁት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት የተፈናቀሉት በሙሉ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የሚደረግ በመሆኑ ቆጠራው ላይ የሚፈጠር ችግር አይኖርም።ከሚሊዮን በላይ ተፈናቃይ የሚገኝባት ኢትዮጵያ ቆጠራውን ለማካሄድ የሰላምና የደህንነት ሁኔታው አስተማማኝ አይደለም የሚል ስጋት ከተለያዩ ወገኖች በሚሰጥበት በዚህን ወቅት የማእከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን ዘንድሮን እንደማይሻገር አስታውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለም የሰላም ሚኒስቴር ሚሊዮን የሚሆኑ ተፈናቃዮችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጿል።ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ ነው የቀረው። አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ ከቀዬው መንደሩ ተፈናቅሎ በመጠለያ ጣቢያዎች ይገኛል።እንደመሰንበቻው ባይሆንም በአንዳንድ አባባቢዎች የእርስ በእርስ ግጭቶች መፍትሄ ሳያገኙ ቀጥለዋል።ለማእከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን የትኛውም ችግር የህዝብና ቤት ቆጠራውን የጊዜ ሰሌዳ የሚያስቀይር አልሆነም።ለኢሳት ቃለመጠይቅ የሰጡት የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሳፊ ገመዴ እንደሚሉት ስጋቶች እየተቀረፉ መምጣታቸውና የተቀሩትንም በመጪዎቹ ጊዜያት እልባት በመስጠት ቆጠራውን በታሰበለት ቀን ለማካሄድ በመንግስት በኩል አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው።የማእከላዊ ስታስቲክስ ባለስልጣን ለመጋቢት ቀጠሮ የያዘለትን ተኛውን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ማድረግ የነበረበት ባለፈው አመት ላይ እንደነበረ ነው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው የሚገልፁት።ይሁንና ባለፈው አመት የነበረው የፀጥታ ሁኔታ ቆጠራውን ለማከናወን የሰላምና መረጋጋት ሁኔታው አስተማማኝ ባለመሆኑ ለዚህኛው አመት ተሸጋግሯል ብለዋል።መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግን ባለፉት ወራት በእርስ በእርስ ግጭት በድርቅና በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር እያሻቀበ መቷል።ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉም ሆነ ከኦሮሚያ ወደ ሶማሌ ክልል የሸሹ ዜጎች ወደቦታቸው አልተመለሱም።የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው መልሼአለሁ የሚል ሪፖርት ለምክር ቤት ማቅረቡ ታውቋል።ሆኖም ሁለት ወር በማይሞላ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠር ተፈናቃይ ዜጋን ወደ መኖሪያው መመለስ የማይቻል እንደሆነ ታዛቢዎች ይገልፃሉ።መንግስት የቆጠራውን ቀን ላለመግፋት በሚወስደው የጥድፊያ ርምጃ የበለጠ ቀውስ እንዳይፈጠር የሚሰጉ ወገኖችም አሉ።አቶ ሳፊ ገመዴ የማእከላዊ ሳታስቲክስ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በቀሪው ጊዜያት ቀሪዎቹን ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው በመመለስና መረጋጋት በማስፈን ቆጠራውን ለማካሄድ የሚቻልበት ሁኔታ ይፈጠራል ይላሉ።ስጋቱ አሁንም አለ። ክልሎች በየአስተዳደር ወሰናቸው የሚደረገው ቆጠራ ላይ ሙሉ ስልጣን የተሰጣቸው መሆኑ የብሄርተኝነት ስሜት እየከረረ መምጣቱና ግጭቶች እንዷዲስ የሚያገረሹበት ምልክቶች እየታዩ መሆናቸው ቆጠራውን ተአማኒነት እንዳይኖረውና እንዳያስተጓጉለው ስጋታቸውን የሚገልፁት ጥቂት አይደሉም።መንግስት ግን አሁንም ከአቋሙ ወደ ኋላ አላለም። ለመጋቢት ዝግጅቱን እያካሄደ መሆኑን ቀጥሎበታል።
የህዝብና ቤቶች ቆጠራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይከናወናል ተባለ
አርሶ አደሮች ለረዥም ጊዜ መቆየት የማይችሉ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርቶችን የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የገበያ ማእከላት በቀጥታ የሚሸጡበት አሰራር ተግባራዊ መደረጉን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ። የንግድ ቢሮው ይህንን የገለፀው በከተማ አስተዳደሩ በተገነቡ የገበያ ማእከላት የሚስተዋለውን የመሰረተ ልማትና የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ፣ ሰኞ ሀምሌ አንድ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። አርሶ አደሮች በቶሎ የሚበላሹ ምርቶችን ከማሳቸው ሰብስበው እጃቸው ላይ ስለሚያቆዩ በርካታ ምርቶች ያላግባብ ባክነው እንደሚቀሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ ግብይትና የገበያ ልማት ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍሰሀ ጥበቡ ተናግረዋል። ለረዥም ጊዜ መቆየት የማይችሉ ምርቶችን አርሶ አደሮች ለአንድ ወር ያህል የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጃቸው የገበያ ማእከላት በማስገባት ሸጠው እንዲሄዱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አክለው ገልፀዋል። በተለይ ቲማቲም፣ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ማንጎና ሌሎች የፍራፍሬና የአትክልት ምርቶች ለረዥም ጊዜ መቆየት እንደማይችሉ የገለፁት ሀላፊው፣ ምርቶቹን ለማቆየት የከተማ አስተዳደሩ ባስገነባቸው የገበያ ማእከላት ውስጥ ማቀዝቀዣዎች በቅርቡ ለማስገጠም በሂደት ላይ መሆኑን አስረድተዋል። የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የዋጋ ንረት ለማስቆም፣ የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ የእሁድ ገበያን ከማመቻቸት ጀምሮ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ምርቶችን ወደ ተዘጋጁ የገበያ ማእከላት አስገብተው ለማሀበረሰቡ ተደራሽ የሚያደርጉ፣ ከመንግስት ቦታ ተሰጥቷቸው ሰፊ የእርሻ መሬቶች የሚያለሙ ባለሀብቶች መኖራቸውን አብራርተዋል። በተለያዩ ምርቶች ላይ በከተማዋ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማና በኮልፌ ክፍለ ከተማ የገበያ ማእከላት፣ በከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ ወጪ መገንባታቸውን አስረድተዋል። ወደ ገበያ ማእከላቱ ለሚሄዱ ሸማቾች የትራንስፖርት አገልግሎቱ የተቀላጠፈና የተሻለ እንዲሆን፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመሆን መሰረተ ልማቱ እንዲመቻች መደረጉን ተናግረዋል። በሁለት ሺህ አመተ ምህረት የንግድ ስርአቱን ተላልፈው በተገኙ ከሀምሳ ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን፣ የቢሮው ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ገልፀዋል። ከእነዚህ ውስጥ ሀያ አንድ ሺህ የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን፣ ወደፊት በህገወጥ ድርጊት የተሰማሩ ነጋዴዎችን በመከታተል ቁጥጥር የሚደረግ መሆኑን አክለዋል። ተቋማቱ ከተላለፏቸው ጥሰቶች መካከል ያለ ንግድ ፈቃድ መነገድ፣ የፈቃድ እድሳት አለማድረግ፣ ለንግድ የሚቀርቡ ምርቶችን ጥራት አለመጠበቅ፣ እንዲሁም ለምርቶች ተገቢውን የዋጋ ዝርዝር በግልፅ አለማመላከት እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።
አርሶ አደሮች የሚበላሹ ምርቶችን በቀጥታ የሚሸጡበት አሰራር ተግባራዊ መደረጉ ተነገረ
ኮሚሽኑን ጠይቀን ውሳኔ እየተጠባበቅን ነው ሀኦነንግ ፓኬጂንግ ፈቃድ ከሌለው ድርጅት ጋር ውል የፈፀሙ ድርጅቶች በህግ ይጠየቃሉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የፀና ፈቃድ ሳይኖረውና ለሌላ ስራ የተሰጠውን ፈቃድ በመጠቀም፣ ኢትዮጵያውያን ብቻ እንዲሰማሩበት በተፈቀደ የስራ ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ የቻይና ኩባንያ ታገደ። ሀኦነንግ ፓኬጂንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሀበር የተባለው ድርጅት ለፓኬጂንግ፣ ለወረቀት፣ ለሶፍትና ለናፕኪን ስራዎች በወሰደው ንግድ ፈቃድ፣ ያልተፈቀደለትንና ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተፈቀደውን፣ የተለያዩ የንግድ ስያሜዎች የያዘ ሌብል ስቲከር ማምረት ስራ ውስጥ ገብቶ በመገኘቱ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እንዳስቆመው ሪፖርተር ለማወቅ ችሏል።ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ቀበሌ አንድ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ ከተፈቀደለት ስራ ውጪ ተሰማርቶ በመገኘቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት የሌብል ማምረት ስራው መታገዱን ለሪፖርተር የገለፁት፣ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተካ ገብረየሱስ ናቸው። አቶ ተካ ለሪፖርተር እንደገለፁት፣ ለድርጅቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። በተሰጠው ፈቃድ መሰረት የፓኬጂንግ፣ የወረቀት፣ የሶፍት፣ የናፕኪንና የሌብል ወረቀት ማምረት አለበት። ከዚህ ውጪ ሲሰራ ከተገኘ የተሰጠው ፈቃድ ተሰርዞ ድርጅቱን እንዲዘጋ ይደረጋል። የድርጅቱ ባለቤትና ሀላፊዎች ወደ ኮሚሽኑ መጥተው ከዋና ኮሚሽነሩ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም አቶ ተካ አስረድተዋል። ባልተፈቀደላቸውና የፀና ንግድ ፈቃድ በሌላቸው ዘርፍ ውስጥ ተሰማርተው ቢያመርቱም መሸጥ እንደማይችሉ የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ ውል ፈፅመው ያሳተሙ ድርጅቶች ከተገኙም በህግ እንደሚጠየቁ ተናግረዋል። ምክንያቱ ደግሞ ስራው ኮንትሮባንድ በመሆኑና ቫትም ስለማይከፈልበት መሆኑን አስረድተዋል። ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ከሌለው ድርጅት ጋር ውል ፈፅሞና ሌብል እንዲመረትለት አዝዞ የተገኘ ድርጅት ተጠያቂ እንደሚሆንም አቶ ተካ አክለዋል። ኮሚሽኑ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባለሙያዎቹን ወደ ድርጅቱ ልኮ ድርጊቱ መፈፀሙን ማረጋገጣቸውን የተናገሩት አቶ ተካ፣ አሁንም በድጋሚ ሌላ ቡድን ለመላክ እየተዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል። በህገወጥ መንገድ ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀደ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው በተገኙ በርካታ ድርጅቶች ላይ ኮሚሽኑ እርምጃ መውሰዱንና እየተወሰደም መሆኑን አቶ ተካ አክለዋል። ድርጅቱ ስራ ከጀመረ አምስት ወራት አካባቢ መሆኑን ጠቁመው፣ ስራቸው ህገወጥ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ጠይቀው ውሳኔ እየጠበቁ መሆኑን የሀኦነንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሀበር ዋና ስራ አስኪያጅ ተወካይ ለሪፖርተር ምላሽ ሰጥተዋል። ድርጅቱ የሀበሻ ቢራንና የሜታ ቢራን ሌብል ለማምረት የናሙና ምርት ከመስራት ውጪ ሌላ ስራ እንዳልሰራና ውልም እንዳልፈፀመ ተወካዩ አስረድተዋል።
ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀደ የስራ ዘርፍ ላይ በድብቅ ተሰማርቶ የተገኘ የቻይና ድርጅት ታገደ
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ማህበር ስራ አመራር አባላት እና በቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር ደጋፊዎች መሀከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ በአባላቱ ላይ አጥልቶ የነበረው የእርስ በእስር ግጨት መቀልበሱን ምንጮች ከሪያድ አስታወቁ። ፌብረዋሪ ሀያ አንድ ሁለት ሺህ ምሸት ሲጠበቅ የነበረው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለፅ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል ብለዋል፡፤ በጉባኤው ላይ ከኤንባሲው የተወከሉ ዲፕሎማቶች በታዛቢነት መገኘታቸውን የጠቀሱት አንድ የጉባኤው ተሳታፊ በስራ አመራሩ እና በሼክ መስጠፋ ሁሴን መሀከል ተከስቶ የነበረው ልዩነት በዲፕሎማቱ ብለሀት ከወዲሁ መቀልበሱን ጠቅሰው ስብሰባው ያለምንም ችገር እና ስጋት በሰላም መካሄዱን አረጋግጠዋል። አስተያየት ሰጪው አያይዘው ሲገልፁ ጥቂቶች በብዙሀኑ ደም ዎኝተው የበላይነታቸውን በአቋራጭ ለማረጋገጥ የነበራቸው ህልም መና መቅረቱ የኮሚኒቲው ማህበር ከህግ እና ስረአት ውጭ ለሚንቀሳቀሱ ሀይሎች የማይበገር መሆኑንን ያረጋጋጠበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብለዋል። በተለይ ይላሉ እኚህ አስተያየት ሰጪ ጉዳይ የሚዲያ ሽፋን አግኝቶ በሚመለከታቸው አካላቶች ትኩረት ሳይሰጠው ቀርቶ ቢሆን ኖሮ አያሌ ወገኖች ዘግናኝ የሆነ ነገር ውስጥ ሊገቡ ይችሉ እንደነበር አውስተው ሶሻል ሚዲያዎች አደጋ ከመድረሱ በፌት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው የህዝቡን እሮሮ በማስተጋባት የኮሚኒቲውን አባላት ከአሰቃቂ ግጨት በመታደጋቸው ሊመስገኑ ይገባልም ብለውል። በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በዲያስፖራው ዘንድ ተደማጭነት እና ክብር ያላቸው ሶስት ዲፕሎማቶች ኤንባሲውን ወክለው በታዛቢነት መገኘታቸውን የሚናገሩ ምንጮች ስብሰባው ያለምንም ስጋት እና ሁከት በሰላም እንዲካሄድ ለማስቻል ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጋቸውን አክለው ገልፀዋል። በስብሰው ወቅት የኮሚኒቲው ስራ አመራር የሀያ ወራቱን የስራ ሪፖርት በማስደመጥ በአባልቱ መሀከል ከፍተኛ ውይይት መድረጉን የሚናገሩ እማኞች በስራ አመራሩ የቀረበው ሪፖርት በአብዛኛው አባላት ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ሳይሽሽጉ ተናግረዋል። በመጨረሻም የኮሚኒቲው ሊቀምንበር አቶ ቃሲም ያሲን በቀረብው ሪፖርት ዙሪያ ከአድማጮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በመስጠት በጉባኤው ተሳታፊዎች ዘንድ ሰፊ ውይይት ከመደረጉም በላይ የኮሚኒቲው ሁለገብ የመዝናኛ ማእከል በኮንተራት ለግለስቦች ቢተላለፍ የበለጠ ውጤታማ መሆን እንደሚችል ከአንድ አድማጭ የተሰነዘረውን ሀሳብ የኤንባሲው ተወካይ ክቡር አቶ ተመስገን ኡመር የኮሚኒቲው ንበረት ለዲያስፖራው ያለውን አጋርነት እና ጠቀሜታ በዝርዝር በማስቀመጥ የኮሚኒቲው ንብረቶች በኤንባሲው ስር እንደመሆናቸው መጠን አካሄዱ ህጋዊ መስረት ሊኖረው ስለማይችል የቀርበውን ሀሳብ ውድቅ በማድረግ ተቀባይነት እንደሌለው አረጋግጠዋል፡፤ የማህበሩ ሁለገብ የመዝናኛ ማእከል የሆነው ካፍቴሪያ ዘንድሮም ስልሳ አንድ ሺህ ሪያል ኪሳራ ማሳየቱን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል። በዚህ ስብሰባ ላይ የሀይማኖት አባቶች የህገር ሽማግሌዎች ጨምሮ ከኤንባሲ አንድ ክቡር አቶ አህመድ ጠላህ ሁለት ክቡር አቶ ተመስገን ኡመር ሶስት ክቡር አቶ መስፍን ድባቡ መገኘታቸውን የሚገልፁ የኮሚኒቲው አባላት ከስጋት እና ጭንቀት ይልቅ የጉባኤውን ምሸት በነፃነት ማሳለፋቸውን አስረድተዋል። ለጉባኤው የቀረበ የተባለው ሪፖርት ግልባጭ በእጃችን እንደገባ ሰሞኑን በዚህ ገፅ በስፋት ለመዳሰስ ይሞከራል። ከጅዳ በዋዲ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል የድረገፅ ጋዜጣ የላኩት
የእርስ በእርስ ግጭት ነገሶበት የከረመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የትግራይ ክልል መሪ ፓርቲ የሆነውን ህወሀትን የሚያወግዙ ሰልፎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጥቅምት ሀያ አራት ምሽት ህወሀት በትግራይ ክልል በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ማድረሱን ከገለፁ በሀላ በፌደራል መንግስትና በህወሀት መካከል የነበረው የቆየ አለመግባባት ተባብሶ ወደ ጦርነት አምርቷል። በአዳማ፣ በሞጆ፣ በምእራብ ሀረርጌ፣ በሱሉልታ፣በዱከም፣ ለገጣፎ፣ ሰበታ፣ ሆለታና በሌሎች ቦታዎችም ህወሀትን የሚያወግዙ ሰልፎች መካሄዳቸውን የመንስግት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ተመሳሳይ አላማ ያላቸው ሰልፎች በትናንትናው እለት በሲዳማ ክልል አዋሳ ከተማና በኦሮሚያ ክልል በአጋሮና ጂማ ከተማዎች ተካሂደው ነበር። ባለፈው ሳምንት የፌደሬሽን ምክርቤት የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባና ጊዜያዊ አስተዳዳር እንዲቋቁም ዉሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዛሬው እለት ዶክተር ሙሉ ነጋን በትግራይ ክልል ለተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርገው ሾመዋል። ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ የትግራይን ክልል የሚመራው ህወሀት ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲኖር ፍላጎቱን ቢገልፅም የፌደራል መንግስት የህገወጡ የህወሀት ቡድን ህግ ፊት ሳይቀርቡ ድርድር እንደማይኖር ገልጿል። የተወካዮች ምክርቤት በትናንትናው እለት የክልሉን መሪ ዶክተር ደብረፂዮን ገብረብረሚካኤልን ጨምሮ የስላሳ ዘጠኝ የምክርቤት አባላትን ያለመከሰሰ መብት አንስቷል። በትናንትናው ምሽት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በህወሀት መሪዎች ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ አውጥቶባቸዋል። በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል ያለው አለመግባባት የጀመረው ኢትዮጵያን ለሀያ ሰባት አመታት ሲመራ የነበረው ኢህአዴግ ፈርሶ ብልፅግና ፓርቲ ሲመሰረት፣ ከመስራቾቹ አንዱ የነበረው ህወሀት የውህደቱ አካል አልሆንም ባለበት ወቅት ነበር። የፌደራል መንግስት በኢትዮጵያ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምርጫ ለማካሄድ አያስችልም በማለት ምርጫ እንዲራዘም ሲያደርግ፣ ህወሀት በራሱ ክልልዊ ምርጫ አድርጎ ነበር። ህወሀት የፌደራል መንግስት ምርጫ ማካሄድ ሲገባው ከህገመንግስቱ ውጭ ነው ስልጣን ላይ ያለው ሲል ሲከስ ቆይቷል። መንግስትን የሚመራው ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ የህወሀት ምርጫ ተቀባይነት እንደሌለው ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል። የፌደራል መንግስት ከሳምንታት በፊት ከትግራይ ክልል ጋር ህጋዊ ግንኙነት ማቋረጡን አስታውቆ ነበር።አሁን ላይ በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል የነበረው አለመግባባት ሁኔታው ተባብሶ ወደ ግጭት ሊያመራ ችሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኢሰመኮ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ ሀይሎች የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት እንዲጠብቁና ሰብአዊ መብትን እንዳይጥሱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።
ተመሳሳይ አላማ ያለው ሰልፍ በትናንትናው እለት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል
ፊልሞን አታኽልቲ እባላለሁ። በናይሮቢ ኬንያ ነው የምኖረው። ናይሮቢ መኖር ከጀመርኩኝ ሶስት አመታት ሆኖኛል። ቤተሰቦቼ እዚህ ስለሚኖሩ ከነእሱ ጋር አብሮ ለመስራት ብዬ ነው ወደ ናይሮቢ የመጣሁት። በናይሮቢ ከተማ ኢስሊ በሚባል አካባቢ በአንድ የኢትዯጵያ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ ነኝ። የምኖረው ደግሞ ዌስትላንድ በሚባል ሰፈር ነው። ኬንያን ከኢትዮጵያ ጋር ሳወዳድራት በተለይ ናይሮቢ በጣም በተፈጥሮ ሀብቷ የታደለች አረንጓዴ ከተማ ናት። የአየር ሁኔታዋም በጣም ደስ የሚልና ተስማሚ ነው። በናይሮቢም ይሁን በአጠቃላይ በኬንያ ብዙ ተፈጥሯዊ የመዝናኛ ስፍራዎች አሉ። ይህ ደግሞ ለናይሮቢ ከተማ ተጨማሪ ውበት ፈጥሮላታል። ካለሁበት አርባ ካለ ቪዛ ወደ አንድ መቶ ሀያ ሰባት አገራት መጓዝ እችላለሁ ካለሁበት አርባ አንድ ከባሌ እስከ ቻድ የተደረገ የነፃነት ተጋድሎ ኡጋሊ፣ ማራጓይ እና ጊቴሪ፡ በጣም ተወዳጅ የኬንያ ባህላዊ ምግቦች ናቸው። እኔ ግን የእንጀራ አፍቃሪ ስለሆንኩኝ፤ ለኬንያ እና ለሌሎች ሀገራት ምግቦች እስከዚህም ነኝ። ኡጋሊና ጊቴሪ የሚባሉት የኬንያ ባህላዊ ምግቦች በተለይ ደግሞ እንጀራ በሽሮ በጣም ነው የምወደው። አብዛኛውን ጊዜ እንጀራ ነው የምመገበው። ሀገሬ ሁሌም ይናፍቀኛል፤ በተለይ ደግሞ በመቐለ ከተማ የምትገኘው ያደግኩባት ጅብሩኽ ቀበሌ እጅግ ትናፍቀኛለች። የሚገርመኝ ነገር ያደግኩበት አካባቢ አሁን ከምሰራበት ኢስሊ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ጋር በጣም ነው የሚመሳሰለው። ኢስሊ ማለት በናይሮቢ ትልቁ የንግድ ገበያ ነው። ከተለያዩ አገሮች የሚመጡ ነጋዴዎች ኢስሊን ሳይረግጡ፤ ሳይገበያዩ አይመለሱም። በተለይ ደግሞ የሶማሌያ ዜጎች። በጦርነት ምክንያት ቀዬያቸውን ጥለው ለሚመጡ ስደተኛ ሶማልያውያን ሁለተኛ ቤታቸው እንደ ማለት ነች። በጣም በርካታ ሶማልያውያን በዚሁ አከባቢ ይገኛሉ። ካለሁበት ልዩ መሰናዶ፡ ሎስ አንጀለስ ከአብይ አህመድ በፊትና በኋላ ካለሁበት ስላሳ ስምንት፡ ሳላስበው ወደ ትምህርት አለሙ የመቀላቀሉን ህልሜን አሳካሁኝ ኢስሊ ትልቅ ገበያ ስለሆነ ሁሌም ግርግር አይለየዉም። ለዚህም ነው ካደግኩበት ጅብሩክ ጋር የሚመሳሰልብኝ። ጅብሩክ በመቐለ ከተማ በሰፊው የሚታወቅና ግርግር የሚበዛበት ሰፈር ነው። እናም አብሮ አደጎቼን ሳገኛቸው ከጅብሩክ ወደ ጅብሩክ ነው መጣሁት እላቸዋለሁ። ኢስሊ፤ በኬንያ ትልቁ ገበያ መጀመሪያ የመጣሁ አካባቢ የሰዎቹን ባህሪ መረዳት ከብዶኝ ትንሽ ተቸግሬ ነበር። ከዚያ ውጪ ግን እምብዛም ያስቸገረኝ ነገር አልነበረም። በኬንያ አስቸጋሪ የሚባለው ወቅት ምርጫ ሲደርስ ፤ በተለይ የዛሬ አመት የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፍፁም አልረሳውም። የኬንያ ፖለቲካ ከባድ ነው። በምርጫ ወቅት ሁሉም የሚያሰፈልገውን ገዝቶ ቤቱን ዘግቶ ይቀመጣል። ምክንያቱም ንግድ ቤቶችም ዝግ ይሆናሉ። በሰላማዊ ሰልፍ ወቅት የድጋፍም ይሁን የተቃውሞ ሰልፍ ከሚያደርጉ ሰዎች ውጪ ማንም ሰው ዝር አይልም። በተቀናቃኝ የፖለቲካ ተወዳዳሪዎች ደጋፊዎች መካከል ደም ያፋሰሰ መጥፎ ሁኔታም ተፈጥሮ ያውቃል። ፊልሞን በሞምባሳ ባህር ዳርቻ በናይሮቢ ሁኔታው በጣም ከባድ ስለነበረ፤ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ ሞምባሳ በምትባለው የባህር ዳርቻ ከተማ ነው ያሳለፍኩት። በተረፈ የናይሮቢ ነዋሪ በጣም የዋህ ህዝብ ነው። ይሁን እንጂ አንድ ከተማው የሚታወቅበት መጥፎ ልማድ አለ። እሱም ሙስና ነው። ናይሮቢን የመቀየር እድል ቢሰጠኝ፤ መጀመሪያ የማጠፋው በሰፊው ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ሙስና ነበር። ሀገሬ ኢትዮጵያ ሁሌም ከአይኔ አትጠፋም። ሁሌም ትናፍቀኛለች። አሁን በቅፅበት ራሴን የሆነ ቦታ መላክ ብችል፤ በሀገሬ በተለይ መቐለ ላይ ብገኝ ደስ ይለኛል። ለላየን ፅጋብ እንደነገራት የ ካለሁበት ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት አርባ አራት፡ ዘላቂ ሰላም መኖሩን ሳረጋግጥ ነው ወደ ሀገሬ የምመለሰው
ካለሁበት አርባ ሶስት፡ የናይሮቢ ነዋሪ በጣም የዋህ ህዝብ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በጌዴኦ ዞን በወናጎ ከተማ ከሰማኒያ አምስት ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባእድ ነገር ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ኦይል ሊቢያ ማደያ ማሸጉን የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል። የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ምስጋና በራሶ መንግስት የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የነዳጅ አቅርቦት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል ። ከወናጎ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅንጅት ከህዝቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ከባእድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ሲሸጥ የነበረ ነዳጅ ለማጣራት በተደረገ ክትትል ቤንዚኑ የጥራት ጉድለት እንዳለበት ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል። የወናጎ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ ጎሎ በበኩላቸው በከተማዋ እየተበራከተ የመጣውን ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴና ከደረጃዎች በታች የሚመጡ ምርቶችን የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል ። በዚህም መሰረት ከሰማኒያ አምስት ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባእድ ነገር ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ በኦይል ሊቢያ ማደያ ላይ ጥልቅ ክትትል በማድረግ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን አመላክተዋል ። ህገ ወጥ ተግባራትንና መሰል ችግሮች ለመቅረፍ ከተማ አስተዳደሩ ከዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን የክትትል ስራ አጠናክረው ተጠናክሮ ይቀጥላል መባሉን ከደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ከሰማኒያ አምስት ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባእድ ነገር ጋር ቀላቅሎ ሲሸጥ የነበረ ኦይል ሊቢያ ማደያ ታሸገ
የአለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በየአራት አመቱ አንድ ጊዜ የሚያዘጋጀው ትልቁ የስፖርት መድረክ የቶኪዮ ሁለት ሺህ ሀያ ኦሊምፒክ በጃፓን አስተናጋጅነት ሊካሄድ የቀረው የጥቂት ወራት እድሜ ብቻ ነው። በመድረኩ የሚሳተፉ አገሮች ዝግጅቶቻቸውን በይፋ ጀምረዋል። ተሳትፎዋን በሜልቦርን ኦሊምፒክ አንድ ብላ የጀመረችው ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት በቶኪዮ እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ኦሊምፒክ ላይ ለምታደርገው ተሳትፎ በብሄራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በኩል ዝግጅቷን ጀምራለች። ኢትዮጵያ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ በሮም ኦሊምፒክ ሀ ብላ የጀመረችው የአሸናፊነት መንፈስ በተለይም በአትሌቲክሱ ትልቅ እውቅና ካላቸው በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አገሮች አንዷ እንድትሆን የተጫወተው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ይታመናል። የጃፓኗ ቶኪዮ ለሁለተኛ ጊዜ በመጪው ክረምት በሚካሄደው ቶኪዮ ሁለት ሺህ ሀያ ኦሊምፒክ የታላቁን አትሌት ገድል የሚመጥን ተሳትፎ ለማድረግ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እያከናወነ ከሚገኘው እንቅስቃሴ መካከል ሀብረተሰቡ በእኔነት ስሜት በቅድመ ዝግጅቱ የሚሳተፍበትን ሁኔታ ማመቻቸት አንዱ ነው። የኦሊምፒዝም እንቅስቃሴ ለማሀበራዊ ፋይዳ በሚል ማክሰኞ ጥር ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርእሳነ መምህራንና መምህራን እንዲሁም የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ ዶክተር እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት መድረክ በግዮን ሆቴል ተዘጋጅቶ፣ ኢትዮጵያ በቀጣዩ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎ ውይይት አድርገዋል። ኢትዮጵያ ከ ቶኪዮ እስከ ቶኪዮ ያስመዘገበችው ውጤት በሂደት ከመሻሻል ይልቅ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ለምን የሚሉ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ዝግጅቱን በሚመለከት ከዚህ በፊት ኦሊምፒክ ሲቃረብ ካልሆነ እንዲህ እንደ አሁኑ የስርአቱ መሰረት የሆኑ ትምህርት ቤቶችን፣ ጨምሮ ሌሎችም የሀብረተሰብ ክፍሎች በእኔነት ስሜት የሚሳተፉበት ሁኔታ ባለመኖሩ ስፖርቱን ከባህልና ትምህርት እንዲሁም በኦሊምፒክ እንደሚነገረው የህይወት ፍልስፍና አንድ አካል አድርጎ ለመጓዝ እንዳልተቻለ በመድረኩ ተነግሯል። በዚህም ኦሊምፒዝምን በኢትዮጵያ በማስፋፋት፣ የኦሊምፒክ እሴቶችና መርሆዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዳይፈጠር ምክንያት ሆኖ ስለመቆየቱ ጭምር በውይይቱ ተነስቷል። መድረኩ ኦሊምፒክ ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን፣ አሁን እንደተጀመረው መቀጠል እንዳለበት በመድረኩ ከመንፀባረቁም በላይ በተለይ የስፖርት መሰረት ትምህርት ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መሰራት እንዳለበት ተጠቁሟል። በውይይቱ የታደሙት አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፣ አሁን የሁላችንም ትኩረት መሆን ያለበት ከፊት ለፊታችን ለሚጠብቀን የቶኪዮ ሁለት ሺህ ሀያ ኦሊምፒክ ነው። በተለይም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸው ላይ ሰርተው በጎ ገፅታ መፍጠር የሁላችንም ሀላፊነት መሆን ይጠበቅበታል፤ ብለው ይህ ኦሊምፒክ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ ወጣቱ ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲመለስ ማድረግና ኦሊምፒክ ከማናቸውም ሀይማኖት፣ ፖለቲካና ዘር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሳይኖረው ነፃ የሆነ ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚደረግበት መድረክ ስለመሆኑ ጭምር ተናግረዋል። ኦሊምፒክን እንርዳ ሲባል ሚሊዮኖችን አትሌት ለማድረግ፣ ነገር ግን አትሌቶችን በመደገፍ ለተሻለ ውጤት በማብቃት የአገሪቱን ስምና መልካም ገፅታ እንዲያስጠሩ የግድ መሆኑን ያስረዱት አቶ አባዱላ፣ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ነዋሪ በማነቃነቅ የፈጠረው ቤተሰባዊ ግንኙነትና ትስስር በተለይም ሀብረተሰቡ ጤናውን እንዲጠብቅ፣ አንድነቱን እንዲያጠናክር፣ ትልቅ መነቃቃት ሆኖለት አልፏል፤ ብለዋል። ይህ ዛሬ የተጀመረው ኦሊምፒክን የማስረፅ ንቅናቄ ወደ ሌሎች ክልሎች የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማስፋፋት የኦሊምፒክ ችቦ የካቲት ስምንት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ከአዲስ አበባ እንደሚነሳም በውይይቱ ተነግሯል።
ባለስልጣኖችና ርእሳነ መምህራን የተሳተፉበት የኦሊምፒክ ተሳትፎ ንቅናቄ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘባት ሰው ቁጥር ከአምስት ሚሊየን ማለፉን አስታወቀች። በህንድ የተመዘገበው ይህ ቁጥር አለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁ አገራት መካከል ሁለተኛዋ ያደርጋታል። በሀገሪቱ ከቅርብ ቀናት ወዲህ በየእለቱ ዘጠና ሺህ ሰዎች በቫይረሱ እየተየዙ ይገኛሉ። ይህም በአለም ላይ ቫይረሱ እጅግ በፍጥነት እየተስፋፋባቸው ከሚገኙ ሀገራት መካከል ዋነኛዋ አድርጓታል። ቫይረሱ እንዲህ ሊሰራጭ የቻለው ጥላ የነበረውን እገዳ ማንሳቷን ተከትሎ መሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። እስከአሁን በሀገሪቱ በቫይረሱ አማካኝነት ሰማኒያ ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ሆኖም የሞት መጠኑ ከተያዘው ሰውና ከሌሎች አገራት አንፃር ሲታይ አነስተኛ መሆኑ ነው የተገለፀው። ህንድ በየእለቱ ከአንድ ሚሊየን በላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እያካሄደች መሆኑን ገልፃለች። ምንጭ፦ቢቢሲ
በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘው ሰው ቁጥር ከ አምስት ሚሊየን አለፈ
የአለማችን በእድሜ ትልቁ ሰው ይሆናሉ ተብለው የታሰቡት ደቡብ አፍሪካዊ በአንድ መቶ አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። እኝህ የእድሜ ባለፀጋ ፍሬዲ ብሎም፤ በምስራቅ ኬፕ ግዛት በጎርጎሮሳዊያኑ ግንቦት ወር አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አራት እንደተወለዱ የግል መረጃቸው ያሳያሉ። ይህ ግን በአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ የተረጋገጠ አይደለም። በጎርጎሮሳዊያኑ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ በተከሰተው በስፓኒሽ ጉንፋን ወረርሽኝ የሀዳር በሽታ ምክንያት በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ላይ እያሉ ጠቅላላ ቤተሰባቸውን አጡ። የሚገርመው ከወረርሽኙ ያመለጡት ፍሬዲ፤ ለበርካቶች ሞት ምክንያት ከሆኑት ሁለት የአለም ጦርነቶችና እና ከአፓርታይድ ጭፍጨፋም ተርፈዋል። ከሁለት አመታት በፊት ረዥም እድሜ ለመቆየታቸው ሚስጥሩ ምንድን ነው ተብለው የተጠየቁት የእድሜ ባለፀጋው ለቢቢሲ ሲናገሩ ምንም የተለየ ሚስጥር የለውም ብለዋል። አንድ ነገር ብቻ ነበር። ይህም ከፈጣሪ የተሰጠ ፀጋ ነው። ሁሉም ሀይል ያለው እሱ ነው። እኔ ምንም የለኝ። በማንኛውም ጊዜ ልሞት እችል ነበር፤ ግን እርሱ ጠበቀኝ ብለዋል። ፍሬዲ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ያሳለፉት ሰራተኛ ሆነው ነው። ታታሪና ጠንካራ ሰራተኛ ነበሩ። መጀመሪያ ላይ በእርሻው ዘርፍ ከዚያም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ተቀላቅለዋል። ጡረታ የወጡትም በሰማኒያዎቹ እድሜ ላይ እያሉ ነው። ምንም እንኳን ከበርካታ አመታት በፊት ከመጠጥ ጋር ቢለያዩም መደበኛ አጫሽ ነበሩ። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የአገሪቷ መንግስት የእንቅስቃሴ ገደብ ሲጥል ሲጋራ መግዛት ጭንቅ ሆኖባቸው ነበር። በዚህ ጊዜም በአንድ መቶ ኛው ልደታቸው ጋዜጣ ጠቅልለው የራሳቸውን ሲጋራ ሰርተው አጭሰዋል። ይህም ብቸኛው የሚያዝናናቸው ተግባር እንደሆነ የሰማኒያ ስድስት አመቷ ባለቤታቸው ግንቦት ወር ላይ ለሰንደይ ታይምስ ተናግረው ነበር። እኝህ የእድሜ ባለፀጋ ቅዳሜ እለት በተፈጥሯዊ ምክንያት በኬፕ ታውን ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። ከሁለት ሳምንት በፊት አያቴ እንጨት እየፈለጠ ነበር። በጣም ጠንካራ ሰው ነበር። ልበ ሙሉ ነበር። ሲል አንድሬ ኔዶ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግሯል። በቀናት ውስጥ ግን ያ ልበ ሙሉውና ጠንካራው ሰው በአንዴ ኩምሽሽ አለ ይላል አንድሬ። ህልፈታቸው ከዘመኑ ኮቪድ ወረርሽኝ ጋር እንደማይገናኝ ግን ቤተቦቻቸው ያምናሉ።
ፍሬዲ ብሎም፡ የአለማችን የእድሜ ባለፀጋ ደቡብ አፍሪካዊ በአንድ መቶ አመታቸው አረፉ
የአቶ ጃዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሀያ አንድ ተከሳሾች ጉዳይ ዛሬ ማክሰኞ የተመለከተው ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የክስ መከላከያ ውድቅ አድርጎ አቃቤ ህግ የክስ ማሻሻያ እንዲያቀርብ አዘዘ። ችሎት ላይ ምን ተባለ የአቶ ጃዋርና የሀያ አራት ሰዎች የክስ መዝገብየፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሀያ አንድ ሰዎች ያቀረቡትን የክስ መከላከያ ውድቅ አድርጓል።ተከሳሾቹ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ ክሳቸውን ለማየት ስልጣን እንደሌለውና ወንጀሉ ተፈፀመ የተባለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሆኑ እንዲሁም ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ጋር ያላትን ልዩ ጥቅም በመጥቀስ ክሳቸው ወደ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሄዶ መታየት አንዳለበት መከላከያ አቅርበው ነበር።ከዚህም በተጨማሪም የአስተዳዳር አዋጅና የጦር መሳሪያ ቁጥጥር እንዲሁም የቴሌኮም ማጭበርበርን አስመልክቶ ተከሳሾች መከላከያ አቅርበው ነበር።ክሳቸው ህገ መንግስቱ የሚሰጠውን እኩልነት በጣሰ መልኩ ነው የቀረበው በሚል በመከላከያ ላይ ያካተቱ ሲሆን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለዚህም ክስ መልስ ሰጥቶ ነበር።በፍርድ ቤቱ ውሎ እነአቶ ጃዋር መሀመድም ያቀረቡት እነዚህ የክስ መከላከያዎች በችሎቱ በሙሉ ድምፅ ውድቅ ያደረገ ሲሆን በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ አቃቤ ህግ ክሶቹ ላይ ማሻሻያ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል።አቃቤ ህግም ክሶቹን አስተካክሎ እንዲያቀርብ የአንድ ወር ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀ ቢሆንም ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው ግን ተቃውመውታል።የህግ የበላይነት ማስከበር፣ ለተከሳሾች ፍትህ መስጠት፣ ተጎጂዎች ካሳ እንዲያገኙ ከታሰበም ጉዳዩ በፍጥነት እንዲታይ የተናገሩት ጠበቆች የተሰጠው ቀጠሮ እንዲያጥር ጠይቀዋል። በተጨማሪም ከተከሳሾች ውስጥ መንግስት ያሰረን ወንጀል ሰርተን ሳይሆን ምርጫ ላይ እንዳንሳተፍ ነው ያሉት አቶ ሀምዛ አዳነ የቀጠሮው ጊዜ እንዲያጥር ጠይቀዋል።ፍርድቤቱም የሁለቱን ወገን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ለጥር ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ቀጠሮ ይዟል።አለብን ካሉት የደሀንነት ስጋት በመነሳት ባሉበት ቦታ ጊዜያዊ ችሎት እንዲቋቋምላቸው የጠየቁና ባለፉት ሶስት ቀጠሮዎች ያልተገኙት አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነና አቶ ሸምሰዲን ጠሀ በዛሬው ችሎት ላይ ተገኝተዋል።ከዚህ ቀደም በነበረው ቀጠሮ ላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ትእዛዝ እንዳሳዘናቸው አቶ በቀለ ገርባና አቶ ጃዋር መሀመድ ተናግረዋል። እኛ አንቀርብም ያልን በማስመሰል በግድ ፍርድ ቤት ይቅረቡ ተብሎ ትእዛዝ መውጣቱ በጣም አሳዝኖናል፤ በዚህም መሰረት ለደሀንነታችን እየሰጋን ነው የምንመጣው በማለት ወደ ፍርድ ቤት የመጡበትን ሁኔታ ገልፀዋል። አቶ በቀለ ገርባ ከደሀንነታቸው በተጨማሪ የሚደርስባቸው ጥቃት አገሪቷን ችግር ውስጥ እንደሚከታት በመናገር፣ ለሚያጋጥመው ችግር መንግስትና ችሎቱ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። አቶ ጃዋር መሀመድም፣ አገሪቷ ውስጥ ያለው የደሀንነት ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑ በመግለፅ አንዳች ነገር ቢደርስብን፣ በዚህ ምክንያት አገሪቷ ላይ ችግር ቢመጣ፣ ሸኔ ሻእብያ እያሉ ምክንያት መስጠት አያዋጣም። የምትጠየቁት እናንተ የህግ ባለመያዎችና መንግስት ነው ብለዋል።ዳኞቹ በበኩላቸው ትእዛዝ በሚሰጡበት ወቅት ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ የሚል እምነት ኖሯቸው መሆኑን በመጥቀስ የፍርድ ቤትን ትእዛዝ አታከብሩም የሚል እምነት የለንም። በግድ መቅረብ አለባቸው የሚለውን ትእዛዝ የሰጠነው እንደ አማራጭ ነው ብለዋል።ከዚህም በተጨማሪ እነአቶ ጃዋር መሀመድ ያቀረቡትን ክስ በስፋት ማየታቸውን በመናገር፣ የደሀንነታችሁን ሁኔታ እንከታተላለን። ወደዚህ የምትመጡበትንም ሁኔታ እንከታተላለን ብለዋል።በሌላ በኩል የመንግስት ሚዲያዎችና አንዳንድ የግል ሚዲያዎች ዘገባቸው ወገንተኝነት እንዳለበት ቅሬታ ያቀረቡት ደግሞ አቶ ደጀኔ ጣፋ ሲሆኑ፣ የመገናኛ ብዙሀኑ የፍርድ ቤት ውሎን በአግባቡ አንዲያቀርቡ ይህንን ፍርድ ቤቱ እንዲያሳስብልን በማለት ጠይቀዋል።ፍርድ ቤቱም ሚዲያዎቹ ችሎቱ ላይ የተባለውንና የችሎቱን ውሎ ብቻ እንዲዘግቡ አሳስቧል።በሰኔ ወር ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ከሀጫሉ ግድያ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ጃዋር መሀመድና በክስ መዝገባቸው ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ሰዎች የሽብር ወንጀልን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በወጣው አዋጅ፣ የቴሌኮም ወንጀልን ለመከላከል በወጣው አዋጅ፣ የአስተዳደርና የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅንና የአገሪቱን ወንጀል ህግ የተለያዩ አንቀፆችን በመተላለፍ ነው የተከሰሱት።አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ዶክተር ብርሀነ መስቀል አበበና ፀጋዬ ረጋሳ አገር ውስጥ የሌሎና በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብ ውስጥ ከተከሰሱት መካከል ናቸው።የድምፃዊ ሀጫሉ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ ከነበረ ሁከት ጋር ተያይዞ ነበር እነአቶ ጃዋር መሀመድ በቁጥጥር ስር የዋሉት።ከዚያም በኋላ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ሀያ አራት ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ክስ መክፈቱ ይታወሳል። ይኹን እንጂ አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነና አቶ ሸምሰዲን ጠሀ ለደሀንነታችን እንሰጋለን ብለው ሲናገሩ ነበር።ስለዚህም ይህን ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት በሚገኙበት ማረሚያ ቤት ውስጥ ጊዜያዊ ችሎት እንዲቋቋምላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።
አቃቤ ህግ በእነአቶ ጃዋር መሀመድ ላይ የክስ ማሻሻያ እንዲያቀርብ ታዘዘ
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኩባንያ የዘንድሮ የውድድር ዘመን በኮሮና ምክንያት እንዲሰረዝ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የአፍሪካ ውድድር ተሳትፎ አለመኖር ውሳኔን እንደሚቃወም መቐለ ሰባ እንደርታ አስታውቋል።ክለቡ ለሊግ ኩባንያው በላከው ባለ ሶስት ገፅ ደብዳቤ የሊጉን መቋረጥ እንደሚቀበለው የገለፀ ሲሆን የአፍሪካ ውድድር ተሳታፊዎች እንዳይኖሩ መወሰኑ ግን አግባብ አለመሆኑን አስቀምጧል። የአፍሪካ ውድድር አለመኖር ያለውን ተፅእኖ የገለፀው ክለቡ ውሳኔ ለመወሰን የተሄደበትን አካሄድ የክለባችንን አቋም ለመግለፅ እድል አልሰጠም በማለት አሳታፊ አለመሆኑን ተቃውሟል። በተጨማሪም ክለቦች የሚደጎሙበት እና ወጪ የሚቀንሱበት መንገድ ለማመቻቸት ጥረት እንዲደረግ ጠይቋል። ለጠየቃቸው ጥያቄዎችም ፈጣን እና ተገቢ መልስ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቋል።ደብዳቤው ይህን ይመስላል
መቐለ ሰባ እንደርታ በአፍሪካ ውድድር ተሳትፎ ዙርያ ተቃውሞውን ገለፀ
አምስት ክልሎች ከአራት መቶ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለማቅረብ አቅደው ስላሳ ሶስት ኪሎ ግራም ብቻ አቀረቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው ህገወጥ የማእድን ዝውውር በማእድኑ ዘርፍ ላይ አደጋ መጋረጡ ተገለፀ። የማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን የስራ ሀላፊዎች ሰኞ መስከረም ሀያ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የኮንትሮባንድ ንግድ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅእኖ በአሀዝ አስደግፈው ገልፀዋል። የማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማእድናት ግብይት አዋጅን አፀድቆ ወርቅ በባህላዊ አምራቾች ተመርቶ ለብሄራዊ ባንክ እንዲቀርብ የገበያ ሰንሰለት ቢዘረጋም፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የወርቅና ጌጣጌጥ ማእድናት በህገወጥ መንገድ በተለያዩ መንገዶች ከአገር እየወጡ መሆኑንና ይህም በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ሀላፊዎቹ ገልፀዋል። አገሪቱ በአጠቃላይ ከማእድናት የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ እያሽቆለቆለ እንደመጣም ተገልጿል። በሁለት ሺህ አራት አመተ ምህረት ከማእድናት ወጪ ንግድ ስድስት መቶ ሀምሳ ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቶ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ገቢ በየአመቱ እየቀነሰ መጥቶ በተጠናቀቀው የሁለት ሺህ በጀት አመት አርባ ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደተገኘ ተነግሯል። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት እየተስፋፋ የመጣው የኮንትሮባንድ ንግድ እንደሆነ ተመልክቷል። በማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የገበያ ልማት ትስስርና ትንበያ ዳይሬክተር አቶ በትሩ ሀይሌ፣ የኮንትሮባንድ ማእድናት ንግድ ዋነኛ ችግር እንደሆነ ገልፀዋል። እንደ አቶ በትሩ ገለፃ በሁለት ሺህ በጀት አመት ከማእድናት ወጪ ንግድ ሁለት መቶ ስልሳ አምስት ነጥብ ስምንትሁለት ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማስገባት የታቀደ ቢሆንም፣ በሀምሌና በነሀሴ ወር የታየው አፈፃፀም አመርቂ አይደለም። በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ከአምስቱ ወርቅ አምራች ክልሎች የቀረበው የወርቅ መጠን ከእቅዳቸው ጋር ሲነፃፀር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። የትግራይ ክልል በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አንድ መቶ ስላሳ አንድ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ለማቅረብ አቅዶ፣ ያስገባው አራት ነጥብ ስምንትሁለት ኪሎ ግራም ወርቅ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል። የኦሮሚያ ክልል በተመሳሳይ አንድ መቶ ስላሳ አንድ ኪሎ ግራም ወርቅ ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብ አቅዶ፣ ያስገባው አንድ ነጥብ አራትስምንት ኪሎ ግራም ብቻ ነው። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሀምሳ አንድ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ለማቅረብ አቅዶ፣ ያስገባው ነጥብ ሰባትአራት ኪሎ ግራም ብቻ ነው። የጋምቤላ ክልል አርባ አንድ ኪሎ ግራም ወርቅ ለባንኩ ለማቅረብ አቅዶ፣ ያስገባው ሰባት ነጥብ አምስት ኪሎ ግራም ብቻ ነው። የተሻለ አፈፃፀም ያሳየው የደቡብ ክልል ሀምሳ ኪሎ ግራም ወርቅ ለባንኩ ለማቅረብ አቅዶ፣ ነጥብ ሶስትአንድ ኪሎ ግራም አስገብቷል። በአጠቃላይ አምስቱ ክልሎች ከአራት መቶ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለማቅረብ ቢያቅዱም፣ ስላሳ ሶስት ነጥብ ስምንትአራት ኪሎ ግራም ወርቅ ብቻ አቅርበዋል። በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚያመርቱት አምስቱ ክልሎች አፈፃፀም ሲታይ፣ ስምንት ነጥብ ሶስት በመቶ ብቻ እንደሆነ አቶ በትሩ ገልፀዋል። በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ኢዛና ማይኒንግ በአሁኑ ወቅት በኩባንያ ደረጃ በከፍተኛ የወርቅ ምርት የተሰማራ ብቸኛ ኩባንያ ሲሆን፣ አንድ መቶ ኪሎ ግራም ወርቅ ለማምረት አቅዶ አንድ መቶ ስምንት ኪሎ ግራም ወርቅ በማምረት ዘጠና ሰባት ነጥብ ሶስት በመቶ አፈፃፀም እንዳለው ተናግረዋል። በአጠቃላይ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ለብሄራዊ ባንክ አንድ መቶ ሀምሳ ኪሎ ግራም ወርቅ ቀርቦ አምስት ነጥብ አራትሁለት ሚሊዮን ዶላር እንደተገኘ ተገልጿል። ለማእከላዊ ገበያ የሚቀርበው የወርቅ መጠን እያሽቆለቆለ የመጣው በኮንትሮባንድ ንግድ ምክንያት መሆኑን ሀላፊዎቹ ገልፀው፣ በአገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ እንደሆነ ተናግረዋል። ማእድናት የሚመረቱት በርቀት ባሉ ቦታዎች በመሆኑ የክልል መንግስታት የማእድናት ምርት ህጋዊ የገበያ ስርአትን ተከትሎ ለማእከላዊ ገበያ መቅረቡን በማረጋገጥ በኩል ትልቅ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። የማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ህገወጥ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመቆጣጠር ከብሄራዊ ባንክ፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር ተባብሮ በመስራት ላይ እንደሆነ አቶ በትሩ ተናግረዋል። የማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማእድናት ግብይት ህግ ማሻሻሉን፣ የወርቅ ግዥ ማእከላት በየክልሉ እንዲከፈት ማድረጉን፣ ተጨማሪ የግዥ ማእከላት ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኑንና በጥሬ ኦፓል የመሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ገልፀዋል። ኮንትሮባንድ ነጋዴዎችን ለመዋጋት ህዝቡ በስልክ ጥቆማ የሚሰጥበት ነፃ የስልክ መስመር ስድስት ሺህ ስላሳ ስምንት መዘጋጀቱም ተገልጿል። የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሸናፊ ባሳ፣ ከህዝብ በሚደርሳቸው መረጃ መሰረት የመስሪያ ቤታቸው የቁጥጥር ጣቢያዎች ከፍተኛ መጠን ያላቸው ወርቅና ሌሎች የከበሩ ማእድናትን በመያዝ ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል። እነዚህ ማእድናት የአገራችንን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ትልቅ ድርሻ ያላቸው ቢሆኑም፣ ሳንጠቀምባቸው በድንበር እየወጡ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ አደጋ እያስከተሉ እንደሆነ አቶ አሸናፊ ገልፀዋል። እኛ እስከ ሰባትና ስምንት ኪሎ ግራም ወርቅ እየያዝን ነው። ይህ ምን አልባት የማእድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአንድ ክልል ወደ ማእከላዊ ገበያ አስገባለሁ ብሎ በእቅድ ከያዘው መጠን ጋር የሚስተካከል ነው። እኛ የምናወራው በክትትል በእጃችን ስለያዝነው ወርቅ ነው። ያልተያዘውና አምልጦ በድንበር የወጣው ወርቅ ምን ያህል ነው ብለን ማሰብ ይኖርብናል፤ ብለዋል። የጉምሩክ ኮሚሽን ከህዝብና አጋር መስሪያ ቤቶች ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ አቶ አሸናፊ ገልፀው፣ በተለይ የሀብረተሰቡ ትብብር ኮንትሮባንድን ለመዋጋት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። ነፃ የስልክ መስመር መዘጋጀቱን፣ ጥቆማ ለሚያቀርቡ ግለሰቦች ወረታ እንደሚከፈልና መረጃው በሚስጥር እንደሚያዝ አረጋግጠዋል። ከሀብረተሰቡ የሚደርሱን ጥቆማዎች ተጣርተው ትክክለኛነታቸው ከተረጋገጠ ወረታ እንከፍላለን። በጠቋሚዎች ላይ አደጋ እንዳይደርስ መረጃው በከፍተኛ ሚስጥራዊነት ይያዛል። ጉምሩክ ኮሚሽን ገንዘብ ሰብሳቢ ብቻ ሳይሆን የደሀንነት መስሪያ ቤት ባህሪ ያለው ነው፤ ብለዋል። ሀብረተሰቡ ኮንትሮባንድ በአገር ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ተገንዝቦ፣ ከጉምሩክ ኮሚሽንና የፀጥታ አካላት ጋር ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ሀላፊዎቹ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ኮንትሮባንድ በማእድን ዘርፉ ላይ አደጋ መጋረጡ ተገለፀ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት ሀያ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በአሁን ወቅት በህዝብ ጤናና ደሀንነት ላይ በተለያዩ መንገዶች ሽብር የሚነዙ አካላት ላይ የህግ አስከባሪ አካላት ህግ የማስከበር ተግባራቸውን በጥብቅ እንዲያከናውኑ መታዘዛቸውንየጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፅህፈት ቤቱ በኢትዮጵያ ከተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የመረጃ አሰጣጥን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም የጤና ቀውስ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲከሰት የተሳሳተ መረጃን ተቀብሎ ማሰራጨት ከቀውሱ እኩል ጎጂ ነው ብሏል። ማንኛውም ዜጋ በእንደዚህ አይነት ወቅት የሀሰት ዜናዎችን ለማስቆም የሚችለውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት በመግለጫው አሳስቧል። የፌደራል መንግስት ኮቪድ ን በተመለከተ በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት መረጃን የማደራጀት እና በየእለቱ የማሰራጨት ስራን እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጣው ኮሚቴ እና ሌሎች አበይት ኮሚቴዎች ያላቸውን ወቅታዊ የስራ ክንውን እያስተባበረ እና መረጃን እያስተላለፈ መሆኑን ገልጿል። ፅህፈት ቤቱ ህዝቡ እንዲህ ባለው አስከፊ ጊዜ የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት ከሚንቀሳቀሱ አካላት ነቅቶ ራሱን እንዲጠብቅ ጠይቋል። የህብረተሰብ ጤና መረጃን ማዛባት እና በዜጎች መካከል ፍርሀት እና ረብሻን መንዛት በወንጀል የሚያስጠይቅ ሀገራዊ አንድነትን የሚያናጋ ተግባር ነው ብሏል። በኮቪድ ላይ መረጃን የሚሰጡ አበይት አካላት የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሀብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት መሆናቸውን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል።
በህዝብ ጤናና ደሀንነት ላይ በተለያዩ መንገዶች ሽብር የሚነዙ አካላት ላይ የህግ አስከባሪ አካላት ህግ የማስከበር ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ታዘዋል የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የአል አህሊው ኮከብ ሳላዲን ሰኢድን የብሄራዊ ቡድኑ አምበል አድርገው መሾማቸውን ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በይፋ ተናግረዋል።አሰልጣኙ ሳላዲንን ለአምበልነት የመረጡት ልምዱ ለመሪነት የሚያበቃው ስለሆነ ተናግረዋል። ሳላዲን በብሄራዊ ቡድኑ ከፍኛ ልምድ አካብቷል። የመምራት ልምዱ እንድመርጠው አድርጎኛል። በሀይሉ አሰፋ ደግሞ ሁለትኛ አምበል አድርገን መርጠነዋል። ብለዋል።ባለፈው ሳምንት ስዩም ተስፋዬ አምበል መደረጉ ከጭምጭምታ ያለፈ እንዳልሆነም አሰልጣኙ አብራርተዋል። የስዩም አምበልነት በጭምጭምታ ደረጃ የተወራ ነው። አርባ አራት ተጫዋቾች በመረጥንበት ሰአት ስዩም እና በሀይሉ ካሉት ውስጥ ልምድ ያላቸው ስለሆኑ እንዲያስተባብሩና ለተጫዋቾቹ ተጠሪ እንዲሆኑ ነበር የመረጥናቸው። ይህ ማለት ግን አምበል አድርገን መርጠናቸዋል ማለት አልነበረም። ምክንያቱም አሳማኝ አቋም ካላሳዩ ከሚቀነሱት ተጫዋቾች መካከል ሊሆኑ ይችሉ ነበር። ሲሉ አብራርተዋል።
የሳላዲን ልምድ ለአምበልነት እንድንመርጠው አድርጎናል ዮሀንስ ሳህሌ
በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ ሂደት ተስፋን ይዞ የመምጣቱን ያህል በተቃራኒው ስጋቶችንም ያዘለ እንደሆነ በአፅንኦት መገምገሙን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ኢህአዴግ በመግለጫው እንዳለው ለዉጡ አሁንም ህዝባዊ መሰረት ይዞ በኢህአዴግ እየተመራ ያለ ቢሆንም በፀረ ለውጥ አስተሳሰብ አራማጆች በተቀናጀ መንገድ እየተመሩ ተግዳሮት እየፈጠሩ ናቸው። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ላለፉት ሶስት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በድርጅቱ ውስጥም ሆነ በለዉጡ ሂደት የተሟላ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት የለም። የታችኛው መዋቅርም ለውጡን በተሟላ መልኩ አለመደገፉ እና በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ያሉ የአካሄድ ዝንፈቶችና የእርስ በርስ መጠራጠር በግልፅ ተነስተው ትግል ተደርጎባቸዋል ብሏል። እናም እነዚህን ችግርች በቀጣይ እንዲስተካከሉ ለማድረግና ለውጡን ለማስቀጠል የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ መግባባት ላይ መድረሳቸውን መግለጫው አመልክቷል ። መግለጫው እንዳለው ከለውጡ በተቃራኒ ያሉ ሀይሎች ህዝቡን ለማደናገርና ድጋፍ ለማግኘት እንዲያመቻቸው ለውጡን ተከትሎ ያሉ የአመራር ግድፈቶችን፤ እንዲሁም ማንነትንና ሌሎች አጀንዳዎችን ምክንያት በማድረግ ፅንፈኛ አካሄድ እየተከተሉ ናቸው። የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈፀም ሲሉም በዜጎች ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስና ዜጎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረጉ ናቸው ሲልም ወንጅሏል። የለውጡ አደናቃፊ ሀይሎች በህገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር በመታገዝ ግጭትና መፈናቀል እንዲፈጠር፣ ኮንትሮባንድና ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በመሰሉ የኢኮኖሚ አሻጥሮች በመሳተፍ ለውጡን ለመግታት እየተረባረቡ እንደሚገኙም ገምግሟል። አንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ፅንፈኝነትን በመስበክ የቆየውን የህዝቦች አንድነት በመሸርሸርና የህግ የበላይነትን ባለማክበር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ነው ያለው። እናም ከዚህ ተግባራቸው በመቆጠብ በሀሳብ ልእልና እና በውይይት ለመድብለ ፓርቲ ስርአቱ መጎልበት ገንቢ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል። በሀገሪቱ አሁን ላይ ጎልተው የሚታዩት ተግዳሮቶች የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ችግር፣ የስራ ተልእኮ አፈፃፀም መዳከም እና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ እሴት መታጣት መሆናቸውን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስምሮበታል። የመገናኛ ብዙሀንም የህዝቦች አንድነት የሚያጠናከርበትንና የተሻለች ሀገርን ለመገንባት የሚያስችል አተያይ በመፍጠር በኩል ተአማኒነታቸውን የሚፈታተን የስርጭት ችግር እንዳለባቸው ኮሚቴው ገምግሟል። ለዉጡ ያስፈለገው በትናንቱ ለመቆዘም ሳይሆን ወደፊት ለመወንጨፍ ቢሆንም ሚዲያው የህዝቡን አተያይ በመቅረፅ ረገድ ግን ብዙ ይቀረዋል ብሏል የኢህአዴግ መግለጫ። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሀኑ አሉታዊ ሚናው እየጎላ መምጣቱን ገምግሞ ከለውጡ ጋር በተዛመደ መልኩ የሚታረምበትን አካሄድ መከተል እንደሚገባ አመላክቷል። በኢኮኖሚው መስክ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ መኖሩን የገለፀው ኢህአዴግ ይህም ከፍተኛ የስራ አጥነት፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት፣ የብድር ጫና ማስከተሉንና አሁንም መዋቅራዊ ችግሩ ያልተፈታ መሆኑንም ገምግሟል።
በኢትዮጵያ የተከሰተው የለውጥ ሂደት ስጋቶችንም ያዘለ ነው ተባለ
ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለማስከበርና የህዝብና የዜጎችን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም ቀን አመተ ምህረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገ ሲሆን በቅርቡ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተስተዋለውን የፀጥታ መደፍረስ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር አድርጎ የህዝቡን ሰላምና ፀጥታ ወደ ነበረበት ለመመለስ በየቦታው ለታየው ሁከት ረብሻና ስርአት አልበኝነት ዋንኛ መገለጫ በሆኑ አውዳሚ ተግባራት ላይ የተጣለውን ክልከላ እንዲሁም ክልከላዎቹ ሲጣሱ በአዋጁ መሰረት የሚወስዱ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን በመለየት አስቀድሞ ለህዝብ ማሳወቅ እንዲሁም አዋጁ ተፈፃሚ ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ክልከላዎቹን ጥሰው በሚገኙ ሰዎችና ድርጅቶች ላይ ተገቢውን የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ሆኖ ስለተገኘ የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥርመስከረም ቀን አመተ ምህረት አንቀፅ እና በደንቡ አንቀፅ በተፈቀደው መሰረት የሚከተለው መመርያ ወጥቷል።ክፍል አንድየተከለከሉ ተግባራት ንኡስ ክፍል አንድበማንኛውም የአገሪቱ ክፍሎች የተከለከሉ ተግባራትአንቀፅ ሁከትና ብጥብጥ የሚያስነሳ ቅስቀሳና ግንኙነት ማድረግማንኛውም ሁከት ብጥብጥና በህዝቦች መካከል መጠራጠርና መቃቃር የሚፈጥር ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳ በማናቸውም መልኩና ዘዴ ማድረግ ፅሁፍ ማዘጋጀት ማተምና ማሰራጨት ትእይንት ማሳየት በምልክት መግለፅ ወይም መልእክትን በማናቸውም ሌላ መንገድ ለህዝብ ይፋ ማድረግ ፍቃድ ሳይኖር ማንኛውንም ህትመት ወደ አገር ውሰጥ ማሰገባት ወይም ወደ ውጪ አገር መላክመልእክት በኢንተርኔት በሞባይል በፅሁፍ በቴሌቪዥን በሬዲዮ በማህበራዊ ሚድያ ወይም ሌሎች የግንኙነት ዘዴዎች መለዋወጥ።አንቀፅ ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ማድረግበሽብር ከተሰየሙ ድርጅቶችና ከፀረ ሰላም ቡድኖች ጋር ማናቸውንም ግንኙነት ማድረግየአሽባሪ ድርጅቶችን የተለያዩ ፅሁፎች መያዝ ማሰራጨት አርማቸውን መያዝ ወይም ማስተዋወቅየቴሌቪዥን ወይም የሬድዮ ፕሮግራምን መከታተል የኢሳት የኦኤምኤን እና የመሳሰሉትን የሽብርተኛ ድርጅቶች ሚዲያዎችን ማሳየት መከታተልና ሪፖርት ማድረግ የተከለከለ ነው።አንቀፅ ያልተፈቀደ ሰልፍና የአደባባይ ስብሰባየህዝብና የዜጎች ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ከኮማንድ ፓስቱ ፈቃድ ውጭ ማናቸውም ሰልፍና የአደባባይ ስብሰባ ማድረግ የተከለከለ ነው።አንቀፅ ለህዝብ አገልግሎት አለመስጠትህዝብ የሚጠቀምባቸውን ወይም ፈቃድ የወጣባቸው የንግድ ስራዎች ሱቆች ወይም የመንግስት ተቋማት መዝጋት ወይም ምርትና አገልግሎት ማቋረጥ ከስራ ቦታ ያለ በቂ ምክንያት መጥፋት ወይም ስራ ማቆም ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት ስራን መበደልየመንግስት ወይም የግል ተቋማት ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዳይገቡ መዛትና ማስፈራራት የተከለከለ ነው።አንቀፅ በትምህርት ተቋማት አድማ ማድረግበትምህርት ቤቶች በዩኒቨርስቲዎችና በሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያውክ አድማ ማድረግ የትምህርት ተቋማትን መዝጋት ወይም በነዚህ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረግ የተከለከለ ነው።አንቀፅ በስፖርት ማዘውተሪያዎች አድማ ማድረግበስፖርት ማዘውተሪያ ማእከላት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆኑ ሁከቶችን ብጥብጦችን መፍጠር የተከለከለ ነው።አንቀፅ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ማወክየተሽከርካሪ የእግረኛና ሌሎች የመጓጓዣ ዘዴዎችን እንቅስቃሴ መንገድ በመዝጋት በዛቻና በሌሎች መሰል ድርጊቶች ሰላማዊ እንቅሰቃሴን ማወክ አገልግሎት ማስተጓጎል የመጓጓዣ ዋጋ ታሪፍ መጨመር የሚመለከተው አካል ከደለደለው የስራ ስምሪት ውጪ መሆን የተከለከለ ነው።አንቀፅ በመሰረተ ልማቶችና ሀይማኖታዊ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረስበግል በህዝብና በመንግስት ማናቸውም ተቋማት በመሰረተ ልማት በኢንቨስትመንትና በሌሎች የልማት አውታሮች እንዲሁም በሀይማኖታዊ ተቋማት ላይ በማንኛውም መንገድ ጉዳት ማድረስ ወይም ዘረፋ መፈፀም የተከለከለ ነው።አንቀፅ ህዝባዊና ብሄራዊ በአላትን ማወክህዝባዊና ብሄራዊ በአላትን በማንኛውም ሁኔታ ማወክ ማደናቀፍ ወይም ከበአሉ አላማ ጋር የማይገናኙ የፖለቲካ አጀንዳዎች ወይም መፈክሮችን በማንኛውም መንገድ ማስተጋባት የተከለከለ ነው።አንቀፅ ሀይማኖታዊ ባህላዊና ህዝባዊ በአላት ላይ ቅስቀሳ ማድረግሀይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ በሚደረጉ ስብከቶችና ትምህርቶች ሀይማኖታዊ አስተምህሮት ከማድረግ ውጪ በህዝቦች መካከል መጠራጠርና መቃቃርን የሚፈጥር በህብረተሰቡ ላይ ስጋት የሚፈጥር ሁከትና ብጥብጥ የሚቀሰቅስ ቅስቀሳ ማድረግ የተከለከለ ነው።አንቀፅ የህግ አስከባሪዎችን ስራ ማወክየህግ አስከባሪ አካላት የሚሰጡትን ማንኛውም ትእዛዝ አለማክበር ስራቸውን ማደናቀፍ ለፍተሻ አለመተባበር ወይም እንዲቆም ሲጠየቅ አለማቆም ኬላዎችን ጥሶ ማለፍ የተከለከለ ነውበህግ አስከባሪ አካላት ባልደረቦች ላይ ጥቃት መፈፀም ወይም ለመፈፀም መሞከር የተከለከለ ነውአንቀፅ ያልተፈቀዱ አልባሳት መልበስየህግ አስከባሪ ሀይሎችን ዩኒፎርም መልበስ ይዞ መገኘት በቤት ማስቀመጥ አሳልፎ መስጠትና መሸጥ ክልክል ነው።አንቀፅ የጦር መሳሪያ ይዞ መግባትማናቸውም የጦር መሳሪያ ስለት ወይም እሳት የሚያስነሱ ነገሮችን ወደ ገበያ ሀይማኖት ተቋማት ህዝባዊ በአላት የሚከበሩበት ወይም ወደ ማናቸውም ህዝብ የሚሰበሰብበት ቦታ ይዞ መግባት የተከለከለ ነው።አንቀፅ ትጥቅን በሶስተኛ ሰው እጅ እንዲገባ ማድረግማንኛውም የህግ አስከባሪ አካላት ባልደረባ ወይም ማንኛውም ህጋዊ ትጥቅ ያለው ሰው ትጥቁን በማንኛውም ሁኔታ በሶስተኛ ሰው እጅ እንዲገባ ማድረግ ክልክል ነው።አንቀፅ መቻቻልንና አንድነትን የሚጎዳ ተግባር መፈፀምማንነትን ወይም ዘርን መሰረት ያደረገ ማንኛውም አይነት ጥቃት መፈፀም ወይም ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሳ ንግግር መናገር የተከለከለ ነው።አንቀፅ የአገርን ሏላዊነት ደህንነት ህገ መንግስታዊ ስርአት የሚጎዳ ተግባር መፈፀምማንኛውም ሰው ከውጭ መንግስታትም ሆነ ከውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የአገር ሏላዊነት ደህንነትና ህገ መንግስታዊ ስርአትን ሊጎዳ የሚችል ግንኙነትና የመልእክት ልውውጥ ማድረግ የተከለከለ ነው።ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የአገርን ሏላዊነት ደህንነትና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ማናቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሚዲያዎች መስጠት ክልክል ነው።አንቀፅ ያልተፈቀደ ቦታ መገኘትከስደተኛ ካምፕ አግባብ ካለው አካል ከሚሰጥ ፈቃድ ውጭ መውጣት ወይም ህጋዊ ቪዛ ሳይኖረው ወደ አገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው።አንቀፅ ያለፈቃድ ስለሚደረግ የዲፕሎማቶች እንቅስቃሴየኮማንድ ፖስቱ እውቅናና ፈቃድ ሳያገኙ ዲፕሎማቶች ለራሳቸው ደህንነት ጥበቃ ሲባል ከአዲስ አበባ ከአርባ ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውጪ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።አንቀፅ የህግ አስከባሪ አካላት ግዳጅ ላይ ስለመገኘትማንኛውም የህግ አስከባሪ አካል ባልደረባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈፃሚ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ መልቀቅ ወይም አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የአመት እረፍት ፍቃድ መውሰድ ክልክል ነው።አንቀፅ የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ ድጋፍ ማድረግበዚህ መመርያ የተከለከሉ ተግባራትን በመተላለፍ ህገወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ ሰዎችን በገንዘብና በቁሳቁስ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ መደገፍ እንዲሁም ከለላ መስጠት መደለያ መስጠት ማበረታታት የተከለከለ ነው።ንኡስ ክፍል ሁለትበተወሰኑ የአገሪቱ አካባቢዎች እንዳይፈፀሙ የተከለከለ ተግባራትከላይ በንኡስ ክፍል አንድ የተደነገነገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከአንቀፅ የተዘረዘሩት ክልከላዎች ኮማንድ ፖስቱ እየወሰነ ይፋ በሚያደረጋቸው ቦታዎች ወይም አካባቢዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ።አንቀፅ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስማናቸውም የጦር መሳሪያ ስለት ወይም እሳት የሚያስነሱ ነገሮችን ከግቢውና ይዞታው ውጪ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።አንቀፅ በልማት አውታሮችና መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘር ጥቃትየኢኮኖሚ አውታሮች መሰረት ልማትና የኢንቨስትመንት ተቋማት የእርሻ ልማቶች በፋብሪካዎችና በመሰል ተቋማት አካባቢ ከቀኑ ሰአት በኋላ እስከ ንጋት ሰአት ድረስ ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ማንኛውም ሌላ ሰው መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ከላይ በተመለከቱት ቦታዎች የሰአት እላፊውን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የጥበቃ ወይም የህግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።ክፍል ሁለትየተከለከሉ ተግባራት ተፈፅሞ ሲገኝ ስለሚወሰዱ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችአንቀፅ እርምጃ ለመውሰድ ስልጣን ስላለው ሰውከላይ በክፍል አንድ ከአንቀፅ እስከ የተመለከቱ የተከለከሉ ተግባራትን ፈፅመው በተገኙ ሰዎችና ድርጅቶች ላይ የህግ አስከባሪዎችና ባልደረቦቻቸው በአዋጁና በዚህ መመርያ የተዘረዘሩ የሚከተሉትን የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይችላሉ።አንቀፅ ክልከላዎች ሲጣሱ ስለሚወሰዱ እርምጃዎችከላይ በክፍል አንድ የተመለከቱ ክልከላዎችን ተላልፈው በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የህግ አስከባሪዎችያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋልአዋጁ ተፈፃሚነቱ እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ ኮማንድ ፖስቱ በሚወስነው ቦታ እንዲቆይማድረግተገቢውን የተሀድሶ ትምህርት በመስጠት የሚለቀቀውን እንዲለቀቅ ወደ ፍርድ ቤትየሚቀርበውን ደግሞ እንዲቀርብ ማድረግያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በማናቸውም ሰአት ብርበራ ለማድረግ የአካባቢውን ህዝብና ፖሊስ በማሳተፍ ማንኛውንም ወንጀል የተፈፀመበት ወይም ሊፈፀምበት የሚችል ንብረት መያዝ ወይም ንብረቱ ባለበት እንዲጠበቅ ማድረግበማንኛውም ሬድዮ ቴሌቪዥን ፅሁፍ ምስል ፎቶ ግራፍ ቲያትርና ፊልምየሚተላለፉ መልእክቶችን መቆጣጠርና መገደብየተዘረፉ ንብረቶችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግበትምህርት ተቋማት ሁከትና ረብሻ ተሳትፎ በሚያደርጉ ተማሪዎችና ሰራተኞች ላይ ህጋዊ እርምት መውሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለተቋማቱ ትእዛዝ መስጠትማንኛውም የህዝብን ሰላምና ፀጥታን ሊያደፈርሱ ይችላሉ ወይም ለጉዳት ተጋላጭይሆናሉ ተብለው የሚጠረጠሩና የሚታሰቡ ሰዎችን ወይም ቡድኖችን ወደ ተወሰነ አካባቢእንዳይገቡ እንዳይገኙ ወይም በተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ ማድረግ እናአግባብነት ያላቸውን እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል።አንቀፅ ስለ ሰአት እላፊማናቸውም ሰው በኮማንድ ፖስቱ ውሳኔ የሰአት እላፊ በይፋ በሚገለፅበት ቦታና ጊዜ የሰአት እላፊ ክልከላን በመተላለፍ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አይፈቀድም።አንቀፅ ሁከትን ለማስቆምና አደጋን ለመከላከል የሚደረግን እንቅስቃሴ ማወክሰላምና ፀጥታን ሊያደፈርሱ ይችላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች ወይም ቡድኖችን ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ሰዎች ወይም ቡድኖች ወደ ተወሰነ አካባቢ ወይም ህንፃ እንዳይገቡ ወይም በተፈቀደላቸው አንድ የተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ የተሰጠውን ትእዛዝ መተላለፍ ክልክል ነው። ለአካባቢው ደህንነት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ወደ ተዘጋ መንገድ ማንም ሰው እንዳይገባ ኮማንድ ፖስቱ የሰጠውን እግድ ወይም ክልከላ መተላለፍ ክልክል ነው።ንኡስ ክፍል ሶስትመረጃ የመስጠትና የማስታወቅ ግዴታአንቀፅ የተከራይ መረጃ የመያዝና የመስጠት ግዴታማንኛውም ቤት ቦታ ክፍል ወይም ተሽከርካሪ ወይም ተመሳሳይ መገልገያ አከራይ የሆነ ሰው የተከራዩን ማንነት በዝርዝርና በፁሁፍ የመያዝና በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ በ ሰአት ውስጥ የማሳወቅ ግዴታ አለበት። በተጨማሪም የውጭ አገር ዜጋን ያከራየ እንደሆነ የፓስፖርቱን ኮፒና የኪራዩን ውል በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት።አንቀፅ መረጃ የመስጠት ግዴታየህዝብ ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ማንኛውም ተቋም መረጃ እንዲሰጥ በየደረጃው ባለ የህግ አስከባሪ አካል ሲጠየቅ የመስጠትና የመተባበር ግዴታ አለበት።አንቀፅ ራስን ለመከላከል በህግ አስከባሪዎች ስለሚወሰድ እርምጃህግ አስከባሪዎችናቀ በድርጅቶች ጥበቃ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ከላይ የተመለከቱትን ክልከላዎች እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጦር መሳሪያ ወይም በስለትና ህይወታቸውንና ንብረታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ጥቃት በተሰነዘረባቸው ጊዜ ራሳቸውን ለመከላከል የሚያስችላቸውን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።አንቀፅ በትምህርት ተቋማት የመግባት ስልጣንበትምህርት ቤቶች በዩኒቨርስቲዎችና በሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያደርጉ ሰዎችን ለመያዝና ችግሩን ለማስቆም የህግ አስከባሪ አካላት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ በመግባት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ እንዲሁም በሌሎች የግልና የመንግስት ተቋማት ውስጥ አድማ የሚያድርጉ ሰዎችን ለመያዝና ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የህግ አስከባሪ አካላት ባልደረቦች በእነዚህ ተቋማት ውስጥ ለመግባት እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ ሊቆዩ ይችላሉ።ክፍል ሶስትተሀድሶና ፍርድ ቤት ስለማቅረብአንቀፅ በህግ መሰረት በኮማንድ ፖስቱ የሚደረግ የተሀድሶ እርምጃዎችለፍርድ መቅረብ ያለበትን ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ያደርጋልባለፈው አንድ አመት ውስጥ በተፈፀሙ ሁከትና የብጥብጥ እንቅስቃሴዎች ላይ በቡድንወይም በግል የተሳተፈናሀ የጦር መሳሪያ ወይም ማንኛውንም የግልም ሆነ የመንግስት ንብረት የዘረፈናበአቅራቢያው ለሚገኝ የህግአስከባሪ ሀይልየዘረፈውን መሳሪያና ንብረት ይህመመርያ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ በአስር ቀናት ውስጥ በአቅራቢያው ላለ ፖሊስጣቢያየመለሰና እጁን የሰጠ ሰውለ ከዚህ በፊት ለህገወጥ ተግባራት የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገና ይህ መመሪያበወጣ በአስር ቀናትውስጥ ለፖሊስ ጣቢያ እጁን የሰጠ ሰውሀ ወረቀት በመበተን አድማ በማድረግ የተሳተፈ ያነሳሳ ሰው ይህ መመርያ በወጣአስር ቀናት ውስጥ ለፖሊስ ጣቢያእጁን የሰጠ ሰውመ ሰው የገደለ ማንኛውንም ንብረት ያቃጠለ ማንኛውንም ወንጀል የፈፀመ ይህመመሪያ ከወጣበት ጊዜጀምሮ በአስር ቀናት ውስጥ ለፖሊስ ጣቢያ እጁን የሰጠ ሰውእንደ የወንጀል ተሳትፎው ቀላልና ከባድነት ዋና ፈፃሚና አባሪ ተባባሪመሆኑ ታይቶ በኮማንድ ፖስቱ የተሀድሶ ትምህርት ተሰጥቶት እንዲለቀቅ ይደረጋል።
አልሞት ባይ ወያኔ ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃ አፈፃፀም መመርያ
ኢሳት መጋቢት የታንዛኒያ መንግስት ከኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ ወደሀገሩ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ረቡእ አስታወቀ።ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ መግባታቸውን ያስታወቀው የታንዛኒያ ፖሊስ በተያዘው ሳምንት ተጨማሪ ስድስት ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።ወደሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉት ኢትዮጵያውያንም ከነገ በስቲያ አርብ ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ እንደሚመሰረትባቸው ዘጋርዲያን የተሰኘ የታንዛኒያ ጋዜጣ ዘግቧል።ከቀናት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን እድሜያቸው በ እና ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን መዳረሻቸውም ደቡብ አፍሪካ እንደነበር ታውቋል።ከታንዛኒያ በተጨማሪ የማላዊ እንዲሁም የዛምቢያ መንግስታት ወደሀገራቸው የሚገቡ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በየመን መውጫን አጥተው እንደሚገኙና ችግሩ እልባት ባላገኘበት ወቅት ወደ ሀገሪቱ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ስጋት ፈጥሮ እንደሚገኝ ይፋ ማድረጉም ይታወሳል። በየእለቱ በትንሹ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን የሚገቡባት ኬንያ በበኩላ በድንበር ዙሪያ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎቿን በማብዛት ከኢትዮጵያ የሚሰደዱ ሰዎችን ለመግታት ጥረት መጀመሯን ገልፃለች።ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች በመሰደድ ላይ መሆናቸውንም የተለያዩ አካላት አስታውቀዋል።
ወደታንዛኒያ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለፀ
ነገረ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ኙ ፓርቲዎች ህዳር ለሚያደርጉት የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በፖስታ ቤት የተላከለትን ደብዳቤ አልቀበልም ማለቱን የስብሰባው አስተባባሪ የሆነው የመኢዴፓ ፀሀፊ አቶ ዘመኑ ሞላ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ። የኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር አመተ ምህረት ለሚያደርጉትና መኢዴፓ ለሚያስተባብረው ስብሰባ ረቡእ ህዳር የመኢዴፓ አመራሮች ደብዳቤውን ለማስገባት ሄደው የነበር ቢሆንም አቶ ማርቆስ ብዙነህ እና እሳቸውን ተክተው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ፈለቀ ታመዋል በሚል የከንቲባ ጉዳይ የካቢኔዎች ሀላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ማሳወቂያ ደብዳቤውን አንቀበልም ማለታቸው ይታወቃል። በተመሳሳይ ህዳር ወደ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ያቀኑት የትብብሩ አመራሮች ደብዳቤውን የሚቀበላቸው ሲያጡ ጠረጴዛ ላይ ጥለውት የመጡ ሲሆን በፖስታ ቤት በሪኮመንዴ እንደላኩ የትብብሩን ፀሀፊ አቶ ግርማ በቀለን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። ለአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በፖስታ የተላከውን ደብዳቤ ቢደርስም አመራሮቹና ሰራተኞቹ ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ፖስታ ቤት ድረስ በመሄድ እንዳረጋገጡ አቶ ዘመኑ ሞላ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ሰራተኞችና አመራሮች ፖስተኛው ደብዳቤው የሚሰጥበትን ቢሮ ሲጠይቅ ለማሳየት ፈቃደና እንዳልሆኑና በስተመጨረሻም ተቀባይ የለውም ብለህ መለስ። እንደተባሉት አቶ ዘመኑ ሞላ ገልፀዋል።
የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል በፖስታ የተላከውን የኙ ፓርቲዎች ትብብር ደብዳቤ አልቀበልም አለ
ባለቤቴ የጉሙዝ ተወላጅ ነው። እኔ ደግሞ የኦሮሞ ተወላጅ፤ ሁለታችንም የብሄር ጉዳይ በመካከላችን ሳይኖር በትዳር ልጆች አፍርተን አብረን እንኖራለን። እኔን ከባለቤቴ ማነው የሚለየኝ፤ በማለት ሀሳባቸውን የሰጡት ወይዘሮ ድርቤ ጉማ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሁለት አመተ ምህረት ጀምሮ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ይኖራሉ። በጋብቻ፣ በጉርብትና እና በአካባቢ በማህበራዊ ኢኮኖሚ ተሳትፎ በቆየው የቤንሻንጉል ጉሙዝና የኦሮሞ ተወላጆች መካከል ይህ ነው የሚባል ችግር እንዳላዩ የሚናገሩት ወይዘሮ ድርቤ፤ በቅርቡ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የተከሰተው ችግር እንግዳ ሆኖባቸዋል። ኦሮሞ ሰንጋ ጥሎና ጠምቆ ከጎረቤቱ እና ከአካባቢው ጋር የሚበላ ጥሩ ባህል ያለው፤ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ህዝብም ያለውን አካፍሎ አብሮ የሚኖር መሆኑን ምስክርነት ሰጥተዋል። በሁለቱ ህዝቦች መካከል ጣልቃ የገባውን መንግስት ለይቶ በማውጣት የህዝቡን አብሮ የመኖርና መተሳሰብ መመለስ እንዳለበት ጠይቀዋል። በተለይም ተሳስበው የሚኖሩትን ህዝቦች ለመለያየት በማህበራዊ ድረገፅ የሚሰሩትን መታገል መንግስት ከፍተኛ ድርሻ አለው ብለዋል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ትናንት ለአንድ ቀን በተካሄደው የቤንሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ የጋራ መድረክ ላይ የአሶሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አልሄደር መሀመድም፤ ኦሮሞና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ተጋብተው ያፈሩት ልጅ ለሁለቱም ዳኛ ነው ይላሉ። ሁለቱ ህዝቦች የተሳሰሩ በመሆናቸው አንዱ የሌላውን ጉዳት አይፈልግም። ይልቁንም ትውልዱን ከገባበት ደባል ሱስ በማላቀቅ፤ በመልካም ስነ ምግባር በማነፅና ተተኪ መሪ በመፍጠር ላይ የሁለቱ ክልል አመራሮች እንዲረባረቡ ጠይቀዋል። የሀይማኖት አባቶችና ወላጆች የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል። ከምስራቅ ወለጋ ሳሲጋ ወረዳ በሬዱ ቦሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የተሳተፉት አርሶ አደር መልካሙ አበበ፤ በተፈጠረው ችግር አርሰው በሚበሉትና ከሞቀ መሬታቸው ለወራት ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ መሆናቸው እንዳሳዘናቸው ይገልፃሉ። እርሳቸውም እንደሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ሁሉ በህዝቦች መካከል ችግር እንዳላዩ ይናገራሉ። በእድሜያቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ካዩት የህዝቦች መፈናቀል፣ ሞትና የተለያየ ጉዳት ማዘናቸውን ያስረዳሉ። በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል በተፈጠረ እርቅ ወደ ቀዬአቸው ሰሞኑን ከተመለሱት መካከል መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ መልካሙ፤ የቀሩትም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መንግስት እንዲሰራ ጠይቀዋል። ከጉባኤው ተሳታፊዎች ለተነሱት አስተያየቶችና ለቀረቡ ጥያቄዎች አስተያየት የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ፤ ባለፉት ስድስትና ሰባት ወራት በሁለቱ ክልሎች በተፈጠረው ችግር ህዝብ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ፣ በመካከላቸው የንግድ ልውውጥ እንዳይኖር፣ እንዲሁም ለጤና እና ለማህበራዊ ችግሮች ከመጋለጥ በስተቀር ትርፍ አልተገኘም። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገና ያልተነካ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የሚበቃ ሀብት እያለው አንዳንድ ወገኖች በተለያየ ነገር ጠብ መፍጠርና ለጉዳት መዳረግ አሳፋሪ ድርጊት ነው ያሉት ርእሰ መስተዳደሩ፤ ህዝቡም ይህንን ተገንዝቦ ለልማት እና ለእድገት መነሳሳት እንዳለበት አሳስበዋል። እንደ አቶ ለማ ገለፃ፤ ህዝቡ አንድ እንደሆነ በመድረክ የሚሰጠው አስተያየት በንግግር መቅረት የለበትም። መንግስት ትልቁን ድርሻ ይዞ በልማት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባዋል። ሁሉም ድርሻውን የመወጣት ሀላፊነትም አለበት። የኦሮሚያ ክልል በሁለቱ ህዝቦች መካከል ሰላም እንዲሰፍን የተጀመረውን ጥረት በማጠናከር አጥፊዎችን ለህግ በማቅረብ በኩል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል። በተለይም በልማት በመደጋገፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል። ባለፈው አመት ስራ የጀመረው የኦሮሚያና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሰላምና የልማት ስትራቴጂ እቅድ የዚሁ አካል መሆኑን አመልክተዋል። ከሁለት ሺህ አመተ ምህረት እስከ ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ድረስ የሚቆየው ፕሮጀክት ሰፊ ተግባሮችን እንደሚያከናውን ተናግረዋል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን በበኩላቸው፤ የጉባኤው ተሳታፊዎች በሁለቱ ክልል ህዝቦች አምባሳደር በመሆን ለሰላም እንዲሰሩ አሳስበዋል። ክልሉ ለሁለቱ ህዝቦች ብቻ ሳይሆን በክልሉ ለሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦችም በሰላምና በፍቅር የሚኖሩበት ክልል እንዲሆን ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው፤ በክልሎች መካከል የተጀመረው የጎንዮሽ ግንኙነትና በልማት ለመተሳሰር እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ይገልፃሉ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸው እንደሚቆም ቃል ገብተዋል። ተሞክሮው ተቀምሮ ለሌሎቹ እንደሚስፋፋም ተናግረዋል። በክልሉ ሰላም፣ ልማትና በህዝቦች መካከል የቆየው አብሮነት እንዲጠናከር ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ ለፌዴራልና ክልል መንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።አዲስ ዘመን ሚያዝያ ሁለት ሁለት ሺህ በ
ህዝብ ለህዝብ ያቀራረበው የሰላም ጉባኤ
ጥቅምት ፯ ሰባት ቀን ፳፻፯ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና የተቃዋሚ የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ችላለች በሚል በተደጋጋሚ ቢነገርም አሁንም ስንዴ ከውጭ እያስገባን ነው በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትርንስትሩ በምግብ ራሳችንን መቻላችንን አለማቀፍ ተቋማት ሳይቀር ያረጋገጡት መሆኑን በመግለፅ፣ ኢትዮጵያ በአለፈው አመት ሶስት መቶ ሚሊዮን ኩንታል የግብርና ምርት ማምረት መቻሏን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ የግንቦትሀያ በአል በሚከበርበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትርኒስትሩ ባቀረቡት ንግግር ኢትዮጵያ በተጠቀሰው አመት ሁለት መቶ ሀምሳ ሚሊዮን ኩንታል ማምረቷን ተናግረዋል በአንድ የምርት ዘመን አንድ ጊዜ ሁለት መቶ ሀምሳ ሌላ ጊዜ ሶስት መቶ ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተመርቷል በሚል የሚቀርበው ሪፖርት መንግስት ለህዝብ የሚያቀርበውን ሪፖርት ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ ከቶታል። አትዮጵያ ሀምሳ ሚሊዮን ኩንታል ተጨማሪ ምርት ለማምረት በትንሹ ከ አምስት አመት ያላነሰ ጊዜ የሚወስድባት ቢሆንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትርኒስትሩ በሶስት ወር ውስጥ ተጨማሪ ሀምሳ ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደተመረተ አድርገው ለፓርላማው ያቀረቡት ሪፖርት አጠቃላይ የቀረበውን ሪፖርት ባህሪ የሚያሳይ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል። ኢትዮጵያ ረሀብን በማጥፋት የሚሊኒየም የልማት ግቦችን አሳክታለች በማለት ጠቅላይ ሚኒስትርንስትሩ ያቀረቡት ሪፖርትም ፍፁም ሀሰት መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ድርጅት ያወጣውን ሪፖርት በመጥቀስ ዘግቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ሀያ ስምንት በመቶ ኢትዮጵያውያውያን አሁንም በአስከፊ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑን ያሳያል።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአንድ የምርት ዘመን ሀምሳ ሚሊዮን ኩንታል ልዩነት የታየበት መረጃ ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ውስጥ ከሶስት መቶ ስላሳ ሺህ በላይ ህፃናት ድጋፍና እንክብካቤ የሚያገኙበት የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራም በተሟላ ሁኔታ ወደ ተግባር ሊያስገባ መሆኑ ተገለፀ። ዛሬ በከተማ አስተዳደሩ በሁሉ አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራም ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ የቢግ ዊን ፊላንትሮፒ ሀላፊ ዶክተር ከሰተ ብርሀን አድማሱ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ፥ በመዲናዋ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ህፃናት የአእምሮ እድገት መጠን ችግሮች ተጋላጭ መናቸውን ገልፀዋል። ተገቢውን ትኩረትና እንክብካቤ ማግኘት አለመቻላቸውንና ባለመቻላቸው ምክንያት የወደፊት ህይወታቸው ላይ ተፅእኖ እንደሚያመጣም በአፅንኦት ተናግረዋል። አክለውም ይህ ሁሉ አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራም ትውልድ የሚቀይር ፕሮግራም ነው ብለዋል። ይህ በአፍሪካ መጀመሪያው እንደሆነ የተነገረለት ፕሮግራም፥ በአዲስ አበባ በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ውስጥ በዘጠኝ ፓኬጆች ከሶስት መቶ ስላሳ ሺህ በላይ ህፃናትን ለመድረስ መታቀዱም ተነግሯል። ከነዚህም ውስጥ ቤት ለቤት የሚሰጥ የወላጆች ምክርና ድጋፍ፣ በየመንደሩ የሚከፈት አረንጓዴ የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች፣ የህፃናት ማቆያ ቦታዎች፣የህፃናት አልሚ ምግብ አቅርቦት እና የመሳሰሉት ይገኙበታል። በመድረኩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር ህፃናት ትልቅ ትኩረት የሚፈልጉ መናቸውን ገልፀው፥ ህፃናት ላይ ኢንቨስት ካልተደረገ ሀገር ናትውልድ ችግር ውስጥ እንደሚገባም ሊታወቅ ይገባል ብለዋል። ፕሮግራሙ አላማ ከሶስት አመታት በኋላ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችና ህፃናትን በሙሉ የዚህ ፓኬጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሆነም ጠቁመዋል ። በሚቀጥሉት ጊዜያትም አስተዳደሩ በከተማዋ ቤት ለቤት ክትትልና ድጋፍ የሚያደርጉ አምስት ሺህ ባለሙያዎችን እንደሚቀጥርም ነው ያስታወቁት። ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው ይህ ስራ እንዲሳካ ዋናው የአመራሩ ቁርጠኝነት ነው ማለታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
የመዲናዋ አስተዳደር የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራምን ልተገብር ነው አለ
በአገሪቷ እየተባባሰ የመጣውን የኮንትሮባንድ ንግድ ለመቀነስና ለማስቆም ገቢዎች ሚኒስቴር ለጉምሩክ ስራዎች ብቻ የሚመደብ የፖሊስ ሀይል እንደሚያሰማራ አስታወቀ። የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንዳስታወቁት፣ ተቋሙ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ አዲስ ዘመቻ ማካሄድ ጀምሯል። ስር የሰደደውን የኮንትሮባንድና የህገወጥ ንግድ እንቅስቃሴ እናስቆመዋለን፤ ግን በምን ያህል ፍጥነት እንደምናስቆመው ነው እርግጠኛ መሆን የቀረን፤ ያሉት ሚኒስትሯ፣ ይህንን ከህዝቡ ከተገኘው ድጋፍና ትብብር ባሻገር ህገወጥ የወጪና ገቢ ምርቶችን ዱካ ለማስቆም፣ ተጠሪነቱ ለፌደራል ፖሊስ ሆኖ የሚንቀሳቀስና ብቸኛ ስራውም የኮንትሮባንድ ንግድን የሚመክት የጉምሩክ ፖሊስ እንዲቋቋም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰሞኑን እንደወደወሰነ ሀላፊዋ አስታውቀዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኮንትሮባንድ መንገድ ከሚወጡ ሸቀጦች ይልቅ ትልቅ ቦታ ይዞ የሚታየው የውጭና የአገር ውስጥ የመገበያያ ገንዘቦች ናቸው። ይህ እንዳለ ሆኖ፣ ገቢዎች ትኩረት ከሚሰጥባቸው መካካል የታክስ እፎይታና የታክስ ነፃ መብቶች ላይ የሚታዩ ችግሮች ይገኙበታል። ከሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ጀምሮ ከአራት መቶ ቢሊዮን ብር የታክስ እፎይታና የታክስ እድል መሰጠቱን ሚኒስትሯ አስታውሰው፣ አብዛኛው የታክስ እፎይታና ነፃ እድሎች ላልተገባ ተግባር ይውል እንደነበር ገልፀዋል። በምሳሌነት ከጠቀሷቸው ውስጥ በአፋር ክልል ሀባላ በምትባልና ሁለት ሺህ የማይበልጡ ነዋሪዎች በሚገኙባት ከተማ ውስጥ ሀምሳ አምስት አለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ሆቴሎች ለመገንባት በሚል ሰበብ የቀረቡ የታክስ ነፃና ጥያቄዎች ይገኙባቸዋል። እንዲህ ባለው መንገድ በርካታ ብረት፣ የቤትና የቢሮ እቃዎችና ሌሎችም ያለቀረጥ እየገቡ ሲቸበቸቡ ቆይተዋል።
ገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ፖሊስ እንደሚያሰማራ አስታወቀ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ሶስት ሰራተኞች የተሰጣቸውን ሀላፊነት ወደ ጎን በማለት፣ ስምንት መቶ ሰማኒያ ብር ወጪ አድርገው ለሌሎች በማስተላለፍ የጥቅሙ ተካፋይ ሆነዋል ተብለው ተጠርጥረው ሚያዝያ ሀያ ስምንት ቀን ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት በቁጥጥር ስር ዋሉ። ተጠርጣሪዎቹ የተጠቀሰውን ገንዘብ ወጪ እንዲሆን ያደረጉት የባንኩ ደንበኛ ከሆነው ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ የባንክ ሂሳብ ላይ መሆኑ ታውቋል። የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ ባለመወጣት የወንጀል ድርጊት በመፈፀም የተጠረጠሩት አብዱራህማን አህመድ፣ ሊንዳ አስፋውና ዘካሪያስ ጥላሁን የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው። ከተጠቀሰው ድርጅት ሂሳብ ላይ ገንዘቡን ተቀናሽ በማድረግ ገቢ ያደረጉት ዎክላ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሀበር ለተባለው ድርጅት መሆኑን፣ ድርጊቱን እያጣራው የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት አሳውቋል። ዎክላ በሀሰተኛ ሰነድ የተቋቋመ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሀበር መሆኑን፣ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብርሀንና ሰላም ቅርንጫፍ ከሀያ ሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ከተለያዩ ተቋማት ሂሳብ ላይ ተቀናሽ በማድረግ እነ ሀይለ ማርያም ቤጌናና እነ ድረስ አበበ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በድርጅቱ ስም ሂሳብ በመክፈት ገቢ አድርገውለታል የተባለ ድርጅት መሆኑን የምርመራ ዘርፉ አክሏል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ ቀሪ ምርመራ እንዳለው በማሳወቅ ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርምራ የ ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን የ ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዶ የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለግንቦት ስምንት ቀን ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት ቀጠሮ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስት ሰራተኞች ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር ማጭበርበር ተጠርጥረው ታሰሩ
የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን በጥረት ኮርፖሬት የገንዘብ ምዝበራ ላይ በተጠርጣሪነት ያቀረባቸው አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ የባህዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው አቃቤ ህግ የጠየቀው የ ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቅዷል።ተከሳሾች ክሳችን በክልሉ ሊታይ አይገባም ምክንያቱም በክልሉ የህግ የበላይነት እያየን አይደለም ከዚህ ቀደምም በክልሉ የደቦ ፍርድ እንዲደረግብን ተደርጓል ሲሉ አንስተዋል።እነአቶ በረከት የዋስትና መብታችን ተከብሮ በውጭ ሆነን ልንከራከር ይገባል የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥብንም አይገባም ሲሉም አንስተዋል።አቃቢ ህግ በበኩሉ ምርመራዎች ያልተጠናቀቁ በመሆኑ ሰነዶችም በየቦታው የተበታተኑ በመሆኑ ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ስር አድርጎ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብሏል ከነበሩበት የስልጣን ደረጃ አንፃር መረጃ የማሸሽ አቅማቸው ከፍተኛ ስለሆነ የዋስትና መብት ሊሰጣቸው አይገባም የሚል ነጥብ አቅርቧል። በተጨማሪም አቃቢ ህጉ ተጠርጣሪዎቹ አጠፉ የተባሉት ሀብት እንዲሁም ድርጅቶቹ በክልሉ የሚገኝ በመሆኑ ጉዳያቸው በክልሉ ፍርድ ቤቶች ሊታይ ይገባል ብለዋል።ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ሀሳብ ተመልክቶ ተጠርጣሪዎች ቀድሞ የነበራቸው ስልጣን የታወቀ በመሆኑ በማረሚያ ቤት በሚቆዩበት ጊዜ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው በማረፊያ ቤት የነበራቸው ቆይታም ተጠናቆ ወደ ክልሉ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ አዟል።ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያችን መታየት ያለበት በፌደራል ደረጃ ነው በሚል ያቀረቡትን ጥያቄ ችሎቱ ካዳመጠ በኋላ የተጠረጠሩበት ጉዳይ በክልሉ ውስጥ በሚገኝ ሀብት ዙሪያ የተመሰረተ በመሆኑ ጉዳያቸው በዚያው እንደሚታይ ተመልክቷል።የባህዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ ያቀረበውን የ ቀናት የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ የካቲት ቀን አመተ ምህረት ጉዳዩ እንዲታይ ወስኗል።ሪፖርተር ራሄል ፍሬው ከባህርዳር
እነአቶ በረከት ስምኦን ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሶስት መቶ ስላሳ አንድ ኢትዮጵያና ኩባ በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተስማሙ። የኩባ ምክትል ፕሬዘዳንት ሳልቫዶር አንቶኒዮ በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋርም በዛሬው እለት መክረዋል። ሁለቱ ባለስልጣናት በምክክራቸው የሁለቱን አገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮችን የበለጠ ለማጎልበት መስማማታቸውም ታውቋል። ውይይታቸውን የተከታተሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ለኢዜአ እንዳሉት ባለስልጣናቱ ሁለቱ አገራት በቀጣይ በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማሳደግ ተስማምተዋል። የኩባው ምክትል ፕሬዘዳንት ሳልቫዶር አንቶኒዮ በበኩላቸው ሁለቱ አገራት ከዚህ ቀደም በአለም አቀፍ መድረኮችና ጉዳዮች ላይ የነበራቸው ትብብር ጥሩ ውጤት ያመጣ መሆኑን አስታውሰዋል። በቀጣይም ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትስስር አጠናክራ እንደምትቀጥልም ተናግረዋል። ምንጭ፦ ኢዜአ ሶስት መቶ ስላሳ አንድ
ኢትዮጵያና ኩባ በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ
ህዝቡ ሳያውቀው ህገ መንግስቱ ተቀይሮ ይሆን መንግስት እኔ በሾምኳቸው የመስጊድ ኢማሞች አሰጋጆች አልሰገዳችሁም በሚል ንፁሀን ሙስሊም ግለሰቦች ላይ ክስ ያቀረበበት ሰነድ ተገኘ ከፍርድ ቤት የውስጥ ምንጮቻችን የተገኘውና በፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሀን አለባቸው ፊርማ በታህሳስ አራት ሁለት ሺህ ስድስት የተፃፈው ይኸው የክስ ሰነድ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ የቀረበ ሲሆን ሁለት መስጂድ ውስጥ በኢማምነት ያሰገዱ ሙስሊም ግለሰቦችንም ተከሳሽ አድርጎ አቅርቧል። ሰነዱ እጅግ አስገራሚውን ክስ ሲያብራራ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በቁባ መስጂድ የአህባሽ ተከታዩን ኢማም ተከትሎ ለመስገድ ፍቃደኛ ያልሆነውን ህዝበ ሙስሊም ማሰገዳቸውንና በዚህ ተግባራቸውም የሀይማኖት ሰላም ስሜት መንካታቸውን ገልጿል። ቃል በቃልም ሁለተኛ ተከሳሽ መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም ሳይፈቀድለት የእነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊው ሙስሊም እንዳይሰግድ በማድረግ ወንጀል መስራቱን ገልጿል። እስካሁን መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ አልጣስኩም እያለ ሲከራከር የቆየው መንግስት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጋለጥ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን መከራከሩ እንደማያዋጣው አውቆ በማን አለብኝነት እኔ የሾምኩትን ኢማም አልተከተላችሁም በሚል ፍርድ ቤት ችሎት ማሰየም መጀመሩ ህገ መንግስቱ አንድ ቀን ይከበር ይሆናል ለሚሉ ወገኖች ትልቅ መርዶ ይዞ መጥቷል። የአገሪቱ የፍትህ አካላት የሆኑት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች መንግስት የሾመውን ኢማም ተከትላችሁ አልሰገዳችሁም በሚል ኢ ህገ መንግስታዊ ክስ ላይ በይፋ መሰየማቸውም ለሀገሪቱ የፍትህ ስርአት የቁልቁለት አዘቅት መሆኑ አያጠራጥርም ህዝበ ሙስሊሙ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሰባት ጀምሮ በመንግስት ሹመኞች ቁጥጥር ስር የዋለውን መጅሊስ ተቀባይነት የነሳውና ለመሪ ተቋሙ መመለስም እስካሁን እየታገለ ያለው መጅሊሱ የመንግስት ካድሬዎች መጫወቻ በመሆኑ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በመጅሊሱ ስም የሚካሄዱት ሁሉም ተግባራት በመንግስት የሚሾፈሩ መሆናቸውም የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ቆይቷል። የዛሬውን ዜና ልዩ የሚያደርገው ግን መንግስት ሽብርተኝነት እና ሌሎች የማስመሰያ ስሞች ሳያስፈልጉት እኔ የመረጥኩልህን እምነት አልተከተልክም፤ እኔ በሾምኩልህ ኢማም አልሰገድክም ሲል በግልፅ በሰነድ ጭምር ምስክር ጠርቶ ችሎት ፊት ሰዎችን ማቆሙ ነው። ይህም ይፋ መውጣቱ መንግስት የደረሰበትን የሀይማኖታዊ አፈና ደረጃ ለመላው አለምና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት ይበልጥ ይፋ የሚያደርግ መሆኑ አያጠራጥርም። አዎን የመንግስት ሀይማኖታዊ ጭቆና በምንም መልኩ መደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህ ግን ከሁለት አመታት በላይ ኢ ፍትሀዊነትን ሲታገል የቆየው ህዝበ ሙስሊም የበለጠ በትግሉ ላይ እንዲጠናከር የሚያደርገው እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጠው አይደለም፤ ህዝብ ተስፋ አይቆርጥም ህዝበ ሙስሊሙ የሀይማኖት ነፃነቱ እስኪከበርና የዜግነት መብቱን የሚጋፉ አሰራሮች እስኪቀረፉ ድረስ በፅናት መታገሉን ይቀጥላል፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና ድምፃችን ይሰማ አላሁ አክበር
የመስጊድ ኢማሞች የሚሾሙት በመንግስት በራሱ መሆኑን መንግስት አመነ
ሁለት መቶ ሀያ ሎስ አንጀለስ እንደሚታወቀው በዘጠኝ አራት ሁለት ሺህ በሎስ አንጀለስ ከተማ የሊትል ኢትዮጵያን አመታዊ በአል ለማክበር ዝግጅት ሲደረግ ከርሞ ነበር። በዚህ በአል ላይ ወያኔ ድንኳን ሊከራይ አይችልም በሚል አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና የበአሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሲከራከሩ ነበር የሰነበቱት ሆኖም ግን እስካሁን በሚሰራበት ህግ ማንንም መከልከል አይቻልም ፤ ሁላችሁም ተሳተፉ፤ ተቃውሟችሁንም በሰላማዊ መንገድ እስከሆነ ድረስ የማቅረብ መብታችሁ የተጠበቀ ነው በሚል ስምምነት ተደርጎ እኛም በቂ ዝግጅት አድርገን ትናንትና በቦታው ተገኘን። በነገራችን ላይ፤ የበአሉን አዘጋጅ ኮሚቴ በስራ በማገዝም ትብብር አድርገናል የድንኳን ምደባው በእጣ ነበር። እጣው ያለምንም አድሎና ግልፅና ለቁጥጥር አመች በሆነ መንገድ ነበር የተዝጋጀው። የድንኳኑ አመዳደብ ጎደሎ ቁጥር በአንድ በኩል፤ ሙሉ ቁጥር በሌላ በኩል እንዲሆን ተደርጎ ነበር የታሰበው፤ በዚህ መሰረት እጣው ሲመዘዝ ለኛ የደረስን ስድስት ቁጥር ሲሆን ለወያኔ የደረሰው ስምንት ቁጥር ነበር። ስለዚ የእኛና የወያኔ ድንኳን ምሰሶው በአንድላይ የታሰር ነበር። ይህ አጋጣሚ ብዙውን ህዝብ፤ ፍረንጆችን ሁሉ ሳይቀር ያስደነቅ ነበር። እኛን ደግሞ እጅግ ያሰደሰተ አጋጣሚ ነበር። አምባሳደር ተብየው ዘሪሁን ረታ አበደ፤ ስማይ ሊነካ ደረሰ፤ የአዘጋጅ ኮሚቴው እኛን እንዲያስነሳለት ጠየቀ አልሆነም፤ ፖሊስ ጠራ፤ አልሆነም። ያለው አማራጭ የሚደርስበትን የውግዘት ናዳ ተቀብሎ መቀመጥ አለበለዚያ ጥሎ መሄድ ነበር። እኛ ድንኳናችን ወያኔ ከዚህ በፊት በገደላችው ስዎች ምስልና አሁን በርሀብ ምክንያት አፅማቸው ገጦ በወጣ ህፃናት ሸበብነው። በአሁኑ ሰአት ያለውን ርሀብ የሚያጋልጥ የቪዲዮ ክሊፕ በፕላዝማ ስክሪን ደቅነን ነበር። በርካታ ስለርሀቡ ምክንያት የሚግልፁ ፅሁፎች ነበሩን። ልዩ ልዩ ወያኔንና ስርአቱን የሚያጋልጡ መፈክሮች ተዝጋጅተው በአርበኞች እጅ ተይዘው ነበር። የዚህ ግሩፕ ሎጎ በአዋቂዎች ተሰርቶ በድንኳኑ ውስጥ ተገትሮ ነበር። ምድረ ጨሰች፤ ወያኔ ጥጥ አጥቶ እንጅ ጀሮውን በጥጥ መድፈን ይፈልግ ነበር። እኛ ቀደም ብለን ደህንነታችን እንዲጠበቅልን ለፖሊስ አመልክተን ስለነበር አንድ ፖሊስ የኛን ድህንነት እንዲጠብቀ ተመድቦ አይዟችሁ እያለ በአካባቢው ያንዣብብ ነበር። እኛም ጨዋነት በሞላው አንድበት ወያኔን ልክ ልኩን መንገራችን ቀጠልን። በወያኔ ድንኳን አካባቢ አንድም ስወ ተውር ማለት አልቻለም። አንዳንድ ፈረንጆች ሂደው አነጋግረው ወደኛ ዘወር ሲሉ ፊታቸው በሀዝን ይዋጣል ምክንያቱም ወያኔ የሚያሳያቸው የትዋበ ህንፃ፤ የአባይ ፏፏቴና የቱሪስት ቦታዎችን ሲሆን እኛ ደግሞ አሁን በተጨባች ኢትዮጵያ ወስጥ ምን እየሆነ እንድሆን ነበር። ተኩረት በሚስብ አቀራረብ አርበኞች እየተባበሩ ባደረጉት ቅስቀሳ የበአሉን ተሳታፊ አይን ስቧል። ወያኔ ከዉሀ የገባች አይጥ መስሎ ሲንቆራጠጥ ነበር የዋለው። ቦንድም አልተሸጠ፤ ብሮሸርም አልታደለ። አራት ስዎች ብቻ ነበሩ አምባሳደር ተብዬውን አጅበው የዋሉ። ከአጃቢዎች ውስጥ ሁለቱ ከዚህ በፊት ከነበሩበት ድርጅት ወንጅል ሰርተው የሄዱ ናቸው። መቸም ወያኔ ውንጀለኛና የወንጀለኛ ዋሻ ነው፤ እውነተኛ ቦታቸውን አግኝተዋል። በመጨረሻም ወያኔ ድንኳኑን ዘግቶ ለመሄድ ወሰነ። እቃውን ጠቅልሎ ሲወጣ ጉዳት እንዳይደርስበት ስለሰጋ በአካባቢው ያሉ ፖሊሶችን ጠርቶ ተጠብቆ ወጣ። እኛም መፈክራችን እያቀለጥን፤ ወያኔና ውሻ ወደ ቤት እያልን ሽኜናቸው። የማቻል ሆኖ ነው እንጅ ክቡር አምባሳደሩ በመትረየስ ቢያስጨርሱን በወደዱ ነበር ነገር ግን ሎስ አንጀለስ ስድስት ኪሎ ባለመሆኑ ተርፈናል። የተቃውሞው ተሳታፊዎች በሎስ አንጀለስ ኗሪ የሆኑና በሳንዲያጎ የሚገኙ የኦጋዴን ተወላጆች ኢትይዮጵያዊያዊያንና አሜሪካዊያን ለፍትህና ለዴሞክራሲ በሚል ጥላ ስር ነበር። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር የአቶ አንዱአለም አራጌ፣ የአቶ እስክንድር ነጋና የሌሎች ተከሳሾች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ ሽብርን የሚያወግዝ በህዝብ ላይ ሽብርን አይነዛም
እንደገና ድል፤ እንደገና ጉብዝና በሎስ አንጀለስ ኢትዮጵያዊያንና አሜሪካዊያን ለፍትህና ለዴሞክራሲ
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እ ኤ አ ማርች አንድ ቀን ሁለት ሺህ በአመታዊው የምክር ቤት ዱማ ስብሰባ ንግግር ሲያደርጉ፣ ቃላቶቻቸውን ለማፅናት የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማሳየት ንግግራቸውን በተደጋጋሚ ሲያቋርጡ ነበር። እስከ ዛሬ ድረስ ማንም አልሰማንም ነበር፣ አሁን ግን ልትሰሙን ግድ ይላችኋል፤ ያሉት ፑቲን፣ እስካሁን ሩሲያን ለማፈንና ለመቆጣጠር የተደረጉ ጥረቶች በሙሉ ፍሬ አልባ ሆነዋል። እውነቱን ለመቀበል ጊዜው አሁን ነው። ይህ ባዶ ማስፈራሪያ አይደለም፤ በማለት ለተቀናቃኝ ሀያላን አገሮች መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ፑቲን ይኼንን አለም ሲከታተለው የነበረውን ንግግራቸውን በጠንካራ ቃላት እንዲሞሉ ያደረጓቸው ዋነኛ ምክንያቶችም በግድግዳው ላይ በንግግራቸው መካከል ሲያሳዩዋቸው የነበሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ውስጥ ሲታዩ የነበሩት፣ ባለፈው የአውሮፓውያን አመት መጨረሻ ላይ ተሞክረው ውጤታማነታቸውን ያስመሰከሩት አሀጉር አቋራጭ ሚሳይሎችና የውሀ ውስጥ በራሪ ድሮኖች ነበሩ። ፕሬዚዳንቱ ንግግር እያደረጉ በመሀል ሲያሳዩዋቸው ከነበሩ በኮምዩውተር የተቀናበሩ ምስሎች በአንዱ ከሩሲያ የተወነጨፈው ሚሳይል አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጦ፣ የላቲን አሜሪካን ጥጋ ጥጎች ታክኮ ወደ ሰሜን አሜሪካ ክልል ሲገባ ያሳያል። የእርሳቸው ሚሳይል እጅግ ትኩረት ሊስብ የቻለው ግን ሊገታ የማይችል ነው መባሉ ነው። የሩሲያ አዲሱ ሳርማት አሀጉር አቋራጭ ሚሳይል በአለም የትኛውም ስፍራ የሚደርስ የኑክሌር አረር ማስወንጨፍ ይችላል ፑቲን እንደሚያሸንፉበት ግምት የተጣለበት ምርጫ የሁለት ሳምንታት እድሜ ሲቀረው፣ ባለፈው ሳምንት በዱማ ያደረጉት ንግግር ስድስት አይነት መሳሪያዎች ይፋ የሆኑበት ነበር። የመጀመርያው ርቀት የማይገድበው በኒክሌር የተደገፈ አሀጉር አቋራጭ ሚሳይል ነው። ይኼ መሳሪያ ይዞት የመጣው እምብዛም ለየት ያለ ነገር እንደሌለው ተነግሮለታል። በአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳዎቹ የአሜሪካ አየር ሀይል ዝቅ ብሎ የሚምዘገዘግ ሚሳይል ላይ ምርምር ሲያደርግ እንደነበር ያስታወሱም ነበሩ። ይህ መሳሪያ በተለይ ከምድርም ሆነ ከህዋ የሚተላለፉ ቅድመ ማስጠንቀቂያዊችም ሆኑ የሚሳይል ማስተጓጎያና መከላከያ መሳሪያዎች፣ ሊለዩትና ሊያስቆሙት እንደሚችሉ ተገልጿል። ነገር ግን ሩሲያ እንዴት ይኼንን ሚሳይል ወደ ተግባር ልታመጣው ትችላለች የሚለው ጥያቄ ግን ብዙዎችን እያወያየ ነው። ሆኖም ቭላድሚር ፑቲን፣ ይህ መሳሪያ በአለም ላይ የትኛውም አገር የለውም፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ሊኖራቸው ይችላል። ያኔ ደግሞ እኛ የተሻለ መሳሪያ ይኖረናል፤ ሲሉ ሚሳይሉን ቀድመው የሩሲያ ማድረግ መቻላቸውን አስረግጠዋል። ሙከራ ተደርጎ ውጤታማ መሆን እንደቻለም በሙከራ ጊዜ የተቀረፁ ምስል ተጠቅመው ለማረጋገጥ ሞክረዋል። ሁለተኛው ፑቲን ይፋ ያደረጉት የመሳሪያ አይነት አቫንጋርድ የተሰኘ ነው። ከሰማይ የተወረወረ የኮከብ ስባሪ ይመስል ኢላማውን ድባቅ ሊመታ የሚችልና እንደ ቀደመው ሚሳይል ሁሉ ከህዋም ሆነ ከምድር የሚደረጉ ክትትሎችን በቀላሉ ሊያልፍ የሚችል እንደሆነ ገልፀው፣ አቅጣጫውን በፍጥነት በመቀየር ኢላማው ዘንድ ለመድረስ የሚያደርገው ጉዞ ከእይታ የተሰወረ ነው ብለዋል። እንዲህ ያሉ መሳሪያዎች በአጭር ጊዜ ወይም ያለምንም ማስጠንቀቂያ በጠላት ንብረቶችና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ አደጋ ለመጣል ተወዳዳሪ የሌለው ይሆናልም ተብሏል። ሳርማት የተባለው አርኤስ ሀያ ስምንት ከባድ አሀጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳይል ሌላኛው ፑቲን በምስል ተደግፈው ይፋ ያደረጉት መሳሪያ ነው። እ ኤ አ ከሁለት ሺህ ስራው ተጀምሮ እ ኤ አ በሁለት ሺህ ሀያ አንድ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ የሚሳይል አይነት ነው። ካሁን በፊት ጥቅም ላይ ይውል የነበረው አገር ስላሳ ስምንት የተባሉትን ሚሳይል የሚተካ ሲሆን፣ የአሜሪካን የሚሳይል መለያ መሳሪያዎች ማለፍ የሚችል መሆኑ ተነግሮለታል። ይህ ሚሳይል የሚሸከማቸው የተለያዩ መሳሪያዎች ሲኖሩት፣ በተፈለገ ርቀት በኢላማውን ለመምታት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ገጥሞለታል። ፑቲን ይኼንን መሳሪያ በተመለከተ ሲያስረዱ የተጠቀሙበት በኮምፒዩተር የተቀነባበረ ቪዲዮ፣ ሚሳይሉ እነዚህን መሳሪያዎች የአሜሪካ ግዛት በሆነችው ፍሎሪዳ ላይ ሲጥል ያሳያል። ቶፖል አሀጉር አቋራጭ ሚሳይል ሩሲያ በቅርቡ ለእይታ ያቀረበችው ነው ሌላው ግርምትን የፈጠረውና ፑቲን ይፋ ያደረጉት መሳሪያ የውሀ ውስጥ ድሮን ሲሆን፣ ይህም ኑክሌር አቅም ያለው ነው። ይህ መሳሪያ ለረዥም ጊዜያት ሩሲያ እየሰራችው ነው እየተባለ ቢወራም፣ ከመንግስት የተሰጠ ምንም አይነት ማረጋገጫ ግን አልነበረም። አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ይህ የባህር ሰርጓጅ መሳሪያ የሚሳይል መከላከያዎችን ለማምለጥ እስከ ዛሬ ድረስ ከነበሩ የተለያዩ እርምጃዎች ለየት የለ እንደሆነ ተነግሮለታል። ስድስተኛውና የመጨረሻው የሚሳይል አይነት አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሀምሳ ማይል ርቀት መሄድ የሚችልና ከድምፅ ፍጥነት በአስር እጥፍ ሊጓዝ የሚችል ዘመናዊ መሳሪያ ነው ተብሏል። ምንም እንኳን ፑቲን እነዚህም መሳሪያዎች ቢያስተዋውቁም፣ ሩሲያ ረዥም ርቀት ላይ ያለን ኢላማ የመምታት ውስንነት ለማስተባበል የተጠቀሙበት ስትራቴጂ ነው በማለት ያጣጣሉት አልጠፉም። ፑቲን ይኼንን ይፋ እንዲያደርጉ ያደረጋቸውም አሜሪካ በረዥም ርቀት ሚሳይል ያላት የመሪነት ሚና አሳስቧቸው እንደሆነም ያወሳሉ። ከፑቲን መሳሪያዎች ይፋ መሆን በኋላ የተለያዩ ሚዲያዎች የማይበገረው የሩሲያ ሚሳይል ይፋ ሆነ እያሉ ይፋ ሲያደርጉ፣ አሜሪካ ደግሞ ምንም ይሁን ምን ለሚመጣው ሁሉ ዝግጁ ነኝ ስትል በፔንታጎን ቃል አቀባዩዋ ዳና ዋይት አማካይነት አስታውቃለች። ለሚመጣው ሁሉ ዝግጁ ነን፤ ሲሉ ዋይት ተናግረዋል። ቃል አቀባዩዋ ይኼንን ይበሉ እንጂ አሜሪካ የሚሳይል መከላከል አቅሟ እጅግ ደካማ እንደሆነ፣ ይህም ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ አሜሪካ አብራው የኖረችው እውነታ እንደሆነ የሚናገሩ ተቺዎች አሉ። ስለዚህም እንኳን የተባሉት የሚሳይል አቅሞች ተጨምረው ይቅርና አሁን ባላት የሚሳይል አቅም ሩሲያ ከአሜሪካ በእጅጉ የላቀ የሚሳይል አቅም እንዳላት የሚናገሩ ብዙ ናቸው። ቭላድሚር ፑቲን ዋነኛ ከሚባሉት ጄኔራሎቻቸው ጋር
አለምን ያስደመሙት የቭላድሚር ፑቲን አዳዲሶቹ የኑክሌር መሳሪያዎች
ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ የሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት በዘ ሀበሻ አንባቢዎች የአማቱ ምርጥ የሴት ጋዜጠኛ በሚል የተመረጠችውና በእስር ቤት እየማቀቀች የምትገኘው ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ከትላንት ጀምሮ ከእናት ከአባት እና ከነፍስ አባት ውጪ እንዳትጠየቅ በመከልከሏ የረሀብ አድማ ላይ መሆኑና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሀይሉ በፌስቡክ ገፁ ባሰራጨው መረጃ ገለፀ። በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ከተመሰረተባቸው ውስጥ አንዷ የሆኑት ኮሎኔል ሀይማኖት በተመሳሳይ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው እና የጉምሩክ አመራር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ባለቤት ፤ ርእዮት ያለችበት ክፍል እንዳሉና፤ ከኮሎኔል ሀይማኖት በተደጋጋሚ ዛቻ ፣ ስድብ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባት እንደሆነ በዛሬው እለት ሊጠይቋት ለተፈቀደላቸው ለእናቷ ገልፃለች። እንዲሁም ከማረሚያ ቤቱ የሴት ፖሊሶችና እና ደህንነቶችም ተመሳሳይ ማስፈራሪያ፣ ስድብ እና ዛቻ እየበረታባት እንደሆነ ተናግራለች። ዛሬ ለበአል ሊጠይቋት ከሄዱ ቤተሰቦቿ እና ጓደኞቿ መሀል እናቷ ብቻ እንዲያዩአት የተፈቀደላቸው ሲሆን፤ እየደረሰባት ያለውን የሰብአዊ ጥሰትም በመቃወም ከትላንት ጀምሮ የምግብ አድማ ላይ መሆኗን በመግለጿ፤ ይዘውላት የሄዱትን ምግብ መልሰውታል ያለው ጋዜጠኛው በዚህ ስሜት ውስጥ ያሉትን የርእዮት ቤተሰቦች ለማፅናናትም የሚከብድ ነገር ነው። ሲል ስሜቱን ገልጿል።
ርእዮት አለሙ በ እስር ቤት የረሀብ አድማ ጀመረች፤ በሙስና የታሰሩት ኮሎኔል ሀይማኖት እያስፈራሯት መሆኑን ተናገረች
በየሁለት አመቱ ብቅ የሚለው የአፍሪካ የተወዳዳሪነት ሪፖርት፣ በአለም የኢኮኖሚ ፎረም በኩል እየተዘጋጀ የሚወጣ ነው። በዚህ አመት ለንባብ የበቃው ሪፖርት የአፍሪካን ተወዳደሪነትና ፈታኝ ገፅታዎችን ዘክሯል። የአለም ባንክ በየአመቱ ከሚያወጣቸው ሪፖርቶች መካከልም ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ይፋ የተደረገውና የአገሪቱን የተወዳዳሪነት፣ የመዋቅራዊ ለውጥና መሰል ጉዳዮች የቃኘው ሪፖርትም ይጠቀሳል። በአፍሪካ አገሮች ዘንድ እየታየ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ከአለም ንፍቀ ክበብ የሚገዳደሩት የእስያና የላቲን አገሮች ናቸው። በተቀረው ግን ላለፉት አመታት አፍሪካ ሳታቋርጥ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገቧን ቀጥላለች። ሁሉም ፈጣን እድገት ማስመዝገብ ብቻም ሳይሆን ያደጉ አገሮች በበርካታ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በሚናጡበትና አመታዊ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ባልቻሉበት በዚህ ዘመን እንኳ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገሮች የአለምን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ይዘውራሉ። በአለም የኢኮኖሚ ፎረም ሪፖርት መሰረት ባለፉት አርባ አመታት የአፍሪካን ኢኮኖሚ ዘርፎች ተቆጣጥሮ የነበረው ግብርናም የበላይነት ይዞታውን እያስረከበ ይገኛል። እጅ ሰጥቷል። በአርባ አመታት ውስጥ የግብርና ኢኮኖሚያዊ ድርሻ በአማካይ ከስላሳ ከመቶ ወደ ከመቶ ቀንሷል። ሆኖም የግብርናው ወደኋላ መሸሽ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት አላስቻለም። ኢንዱስትሪና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች በአፍሪካ እንግዳ ናቸው። ከዚህ ይልቅ የአገልግሎት ዘርፍ ከአራት አሰርት በፊት ስላሳ አምስት ከመቶ የነበረው ድርሻ አሁን ላይ ሀምሳ አምስት ከመቶ ደርሷል። የግብርናውን የበላይነት የተቆጣጠረው ይኸው ዘርፍ ሆኖ ይገኛል። በአለም የኢኮኖሚ ፎረም ዘንድሮ ይፋ የተደረገው ሪፖርት አብዛኛው ይዘቱ ከዚህ ቀደም የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ በየአመቱ ከሚያወጣቸው የጥናት ውጤቶች ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። በአፍሪካ ደረጃ እየታየ ያለው እድገት ልክ ኢትዮጵያ ላይ እንደሚሰነዘሩት አይነት መዋቅራዊ ለውጥ ከማምጣት ይልቅ፣ የአገልግሎት ዘርፍ ላይ የተመረኮዙ ሆነው ተገኝተዋል። መዋቅራዊ ለውጥ ማለት በሪፖርቱ ማብራሪያ መሰረት፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችንና ወይም የምርት ሀይሎችን ምርታማነታቸው ዝቅተኛ ከሆኑ ዘርፎች ይበልጥ ምርታማና ውጤታማ ወደሆኑ ኢኮኖሚ ክፍሎች ማሸጋገር መቻል ሲሆን፣ በአፍሪካ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ለውጥ አልመጣም። ይብሱን ከሰሀራ በታች በሚገኙ አገሮች ውስጥ የኢኮኖሚ ሀይሎች ከሆኑት መካከል የሰው ሀይል ከግማሽ በላይ ተሰማርቶ የሚገኘው በግብርና ሲሆን፣ ከዚህ ዘርፍ እየተሰደደ በብዛት ወደ አገልግሎት ዘርፍ የሚገባው ማለትም ወደ ንግድና ወደ ሌሎች ንኡስ ዘርፎች እየገባ ያለው የሰው ሀይል ቁጥር ወደ አምራች ኢንዱስትሪው ከሚገባው በከፍተኛ መጠን በልጦ ይታያል። በአፍሪካ እያደገ መሆኑ የሚነገርለት መካከለኛ ገቢ ያለው የህዝብ ቁጥር የአሀጉሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ወደ ላይ ከሚመነድጉት ዋናው ምክንያት መሆኑን ከጥቂት ወራት በፊት በተባበሩት መንግስታት ይፋ የተደረገው የአለም ኢኮኖሚ ሁኔታ ማሳያ ሪፖርት ይጠቀሳል። ከዚህም ባሻገር የንግድ እንቅስቃሴ መሻሻሎችና ቢዝነስ ለማካሄድ እንቅፋት የነበሩ እንቅፋቶች መሻሻል የአፍሪካ አማካይ እድገት በአምስት ከመቶ እያደገ እንዲቀጥል ለማስቻል አግዘዋል ተብለዋል። በአፍሪካ በፍጥነት ከሚያድገው ኢኮኖሚ ጎን ለጎን የአሀጉሪቱ የህዝብ ቁጥር እድገትም አብሮ ይነሳል። ኢኮኖሚያዊ እድገቱ ለህዝቡ ኑሮ መሻሻል የሚያበረክተው አቻዊ አስተዋፅኦ ጥያቄ አጭሯል። ሪፖርቱም ይህንን መከራከሪያ ያቀርባል። የአለም ባንክ በበኩሉ በቅርቡ ይፋ ያደረገውና ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ያተኮረው አመታዊ ሪፖርት እንደሚያትተው ኢትዮጵያ ከግብርና ዘርፍ ይልቅ በአምራች ኢንዱስትሪ የሚመራ፣ ኢንዱስትሪ ተኮር ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገውን እንቅስቃሴና የመንግስትን የአምስት አመት የልማት እቅድ ቃኝቷል። በዚህ መሰረት ቅኝቱ እንደሚያመለክተው አገሪቱ አሁንም በግብርና ዘርፍ የበላይነትም የምትመራ መሆኗን ሲሆን፣ ሶስት አራተኛውን የሰው ሀይል የሚቀጥረውም ይኼው የግብርናው መስክ ነው። በመሆኑም የአገሪቱ መዋቅራዊ ለውጥ ደካማ ከመሆን በላይ ገና ምልክቱ እየታየ የሚገኝበት ምእራፍ ላይ ይገኛል። በመሆኑም ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሰው ሀይል ለማጉረፍ ያልተሳካላት አገር ተብላ ተፈርጃለች። ግብርና ሰባ ስምንት ከመቶ የሚሆነውን ህዝብ አሰማርቶ እንደሚገኝ የአለም ባንክ ይፋ አድርጓል። ማእድን ዘርፍ ነጥብ አምስት ከመቶ፣ አምራች ኢንዱስትሪ አስምት ከመቶ፣ ኮንስትራክሽን ሁለት ከመቶ፣ ንግድ ሰባት ከመቶ፣ ትራንስፖርት ነጥብ ዘጠኝ ከመቶ፣ ፋይናንስ ነጥብ ሶስት ከመቶ፣ የህዝብ አገልግሎት ሶስት ከመቶ እያለ በንኡስ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ውስጥ የተሰማራውን የሰው ሀይል ቁጥር ባንኩ አስፍሯል። የኮንስትራክሽን ዘርፉ በፍጥነትና በከፍተኛ መጠን በማደግ ትልቁን ድርሻ ቢይዝም በሰው ሀይል ረገድ የያዘው ድርሻ ያን ያህል ሆኖ ይታያል። በአንፃሩ መንግስት በጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች አማካይነት ሚሊዮኖች የስራ እድል እንዲያገኙ እያደረገ እንደሚገኝ፣ የራሳቸውን ገቢ ከመፈጠር ባሻገር መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን እንዲፈጥሩ ጭምር እየረዳ እንደሆነም ደጋግሞ ሲገለፅ ይደመጣል። የአለም ባንክ በበኩሉ መንግስት በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍም ሆነ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ አሰልጥኖ ለአምራች ኢንዱስትሪው ግብአት እንዲሆኑ የሚያወጣቸው ዜጎች አብዛኞቹ የስራ እድል እያገኙ አለመሆኑን በሪፖርቱ ማቅረቡም አይዘነጋም። የምርታማነት ውጤት ከሚወስኑ ተግባር መካከል አንዱ የሆነው ውጤታማ የሰለጠ የሰው ሀይል ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በተለይ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ተቋሞቿ ውስጥ ከሌሎች አቻ አገሮች ጋር ተነፃፅራ የተገኘው ውጤት የተሻለ ከሆነባቸው መስኮች መካከል አንዱ ለጉልበት የሚከፈል ዝቅተኛ ወጪ ነው። በዚህ መሰረት እንደ ዛምቢያና ቬትናም ከመሳሰሉ አገሮች ጋር ሲነፃፀር ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ አንድ ድርጅት ከአንድ ሰራተኛ በአማካይ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዶላር ግምት ያላቸውን ምርቶችን ያመርታል። በአንፃሩ ከቻይናና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ስንነፃፀር ግን ኢትዮጵያ ያላት የሰው ሀይል ምርታማነት ዝቅተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። ለምሳሌ አንድ የእንጨት ወንበር ኢትዮጵያ ውስጥ ለማምረት ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ዶላር ያስወጣል። በአንፃሩ በቻይና አንድ መቶ ዶላር፣ በቬትናም ስምንት መቶ ሰማኒያ ስምንት ዶላር እንዲሁም በታንዛንያ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ አራት ዶላር ያስወጣል። በአንፃሩ ፖሎ ቲሸርቶችን ለማምረት በኢትዮጵያ ሀምሳ ዶላር ሲያስወጣ፣ በቻይና አንድ መቶ፣ በቬትናም አንድ መቶ አንድ፣ በታንዛንያ አንድ መቶ ሁለት ዶላር ወጪ ያስከትላል። ከዚህም በተጨማሪ የቆዳ ውጤቶችን ለማምረት በኢትዮጵያ የሚጠይቀው የሰራተኛ ወጪም ከሌሎቹ አገሮች አኳያ ሲነፃፀር ዝቅተኛ ሆኖ ይታያል። በኢትዮጵያ ዶላር የሚጠይቀው የቆዳ ውጤቶች መስክ በቻይና አንድ መቶ ዶላር፣ በቬትናም ሀያ ዘጠኝ ዶላር እንዲሁም በታንዛንያ ስላሳ ሰባት ዶላር ይጠይቃል። ይህም ሆኖ በአገሪቱ የሚታየው የምርታማነትና የክህሎት ችግር የአገሪቱን አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚፈታተን ክስተት እንደሆነ የአለም ባንክ አካቷል። ከዚህም ባሻገር ድርጅቶችና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የቴክኒክ እውቀት ያላቸውን ሙያተኞች ለመቅጠር የሚያስችል ተግባቦት የሌላቸው መሆኑን ያመለከተው ባንኩ፣ ጥናት ካደረገባቸው ስልሳ ድርጅቶች ውስጥ ብቻ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አስታውቀዋል። በመሆኑም ከቴክኒክና ሙያ ተመርቀው ከሚወጡት ውስጥ ስራ ማግኘት ያልቻሉትን በሚመለከት በዝርዝር አስቀምጧል። ለአብነትም ከስፌት ማሰልጠኛዎች ከሚመረቁት ውስጥ ስላሳ ስድስት ከመቶው ስራ የማያገኙ ናቸው። በኤሌክትሪክ ስራዎች ከሚመረቁት ስላሳ ስድስት፣ በኮምፒውተር አፕሊኬሽንሽና በአጠቃቀም አርባ ሁለት ከመቶ፣ በብረታ ብረት ቴክኖሎጂ አርባ ሶስት ከመቶ፣ በግምበኝነት አርባ ዘጠኝ ከመቶ፣ በእንጨት ስራ ወይም በአናጢነት ሀምሳ ሶስት ከመቶ፣ በሽመና ሀምሳ አራት ከመቶ፣ በጨርቃ ጨርቅ ምህንድስና ስልሳ ከመቶ እንዲሁም በቧንቧ ስራ ሰባ አንድ ከመቶ ስራ የማያገኙ ነግር ግን ከቴክኒክና ሙያ ተመርቀው የሚወጡ መሆናቸውን የአለም ባንክ ይፋ አድርጓል። በጠቅላላው በአገሪቱም ሆነ በአፍሪካ የሚታየው ከፍተኛ ኢኮኖሚ እድገት ተወዳዳሪነት ለማምጣት ብዙ ከሚቀረው መሆኑን ሁለቱም ሪፖርቶች ሲጠቁሙ፣ በአብዛኛው በግብርና ሸቀጦች ላይ የተመሰረተው የወጪ ንግዳቸው፣ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አምራች ኢንዱስትሪያቸው፣ በሰለጠነ የሰው ሀይል አለመኖርና በክህሎት ችግሮቻቸው ሳቢያ አፍሪካውያኑ የሚያስመዘግቡት ኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረታዊ ለውጥ በማምታት ህዝቦቻቸውን ተጠቃሚ ከማድረግና የኑሮ መሻሻሎችን ከማስዝገብ አኳያ የሚኖራቸው ሚና ጥያቄ ውስጥ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተወዳዳሪነትና በመዋቅራዊ ለውጥ ሲቃኝ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት ሀያ አራት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በማሊ በደረሰ ጥቃት የስድስት ሰወች ህይወት ማለፉ ተነገረ። በማሊ በሞንዶሮ ከተማ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ስድስት ወታደሮች ሲገደሉ አስር ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ። በአፀፋውም የሀገሪቱ ወታደራዊ ሀይል ባደረሰው የአየር ጥቃት በታጣቂዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስ ፤ የታጣዊቆቹ በርካታ ተሽከርካሪዎች መውደማቸው ነው የተገለፀው። ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገረው ታጣቂዎች በመስከረም ወር በወታደራዊ ካምፕ እና በቦልኪሴይ ባደረሱት ጥቃት አርባ ወታደሮች መገደላቸው የሚታወስ ነው ። በሀገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን አመፅ ለማስቆም የማሊው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ከጅሀዶች ጋር መደራደር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል ። ምንጭ ቢቢሲ
በማሊ በተፈፀመ ጥቃት ስድስት ወታደሮች ተገደሉ
በከፋለሰሞኑን የአለምንና የኢትጵያውያንን ሀሳብና አስተየት ለመለዎጥ ወይም ለማሳሳት ወያኔ በወኪሎቹ አማካይነት የተለመደዉን ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ ከርሞአል። አባይ እንደሚጠቅመን ሆኖ ቢገደብልን እጂግ ደስ ይለን ነበር። የወያኔ ትግሬዎች ሰለአባይ ከባለቤቱ ከኢትጵይያ ህዝብ በላይ የሚያቀነቅኑበት የሚጮሁበትና ሚያስመስሉበት ምክንያቱ ሌላ ነው። እነሱ ሀገር ወዳድ ሌሎች ኢትዮጵዉያን ሀገራቸዉ ብታድግና ብትጠቀም የሚጠሉ ሆነው አይደለም።የኢትዮጵያም ህዝብ ይህንን በደንብ ያዉቀዋል። ከእባብ እንቁላል እርግብ አልጠብቅም ብሎአቸዋ። ታዲያ ይሀ ሁሉ የአዞ እንባ ማፍሰስና የኢትዮጵያን ሀዝብ ጩሀት ለመቀማት የመሞከር ሚስጥሩ ምንድነው ወያኔ ኢትዮጵያን ለመጉዳትና ለረጂም ጊዜ እችግር ዉስጥ ለማስገባት ካስጠናቸዉ ትልልቅ ጉዳዮች ፕሮጀችቶች አንደኛዉና ዋናው የአባይ ግድብ ነው። ለዚህም ማስረጃ የሚከተሉትን ነጥቦች ተመልከቱሀ ግድቡ የሚሰራው በጥንቃቄ የመሀል ሀግሩን ህዝብ በተለይም አማራዉንና ኦሮሞዉን እንዳይጠቅም በጣም እርቆ በጠረፍ ላይ ነዉ። ይህም በተለይ አማራዉና ሌሎች በአካባቢው የሚኖሩ ህዝቦች በምንም አይነት ለእርሻ ለመስኖ ለመጠጥ ለኢንዱስትሪና ለኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳይጠቀሙ ታስቦ የተሰራ ነው።ለ ሁለተኛዉ የተንኮል አካል ይህ ጥቅም የማይሰጥ ነገር ግን ሆን ተብሎ በአካባቢዉ ግጭት እንዲነሳና በዚያ ጥቅም በሌለዉ ግድብ ክዚህ በፊት በሺራሮና በባድመ ላይ እንደተደረገዉ ሁሉ የኢትዮጵያዉያንን ደም በማፍሰስና እነሱ እየዘረፉ ለመኖር የዘረጉት ወጥመድ ነው። ግድቡ ከፍ ብሎ ከተሰራ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ወደ ምስራቅና ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተዘርግቶ ሌሎች የሀገሪቱ አካሎች ይጠቀሙ ነበር ። ነገር ግን ያ ባለመፈለጉ የግድቡ ስራ ኤሌክትሪክ ለሱዳንና ለግብፅ ማመንጨትና መሽጥ ብቻ ሲሆን የተመረጠዉም ቦታ እድንበር አካባቢ ነው። ይህም በመሆኑ ድንገት ግጭት ቢከሰት እድንበር ላይ በመሆኑ በግብፅም ሆነ በሱዳን በቀላሉ የሚመታና የሚመክን ነዉ። ልክ ወደ ትግሬ የባቡር ሀዲዱ ሲዘረጋ አማራዉንና ኦሮሞዉን አግልሎ ወይም ሳይነካ ከአዋሽ ተነስቶ ዳር ዳሩን እየዞረ በአፋር በረሀ እንደ ደጋን ጎብጦ ከተጓዘ በኋላ ወደ ቀኝ በመታጠፍ የትግሬ ከተሞችን አዳርሶ እንደቆመው የባቡር መንገድ አይነት መሆኑ ነው።ሀ ሶስተኛዉ ትልቁ የሴራው አካል በአባይ ግድብ ስም እጂግ ግዙፍ የሆነ የኢትዮጵያ ሀዝብ ገንዘብ በህጋዊ መልክ መዝርፍና ማደህየት ነው። በዚህ ግዙፍ የዝርፊያ ስልት በኑሮ ውድነት ላይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች አርሶ አደሮች ነጋዴዎችና ሌሎች የህበረተሰብ ክፍሎች ካፋቸዉ እየተነጠቁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማይጠቅምና በራሳቸዉ ላይ ችግር ለሚፈጥር ሰራ እየተበዘበዙ እየገበሩ ነው። በሌላ በኩል በጣም የሚያሳዝነዉ ወያኔዎች የዘርፉትና በግልፅ አለም ካወቀዉ ገንዘብ ዉስጥ ቢሊዮን በመለስ ሰም የተቀመጠ ሲሆን ቢሊዮኑ ደግሞ ከኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተዘርፎ የሽሸ ነው። ይህ ማለት ወያኔወች የዘርፉት ገንዘብ ብዛት አራት የአባይ ግድቦችን ሊያሰራ የሚችል በመሆኑ ኢትዮጵያ በመድማት ላይ መሆኗን የዉጭ ሚዲያዎ በግልፅ ፅፈዋል።መ ሌላዉ አስገራሚ ሚስጥር አልጃዚራ ላይ ከግብፅ ከኢትዮጵያና ከእንግሊዝ አገር ተጋብዘው በተደርገው ዉይይት ላይ ግብፃዊቷ እዲህ ብላለች ግድቡ ሀገራዊ ናሽናል ሳይሆን ክፍለ አሁጉራዊ ሪጂናል መሆኑን ሟቹ መለስ ዜናዊ ተስማምቶበታል በማለት የዎያኔዉ መሪ ክህደት መፈፀሙን አጋልጣለች ይህንን ታሪካዊቪዲዮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማየት አለበት። ይህም ማለት የግደቡ ባለቤቶች ሱዳን ግብፅና ሌሎች በአካባቢዉ የሚገኙ ሀገሮች ጭምር ናቸዉ ማለት ነው።ከዚህም አልፎ ተርፎ ዜጎች መሰዋእትን ከፍለዉ ባቆዩዋት ሀገር ዉስጥ መብታቸዉን በመጠየቃቸዉ ብቻ በፀራራ ፀሀይና በድብቅ ሲገደሉ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ወገኖቻችንን ከሚኖሩበርት ቦታ በግፍ እያፈናቀሉ የነፃነት ታጋዮችን እያሳደዱ እየደበደቡ እያሰሩና እያሰቃዩ ለህዝቡ ጠላት ከመግዛት በስተቀር ለእድገት ለማይጠቅም ግድብና በአባይ ስም ለኢትዮጵያ አሳቢ መስሎ ለመታየት እየሞከሩ ነው። ፕሮጀክቱ ሲነደፍ በጥላቻና ግዙፍ ገንዘብ ለመዝረፊያ በመሆኑ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዉያንንና በአባይ ተፋሰስ አካባቢ ኗሪ የሆነውን ሰፊ ህዝብ አላማከሩም። ህዝቡም ሀሳቡን ተጠይቆ አልተሳተፈበትም።የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ወያኔ ለአንተ በታሪክ ዉሰጥ ጥሩ አስቦም ሆነ ሰርቶ ስለማያዉቅ በምትወደዉ ወንዝህ በአባይ ሽፋን የተጋረጠብህን ተንኮል በጣጥሰህ ወያኔን በማስወገድ በሚጠቅምህ መልኩ አባይንና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችህን ወደፊት ለመገንባት ስለምትችል አሁን ወያኔ በሚነዛው የዉሸትና ፕሮፓጋንዳ እንዳትረታ።ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
አባይና የመለስ ዜናዊ ወያኔ ታላቁ ሴራ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በአልጀርሰ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት በኢትዮጵያ ቡና ላኪ ድርጅቶችና በአልጄሪያ ቡና አስመጪ ድርጅቶች መካከል በበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ በአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ኤምባሲው በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለይ የንግድ ልውውጥና ኢንቨስትመንት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። የዛሬው ውይይትም ኤምባሲው ጥር አስር ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ካካሄደው አጠቃላይ የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች ማስታወቂያ መድረክ ቀጣይ ምእራፍ መሆኑ ተገልጿል። ቀደም ሲል በተካሄደው የወጪ ምርት ማስተዋወቂያ መድረክ ላይም በተለይ ከኢትዮጵያ ቡና ለማስመጣት ፍላጎት ያላቸውን በመለየት ለቀጣይ ግብይት የሚያመች የመረጃ ልውውጥ ማካሄጃ መድረክ መሆኑን ከአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
በኢትዮጵያ ቡና ላኪ ኩባንያዎችና በአልጄሪያ ቡና አስመጪ ድርጅቶች መካከል የንግድ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት ሀያ አራት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ማንቼስተር ዩናይትድ የናይጀሪያዊውን አጥቂ ኦዲዮን ኢጋሎን ኮንትራት ለተጨማሪ ወራት ማራዘሙን አስታወቀ።ክለቡ አጥቂውን እስከ መጭው ጥር ወር ድረስ ለማቆየት መስማማቱን ነው ያስታወቀው።የናይጀሪያዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ቆይታ ትናንት አብቅቶ ነበር።የክለቡ አሰልጣኝ ኦሊጉናር ሶልሻዬር የቻይናው ክለብ ለተጫዋቹ ለፈጠረለት ተጨማሪ እድል ምስጋና አቅርበዋል።ባለፈው ጥር ወር ማንቼስተርን የተቀላቀለው ኢጋሎ በስምንት ጨዋታዎች አራት ጎል ማስቆጠር ችሏል።በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰኔ አስር ቀን ይጀመራል። ምንጭ፦ ቢቢሲ
ማንቼስተር ዩናይትድ የኦዲዮን ኢጋሎን ኮንትራት አራዘመ
አዲስ አበባ፣ ታሀሳስ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ለሁለት ቀን የሚቆይ የቱሪዝም ማስተዋወቂያ መርሀግብር በፓኪስታን ካራቺ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በኤክስፖ ላይ የኢትዮጵያን ፓቪሊዮን ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን ፥ በውስጡ የኢትዮጵያ የጎብኚ መዳረሻዎች፣ ዘርፈ ብዙ ባህል፣ ታሪክ እና ወደር የለሽ የቱሪዝም መስህቦች የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል። በኢትዮጵያ እና በፓኪስታን መካከል ያለውን ዘላቂ ትስስርም የሚያሳይ ነው መባሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በዛሬው እለት የፓኪስታን የፌደራል ትምህርት እና ሙያዊ ስልጠና ሚኒስትር ማዳድ አሊ ሲንዲ የኢትዮጵያን ፓቪሊዮን ጎብኝተዋል። ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ባህላዊ የቡና ስነ ስርአት የታደሙ ሲሆን፥ አስደናቂ የባህል ትርኢቶችን እንዲሁም በኢትዮጵያ ያሉ የቱሪዝም መስህቦችን በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ዶክተር የተሰሩ እና በመሰራት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በቪዲዮ ተመልክተዋል። ኢትዮጵያ ቱሪዝምን ለማሳደግ እና በዘርፋ ከፓኪስታን ጋር ትስስር ለመፍጠር እያደረገች ያለውን ጥረትም አድንቀዋል። በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር በበኩላቸው፥ በሀገራቱ መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለመፍጠር እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ኤምባሲው በከፍተኛ ተነሳሽነት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በፓኪስታን ተቀማጭነታቸውን ባደረጉ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ በፓኪስታን የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ በሀገሪቱ እና አለም አቀፍ የንግድ ማህበረሰብ እና የመገናኛ ብዙሀን ሙያተኞች የኢትዮጵያን ፓቪሊዮን እየጎበኙ ነው።
ኢትዮጵያ የቱሪዝም መስህቦቿን በፓኪስታን እያስተዋወቀች ነው
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ ሀያ አንድ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት እና የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድኖች በጋራ የኮሮና ቫይረስን በትንፋሽ መለየት የሚያስችል ማስክ መስራታቸውን አስታወቁ። እንደ አጥኚዎቹ ቫይረሱ የሚለየው በማስኩ ውስጥ በሚቀመጡ ቅንጣት መለያዎች አማካኝነት ነው ተብሏል። ተጠቃሚው ማስኩን አድርጎ ለዚሁ ተግባር አብሮ የተሰራውን ቁልፍ መጫን እንደሚጠበቅበትና ማስኩ ውስጥ አብሮ የተቀመጠው ውሀ እንዲወጣ ማድረግ እንዳለበትም ነው ተመራማሪዎቹ የገለፁት። ውጤቱን በ ዘጠና ደቂቃ ውስጥ መመልከት እንደሚቻልና የተጠቃሚውን ሚስጥር ለመጠበቅ ሲባል የሚታየው በማስኩ የውስጠኛው ክፍል መሆኑም ነው የተጠቆመው። አጥኚዎቹ ግኝታቸውን ከጥጥ፣ ፖሊስተር፣ ሱፍ እና ሀር በተሰሩ ማስኮች ላይ በማካተት የተሻለ ውጤት የሚያገኙበትን ስልት እየፈለጉ መሆናቸውንም ገልፀዋል። በፈረንጆቹ በሁለት ሺህ አስር አጋማሽ ተመሳሳይ የኢቦላንና የዚካ ቫይረሶችን መለየት የሚያስችል ሞዴል በማሳቹሴት ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት ኢንጅነሪንግ ፕሮፌሰር ጀምስ ኮሊንስ መሰራቱን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡ ድረ ገፅ፦ ፌስቡክ፡ ዩትዩብ፦ ቴሌግራም፦ ትዊተር፦ በመወዳጀት ይከታተሉን። ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
ተመራማሪዎች የኮቪድ ቫይረስን በ ዘጠና ደቂቃዎች የሚለይ ማስክ መስራታቸውን አስታወቁ
የዚህ እትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም ጊዜያት በኪነጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኢህአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተመንግስት ከተቆጣጠረበት እለት ግንቦት አመተ ምህረት ጀምሮ በድፍረት የስርአቱን አምባገነንነት ፋፋይነት በብሄራዊ ጥቅም ላይዝ ያለውን ቸልተኝነት ጠቅሶ ተችቷል። ይህንንም ተከትሎ በደረሰበት ከባድ ጫና እስርና ግርፋት ሀገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል። በስደት በሚኖርባት አሜሪካም ያለውን የተከፋፈለ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባብሮ ከመምራቱም በላይ በየጊዜው የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁና መሰል ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚዘጋጁ የተቃውሞ ሰልፎችን አስተባብሮ መርቷል። በዚህም በመላው አለም በሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከበሬታን አትርፏል። አክትቪስት ታማኝ በየነ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር ያደረገው ቃለመጠይቅ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ከሀገሬ የወጣሁበት ቀን በረዘመ ቁጥር ሀገሬ ላይ በጣም ክህደት የፈፀምኩ ያህል ይሰማኛል ታማኝ በየነ ቃለ ምልልስ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር
አድማስ ራድዮ ረቂቁን ያዘጋጁት ሁለቱ ሪፓብሊካን ሴናተሮች የአርካንሰሱ ቶም ክተን እና የጆርጂያው ዴቪድ ፐርዱ ናቸው። ሴናተሮቹ እንደሚሉት ከውጭ አገር በሚመጣው ሰው የተነሳ አሜሪካውያን ስራ እያጡ ነው ስለዚህ በህጋዊ መንገድ የሚመጣውን ስደተኛ ቁጥር በግማሽ መቀነስ አለብን ነው የሚሉት። ስለዚህም አንዱ መንገድ ዲቪን ማቆም ነው። ሴናተሮቹ ስለዚሁ ጉዳይ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር መነጋገራቸውንና ያረቀቁት ህግ በዚህ አመት ለሴኔቱ ይቀርባል ብለው እንደሚያምኑ ይፋ አድርገዋል። አንድ ረቂቅ ህግ ሆኖ እንዲወጣ በሁለቱም ምክር ቤቶች እና በፕሬዚዳንቱ መፅደቅ ይኖርበታል። ይህ ረቂቅ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አገር ቤት ላሉ ቤተሰቦቻቸው ግሪን ካርድ የሚያስገኙባቸውንም ዘዴዎች ለመቀነስ አስቧል።
ዲቪ ሎተሪን ለማገድ አዲስ የህግ ረቂቅ ተዘጋጀ
የውጭ ጠላቶቻችንና የውስጥ ገዢዎቻችን በአንድ ድምፅ የሚሰሩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ አይተናል። በጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ማተኮሩን እንተወው አስጠቅቶናል አሳፍሮናል አድክሞናል። በገፍ ለሚሰደደውና ለሚዋረደው ብዙ ሚሊየን ወጣት ትውልድ እንደምናስብ አምናለሁ። እምነት ጩሀት ፀሎት አስፈላጊ ቢሆኑም አንገት ቆራጭ ሽብርተኞችን አይከላከሉም። አፋኝ አግላይና ራሱን አገልጋይ የሆነ የመንግስት ስርአትን አይለውጡም። ሁለቱንም አብሮና ተባብሮ ለመለወጥ ይቻላል የሚል እምነት አለኝ ሙሉውን ለማንበብእዚህ ላይ ይጫኑ።
ከጩሀት ወደ ተግባር የሚነገድበት የስደት ማእበል ትውልድ ከየት መጣ
ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማን ከሀላፊነት እንዳነሷቸው ነግረዋቸዋል። በምትካቸው አዳነች አቢቤን እንደሚተኩም ከ ቀናት በፊት ለታከለ ገልፀውላቸዋል ብሏል አዲስ ስታንዳርድ በዘገባው። አዳነች የኦህዴድ ስራ አስፈፃሚ አባል እና የፌደራሉ ገቢዎች ሚንስትር ናቸው። ታከለ ለምን ከሀላፊነት እንደተነሱ አልታወቀም።በሌላ ዜና ኢህዴግን የማዋሀድ ሀሳብ የኦህዴድኦዴፓን ስራ አስፈፃሚ ለሁለት ከፍሎታል ብሏል ይኼው ዘገባ። ዛሬ የተሰበሰበው ማእከላዊ ኮሚቴው በዚሁ ጉዳይ ላይ ጭምር ይመክራል። በሱማሌ ክልል አዲስ ተቃዋሚ ፓርቲ ተመስርቷል። ስያሜው ቅንጅት ለዲሞክራሲና ለነፃነት ይሰኛል። በዋናነት ፓርቲው ለሱማሌ ህዝብ ነፃነትና ዲሞክራሲ ታገላል። በፓርቲው ማንኛውም የድርጅቱን አላማ የሚደግፍ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ እንደሚሳፍበት ቪኦኤ ዘግቧል። የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ ትናንት ባወጣው መግለጫ ኢህአዴግን ለማዋሀድ የሚደረገው ሽርጉድ ሀገርን ይበትናል ሲል አስጠንቅቋል። ግንባሩን ሊያዋህድ የሚችል አመለካከትና የተግባር አንድነት የለም። የቅርፅ ብቻ ሳይሆን በይዘቱና ፕሮግራሙ አዲስ ፓርቲ ለመመስረት መታሰቡንም ኮንኗል። ያን ማድረግ ኢህአዴግ በምርጫ የተሰጠውን ሀገር የመምራት ሀላፊነት ያሳጣል። ሰሞኑን በማእከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ እንደገና በተቀሰቀሰ ግጭት ህይወት ጠፍቷል። ግጭቱ ያገረሸው በደፈጫ ቁስቋምና ሮቢት በተባሉ ቦታዎች ነው። ትናንት በጠዳ ሰዎች ተገድለዋል በርካቶች ተፈናቅለዋል። በጎንደር ከተማ ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያነሳሱ ወረቀቶች ይበተናሉ። ግጭቱ ከቅማንት ጉዳይ ጋር የተያያዘ እንደሆነ እማኞች ለ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አቢይ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር በሩሲያ እንደሚወያዩ እቅድ ሰለመያዙ ፅህፈት ቤታቸው መረጃ የለኝም ማለቱን ሪፖርተር አስነብቧል። አቢይ ግን በአፍሪካሩሲያ የጋራ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በመጭው ረቡእ ወደ ሩሲያዋ ሶቺ ከተማ እንደሚያቀኑ ዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጠዋል። ከጉባኤው በተጓዳኝ ከአቢይ ጋር እንደሚወያዩ ቀድመው ያስታወቁት ሲሲ ነበሩ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲሱን የክፍያ ተመኑን ከታህሳስ ጀምሮ ይፋ ያደርጋል ብሏል የሸገር ዘገባ። ክለሳው ለ አመታት በተከታታይ የሚተገበረው የታሪፍ ማሻሻያ አካል ነው። የአሁኑ ጭማሪ በኤሌክትሪክ ተጠቃሚዎች ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል። ዝቅተኛ ሀይል ተጠቃሚ መኖሪያ ቤቶች ሀይል ከቆጠቡ የክፍያ ጫናውን መቀነስ ይችላሉ። በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ታጣቂዎች በንፁሀን ላይ የፈፀሙትን ጥቃት የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው ልኬያለሁ ብሏል ሰላም ሚንስቴር። የ ሰዎች ያህል ህይወት የጠፋበት ጥቃት ግን ከተፈፀመ ዛሬ ኛ ቀኑን ይዟል። ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቀን መስጫ ቀንን ባንድ ሳምንት ማራዘሙን ፋና ብሮድካስት ትናንት ዘግቧል። ለህዳር የተያዘው ህዝበ ውሳኔ ወደ ህዳር ተዛውሯል። የጊዜ ሽግሽጉ ምክንያት ለህዝበ ውሳኔው ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ በማስፈለጉ ነው ተብሏል።
ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማን ከሀላፊነት እንዳነሷቸው ነግረዋቸዋል ዋዜማ ሬዲዮ
ፓርቲው ዛሬና ነገ አዲሱን ፕሬዚዳንት ይመርጣልበደቡብ ክልል በጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ ከመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከሺ በላይ ነዋሪዎች መታሰራቸውን አንድነት ፓርቲ ተቃወመ። በቁጫ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰው የመብት ረገጣ እንዲቆም ለማሳሰብ ሰላማዊ ሰልፍ አደርጋለሁ ብሏል። ከትላንት በስቲያ ፓርቲው በፅቤቱ የቁጫ ህዝብ ጥያቄ የሚፈታው የዜጎች መብት ሲከበር ነው በሚል በሰጠው መግለጫ በቁጫ ወረዳ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ እየተባባሰ በመምጣቱ በፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሚመራ ቡድን ወደ ስፍራው በመላክ መረጃ ካሰባሰበ በኋላ በወረዳው ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት መርምሮ ውሳኔ ማስተላለፉን ጠቁሟል። በፓርቲው ብሄራዊ ኮሚቴ ፀሀፊ እና የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል በአቶ ትእግስቱ አወል የተመራው ቡድኑ በቁጫ ለአራት ቀናት ባደረገው የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ሰዎች በሰላም በር ፖሊስ ጣቢያ በአርባ ምንጭና በጨንቻ ወህኒ ቤቶች እንደታሰሩ ማረጋገጡ ተገልጿል። ህዳር ቀን አመተ ምህረት አቶ ዛራ ዛላ የተባሉ የሁለት ልጆች አባት ኮዶ ኮኖ በተባለ ቀበሌ ውስጥ በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ማለፉን የገለፁት የቡድኑ መሪ አባወራው በጥይት ሲመቱ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ የስጋት ሳንታ የገዢው ፓርቲ የወረዳው ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ አሸብር ደምሴ እና የወረዳው የፀጥታ ሀላፊ አቶ አያኖ መለና በስፍራው እንደነበሩ ከአይን እማኞች መረዳታቸውን ተናግረዋል።የወረዳው ህዝብ በአካባቢው ምንም አይነት ልማት ባለመካሄዱና በፖለቲካውና በኢኮኖሚው ዘርፍ እንዲሳተፍ እድል ባለማግኘቱ በቁጭት የማንነትና የመብት ጥያቄ ማንሳቱን የገለፁት አቶ ትእግስቱ ይሄን ተከትሎም የመብት ረገጣና የማፈናቀል ተግባር እየተባባሰ መጥቷል ብለዋል። የፓርቲው የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊና የደቡብ ቀጠና ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ በበኩላቸው የወረዳው ህዝብ ተወላጅ እንደመሆኔ የአካባቢውን ህዝብ እንግልትና የመብት ጥሰት ጠንቅቄ አውቀዋለሁ ካሉ በኋላ የመብት ጥሰቱ እንዲቆም የአካባቢው ሽማግሌዎች ጠቅላይ ሚኒስተርኒስትሩን ለማነጋገር አዲስ አበባ ድረስ መጥተው ሰሚ በማጣት መመለሳቸውን ተናግረዋል።በህዝቡ ላይ በሚደርስበት እንግልት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ መፍትሄ ለማፈላለግ እንቅስቃሴ ሳደርግ ከአካባቢው ባለስልጣናት ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶብኛል ብለዋልአቶ ዳንኤል። የመብቱ ጥሰቱ እንዲቆም መንግስት እርምጃ መውሰድ አለበት ያሉት አቶ ዳንኤል ይሄ ካልሆነ ግን ፓርቲያቸው በቁጫ ወረዳ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ማቀዱን ገልፀዋል። የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሀላፊና የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ስዩም መንገሻ በበኩላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት በክልል ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባም መባባሱን ጠቅሰው ዛሬና ነገ ፓርቲው ለጠራው ጠቅላላ ጉባኤ አዳራሽ ለማግኘት ብርቱ ፈተና እንደገጠማቸው ተናግረዋል።የልኡካኑ መሪ አቶ ትእግስቱ አወልን ጨምሮ ሰባት አባላት በአካባቢው ባለስልጣናት አፍራሽ ተልእኮ ይዛችሁ መጥታችሁ ስለሚሆን እንጠረጥራችኋለን ተብለው ከአራት ሰአታት በላይ መታሰራቸውን ገልፀዋል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ ልኡካን ባቀረቡት ሰፊ ሪፖርት ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ፓርቲው ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። በቁጫ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ረገጣ በአስቸኳይ እንዲቆም የደረሰውን ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት የሚያጣራ ገለልተኛ ወገን እንዲቋቋምና እንዲጣራ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲወስን ቁሳዊ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጐች የሞራል ካሳ እንዲከፈላቸው የቁጫ ወረዳ ተወላጅ በሆነው የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር ላይ እየደረሰ ያለው ማሳደድና ማዋከብ በአስቸኳይ እንዲቆም ሲል በአቋም መግለጫው የጠየቀው ፓርቲው ይህ ካልሆነ ግን ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት ተቃውሞውን እንደሚገልፅ አስታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓርቲው ዛሬና ነገ በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትን የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ሪፖርትን የሚያዳምጥ ሲሆን የውሳኔ ሀሳቦችንም እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። ፓርቲው በሁለቱ ቀናት ጉባኤ አዲሱን ፕሬዚዳንት እንዲሁም የምክር ቤትና የኦዲት ቁጥጥር ኮሚሽን አባላትን እንደሚመርጥ የተገለፀ ሲሆን የፓርቲውን ፕሮግራምና ደንብ የማሻሻያ ረቂቆች መርምሮም እንደሚያፀድቅ ታውቋል።
አንድነት ከሺ በላይ የቁጫ ነዋሪዎች መታሰራቸውን ተቃወመ
ባለፈው የውድድር ዘመን የከፍተኛ ሊጉን በቻምፒዮንነት አጠናቆ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ላደገው ፋሲል ከተማ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ትላናት ስምንት ላይ በላንድ ማርክ ሆቴል የእውቅና እና የሽልማት ስነ ስርአት ተደረጎለታል።የሽልማት መጠኑ እንደየስራ ድርሻቸው እና ባበረከቱት አስተዋፅኦ መጠን የተከፋፈለ ሲሆን አንድ መቶ ስላሳ ብር የተበረከተላቸው ዋና አሰልጣኙ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ከፍተናውን ሽልማት አግኝተዋል። ለረዳት አሰልጣኙ ዘጠና ፣ ለቡድን መሪ አንድ መቶ ፣ ለህክምና ባለሙያ ስልሳ ፣ ለተጨዋቾች በተጫወቱት ብዛት ተሰልቶ የመጀመሪያ ደረጃዎች አንድ መቶ ፣ ለሁለተኛ ደረጃ ዘጠና ፣ ለሶስተኛ ደረጃ ሰማኒያ አምስት ሽልማት ተበርክቶላችዋል። ይህን ሽልማት አጠቃላይ ወጪ የሸፈነውም የጎንደር ከተማ አስተዳደር እንደሆነ ተገልጧል።በሽልማት ስነ ስርአት ወቅት የፈረሰው ዳሽን ቢራ አምና ይገለገልበት የነበረውን ዘመናዊ የተጨዋቾች መመላለሻ አውቶብስ ለፋሲል ከተማ የለገሰ ሲሆን ወደፊትም ክለቡን በማንኛውም ረገድ ለመደገፍ አስፈላጊውን ነገር እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል። ፋሲል ከተማ በከፍተኛ ሊግ በነበረው ተሳትፎ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ ያደርግለት የነበረው የጎንደር ዮንቨርስቲም ቡድኑ በፕሪሚየር ሊግ በሚያደርገው ቆይታው እንደ ወትሮው ሁሉ ድጋፉ እንደማይለየው አስታውቋል ።በተያያዘ ዜና ለሁለት ሺህ ዘጠኝ የውድድር ዘመን የሚጫወትበት አዲስ ማሊያ ከውጭ እንዳስመጣ የታወቀ ሲሆን እና በአካባቢው በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት የፋሲል ከተማ የሜዳ ጨዋታዎች በተለዋጭ ሜዳዎች ሊደረግ እንደሚችል ቢገመትም ክለቡ ሁሉንም የሜዳው ጨዋታዎች በጎንደር ፋሲለደስ ስታድየም እንደሚያከናውን ለማወቅ ችለናል።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ሲጀመር ፋሲል ከተማ ከስምንት አመታት በኋላ የመጀመርያ የሆነውን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በመጪው እሁድ ዘጠኝ፡ ይርጋለም ስታድየም ላይ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደርጋል።
ፋሲል ከተማን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ላሳደጉ አባላት ሽልማት ተበረከተላቸው
በዳዊት መላኩ በጀርመን ፍራንክ ፈርት በዛሬው እለት ማለትም እኤአ ከጠዋቱ ሰእት ጀምሮ መነሻውን የዶቼ ባንክ ዋና ፅህፈት ቤት ከሚገኝበት አድርጎ መድረሻውን የወያኔው ቆንስላ ፅህፈት ቤት ያደረገ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሰልፉ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን የዶቼ ባንክ ቦርድ ለወያኔ መንግስት ሊሰጥ ያሰበውን የሶቨርንግ ቦንድ ሽያጭ እንዲያቆም የሚተይቁ የተለያዬ መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን ለበርካታ ነዋሪዎች ይህን በሚመለከት በራሪ ወረቀቶችን አድለዋል።ሰልፈኞች ያሰሟ ቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል ጀርመን የዜጎችን መፈናቀል አትደግፊየመሬት ወረራን እንቃወማለን ጀርመን ላንባገነን መንግስት የሚትሰጪውን ድጋፍ አቁሚየፖለቲካ እስረኞች ያፈቱ የሚል ይገኝበታል። በተጨማሪም ሰልፈኞቹ የነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን አስመልክቶ በፍራንክፈርት የእንግሊዝ ኢምባሲ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት የተለያዩ መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን እንግሊዝ ዜጋዋ የሚፈታበትን መንገድ አጠናክራ እንድትጠይቅ አሳስበዋል።በተወካያቸው በኩልም ደብዳቤ አስገብተዋል።በመጨረሻም ሰልፈኞቹ ጉዟቸውን ወደ ኢትዮጵያ ኢምባሲ በማምራት የፖሊተካ አስረኞች ይፈቱ ነፃነት እንፈልጋለንፍትህ ለፖለቲካ እሰረኞችፍትህ ለሞስሊም ተወካዮች ፍትህ ለጋዜጠኞችወያኔ ስልጣኑን ይልቀቅመንግስት ዜጎችን ማሸበሩን ያቁም ወዘተ የመሳሰሉ መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን ባለ አንባሸውን የወያኔ ሰንደቅ አላማ አውርደው በትክክለኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ለመተካት የተደረገው ጥረት በፖሊሶች ከፍተኛ ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
በጀርመን ፍራንክ ፈርት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
በአለም ላይ ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ጋዜጠኞች ታስረዋል በመገባደድ ላይ በሚገኘው የፈረንጆች ሁለት ሺህ ብቻ በመላው አለም ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ጋዜጠኞች መታሰራቸውንና ላለፉት አመታት ከአለማችን አገራት መካከል በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ቀዳሚነቱን ይዛ የዘለቀችው ቻይና፤ ዘንድሮም በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ተነግሯል።ተቀማጭነቱ በኒው ዮርክ የሆነው አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ ባለፈው ረቡእ ይፋ ባደረገው አመታዊ ሪፖርቱ እንዳለው፤ ባለፉት ወራት ጊዜ ውስጥ አርባ ስምንት ያህል ጋዜጠኞችን ያሰረችው ቻይና፣ ብዛት ያላቸው ጋዜጠኞች በማሰር ከአለማችን አገራት ቀዳሚነቱን ይዛለች።በአመቱ አርባ ሰባት ጋዜጠኞችን በማሰር በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ቱርክ መሆኗን የጠቆመው የሲፒጄ ሪፖርት፤ ያም ሆኖ ግን በአገሪቱ የታሰሩት ጋዜጠኞች ቁጥር አምና ከነበረው በስልሳ ስምንት መቀነሳቸውን አመልክቷል። ሳኡዲ አረቢያና ግብፅ እያንዳንዳቸው በተመሳሳይ ሀያ ስድስት ጋዜጠኞችን በማሰር በሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፣ ኤርትራ እንዲሁም ቬትናም ጋዜጠኞችን በማሰር የአራተኛና የአምስተኛ ደረጃን መያዛቸውንም ሪፖርቱ ይጠቁማል። በአመቱ በመላው አለም ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞች ቁጥር አምና ከነበረው ሁለት መቶ ሀምሳ አምስት፣ በአምስት ብቻ የቀነሰ ሲሆን በመላው አለም ለእስር ከተዳረጉት ሁለት መቶ ሀምሳ ጋዜጠኞች መካከል ሀያዎቹ ሴቶች መሆናቸውንና የሴት ጋዜጠኞች ድርሻ ከአምናው በ በመቶ መቀነሱን ሪፖርቱ አስረድቷል።በአለማቀፍ ደረጃ ሀሰተኛ ዜናዎችን አሰራጭተዋል በሚል በመንግስታት ለእስር የሚዳረጉ ጋዜጠኞች ቁጥር ባለፉት አራት ተከታታይ አመታት እያደገ መምጣቱን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ በአመቱ በዚህ ሰበብ ስላሳ ጋዜጠኞች ለእስር መዳረጋቸውንም አመልክቷል። ሲፒጄ በየአመቱ ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞችን ዝርዝር በማጥናት ሪፖርት ማውጣት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች የታሰሩበት አመት ሁለት ሺህ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ በአመቱ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ጋዜጠኞች መታሰራቸውንም ሪፖርቱ አስታውሷል።
ቻይና ጋዜጠኞችን በማሰር ዘንድሮም አለምን ትመራለች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በአማራ ክልል ወደ ስራ ያልገቡ ኢንቨስትመንቶች አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ተደርጎላቸው ስራ ሊጀምሩ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሳሰበ። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን ጨምሮ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትልሀላፊ ተፈሪ ታረቀኝ እና ሌሎች የክልሉ የስራ ሀላፊዎች በባህር ዳር ከተማ በስራ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸውም ዩኒሰን የምግብ ዘይት ማቀነባበሪያ፣ ራቫል የብረታ ብረት ማምረቻ፣ ገደፋው ብረታ ብረት አይ ቬ ኮ የመኪና ጥገናና መገጣጠሚያ ድርጅቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በዚሁ ወቅት አቶ መላኩ አለበል የባህር ዳር ከተማ ለዘርፉ የሰጠውን ልዩና አበረታች ትኩረት አድንቀዋል። በክልሉ ሌሎች ወደ ስራ ያልገቡ ኢንቨስትመንቶችም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በበቂ ሁኔታ ተደርጎላቸው ስራ ሊጀምሩ ይገባል ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል። በባህር ዳር ከተማ እየተገነባ ያለውንና በቅርቡ መገጣጠሙ የተጠናቀቀለትን ዘመናዊ የአባይ ድልድይ የደረሰበትን ደረጃም መጎብኘታቸውን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
በአማራ ክልል ወደ ስራ ያልገቡ ኢንቨስትመንቶች ድጋፍ ተደርጎላቸው ስራ ሊጀምሩ ይገባል አቶ መላኩ አለበል
ህወሀት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን በጄኔራል ሳእረ መኮንን ለመተካት ግፊት እያደረገ ነው በኢህአዴግ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ሹም ሽር ተከትሎ ለረጅም አመታት የጦር ሀይሎች ኢታማዦር ሹም ሆነው የቆዩትን ጄኔራል ሳሞራ የኑስን በጄኔራል ሰአረ መኮንን ለማስተካት ህወሀት ግፊት እያደረገ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል። በትግራይ ብሄርተኝነት ፅንፍ አቋም አላቸው የሚባሉት ጄኔራል ሰአረ ኢታማዦር ሹም ሆነው የሚሾሙ ከሆነ፣ በኦህዴድና ብአዴን ዘንድ ተቀባይነት የማግኘቱ እድል አነስተኛ መሆኑን ምንጮች ይገልፃሉ። ለውጥ ፈላጊ የሆኑ የኦህዴድና የብአዴን አባላት የመከላከያውን ስልጣን ተቆጣጥረው የያዙት የህወሀት ጄኔራሎች ተቀይረው ፍትሀዊ የሆነ የስልጣን ክፍፍል እንዲኖር ሲጠይቁ ቆይተዋል። ይሁን እንጅ የመከላከያ አዛዥነት ቦታውን ለመልቀቅ ፍላጎት የላሳየው ህወሀት፣ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ከእድሜና ከድካም ጋር በተያያዘ ይነሱ የሚለውን ሀሳብ ቢደግፍም፣ አዛዥነቱ ከእጁ እንዳይወጣ እየተከላከለ ነው። ጄኔራል ሳእረ ለቦታው ብቁ መሆናቸውን እና ሌሎች የኢህአዴግ ድርጅቶችም ይህን እንዲቀበሉ ለማድረግ ግፊት የሚያደርገው ህወሀት፣ ከማእከላዊ ስልጣን እየተገፋሁ ነው በሚል ድጋፍ ለማግኘት እየጣረ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትርኒስትር አብይ አህመድ በመከላከያ ውስጥ ለውጥ እንዲደረግ ፍላጎት እንዳላቸው ቢታወቅም፣ በጄኔራል ሳእረ ሹመት ላይ ያላቸው አስተያየት ግልፅ አይደለም።
ህወሀት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን በጄኔራል ሳእረ መኮንን ለመተካት ግፊት እያደረገ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ መሀል ፒያሳ፣ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ እየተካሄደ ያለው ታሪካዊው የአድዋ ሙዚየም ዜሮ ኪሎ ሜትር ግንባታ መከናወን ከጀመረ ሶስት አመት ሆኖታል። አብዛኛው ግንባታ ቢጠናቀቅም አሁን ላይ የመጨረሻ ፊኒሺንግ ስራ ይቀረዋል። የመጨረሻው ስራ ደግሞ ሁሉንም አካታች በሆኑ የስነ ጥበብ ስራዎች የታነፀ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትልልቅ ፕሮጀክቶች ፅህፈት ቤት በስነ ጥበብ ላይ ያተኮሩ ግብአቶችን ለማሰባሰብ ሀዳር ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ያካሄደውን የምክክር መድረክ ከተሳተፉ ታዳሚዎች መካከል፣ አንዳንዶቹ ከሰጡት አስተያየት ለመረዳት እንደተቻለው የማጠቃለያ ስራ ስነ ጥበብ የተሞላበት እንዲሆን ማድረግ ከተፈለገ፣ የህንፃውን ዙሪያ በመስታወት እንዲጋረድ ከማድረግ ይልቅ ድንጋይ ልጥፍ ቢሆን ተመራጭ ነው። ድንጋይ ልጥፍ እንዲሆን ያስፈለገበትም ምክንያት የአየር ሁኔታውን ከመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪን ከማዳን፣ ለወጣቶች የስራ እድልን ከመፍጠር፣ የሀብረተሰቡን ተሳትፎና አንድነት ከማንፀባረቅ አኳያ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በመገንዘብ መሆኑን ነው የተናገሩት። ለልጥፍ የሚውሉ ድንጋዮች የሚሰበሰቡት ከየክልሎች እንዲሆን፣ ክልሎችም የየራሳቸው አይነት ድንጋዮች እንዳላቸው፣ እነዚህን የመሳሰሉ ድንጋዮች በተፈለገው ግንባታ ላይ ሲለጠፍ ለስነ ጥበቡ መሸብረቅና ማማር አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ፣ ይህ ሁኔታም የሀብረተሰቡን አንድነትና ተሳትፎ እንደሚያሳይ፣ ለአገረ መንግስቱ ፅናት ያበረከቱት አስተዋፅኦ አካታችነት መንፈስን ሊያመጣ እንደሚችል ሳይገልፁ አላለፉም። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል የኢትዮጵያ ቅርፃ ቅርፅና ሰአሊያን ማሀበር አባል አቶ ወንድወሰን ከበደ እንደገለፁት፣ ፕሮጀክቱ በከተማ አስተዳደር በጀት ይገንባ እንጂ፣ ታሪካዊ ዳራው አገርንና አሀጉርን የሚወክል ስለሆነ፣ የኪነ ህንፃ ጥበብ ታሪካዊ ዳራውን ያማከለ ሆኖ በጥንቃቄ ሊከናወን ይገባል። የአድዋ ዜሮ ፕሮጀክት እየተገነባ ያለው የአፍሪካ ሀብረት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ እስከሆነ ድረስ፣ የአፍሪካውያን ወንድሞቻችን ሀሳብ በማፍለቅም ሆነ በሌላ ነገር የሚያስተላልፍበት መንገድ ሊመቻችላቸው እንደሚገባ፣ ይህም ሁኔታ በአፍሪካውያን ወንድሞች መካከል ሀብረትን እንደሚፈጥር፣ ከተማዋንም የስነ ጥበብና የፋሽን ማእከል ከማድረግ አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ነው የተናገሩት። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ባልደረባ የሆኑት አቶ አሰፋ በአሁኑ ጊዜ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ግንባታ ፕሮጀክት እየተከናወነ ያለበት ቦታ፣ ለዘመቻው የታለፈበት የአድዋ ድልድይ በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከተማና የአገሪቱ መሪዎች ይኖሩባቸው የነበሩ ቤቶች በአንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያዎቹ የነበራቸው ገፅታ ምን ይመስሉ እንደነበር የሚያሳዩ ፎቶግራፎቹ በሙዚየሙ ቢካተቱ ለሚቀጥለው ትውልድ ጥሩ ማሳያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልፀዋል። ከሙዚየሙ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ባህላዊ እቃዎች ለጎብኚዎች ማሳያና መሸጫ ክፍሎች፣ ለአካል ጉዳተኞች መወጣጫ የሚያገለግሉ ደረጃዎች ሊኖሩት እንደሚገባና የእሳት አደጋ መከላከያዎችንም ባካተተ መልኩ መከናወን እንዳለበት ገልፀዋል። አሁን በመሰራት ላይ ያለው ሙዚየም የጠራ፣ ሁሉንም የሚያካትት፣ የሚቀበለውና በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ የሚሰራ ከሆነ ውጤቱ ለሁሉም እንደሚጠቅም የገለፁት በሙዚየም ውስጥ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ባልደረባ አቶ መሀመድ አህመድ ናቸው። ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ኢትዮጵያን ለመበተንና ህዝቦቿን ለመከፋፈል ለሚሰሩና ለሚያሴሩ ወገኖች አንዱ መንገድ ከፋች፣ የቀድሞ ታሪካችን በተዛባ መልኩ በመሰራቱ ነው፤ ብለዋል። በሙዚየሙ ውስጥ የአስር ጀግኖች ስም ዝርዝር ተለጥፎ መታየቱ አንድ ቁምነገር ቢሆንም፣ ስማቸው በትክክል መጣራት እንዳለበትና አቀማመጡም ቅደም ተከተላቸውን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግ መልካም መሆኑን ነው ያመለከቱት። ለምሳሌ ያህል ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ፣ በታሪክ ጎልተው የሚታወቁበት አባ መላ የተባለው ቀርቶ አባ መቻል በሚል ተፅፎ ለእይታ ቀርቧል። ይህም ሁኔታ በአስቸኳይ መታረምና በትክክለኛው መጠሪያቸው መተካት እንዳለበት አስተያየት ሰጪው ሳይጠቁሙ አላለፉም። የኢትዮጵያ ጦር አድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ከተባለው መነሻ ተነስቶ፣ በቀጥታ ሄዶ አድዋ ላይ የተዋጋበት ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት አስተያየት ሰጪው አመልክተው፣ ፍልሚያው ቦታ እስከሚደረስ ድረስ ብዙ ውጣ ውረዶች እንዳለፉ፣ ጦሩ የተገናኘበት ቦታ ወረኢሉ፣ ከዚያም የአሸንጌና የመቀሌ ጦርነቶችንም አልፎ መንቀሳቀሱን የሚጠቁሙ መረጃዎች በአግባቡ መያዝ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሁሉም ጦር ወደ ፍልሚያው እንዳልተንቀሳቀሰ፣ በተለይ የእነ ኩምሳና የእነ አባ ጅፋር ጦር ሸዋ ከመጣ በኋላ አፄ ምኒልክ፣ ሁላችንም ሄደን አገርን ባዶ ልናደርገው ነው። ስለሆነም የመጣው ጦር ወደ መጣበት ተመልሶ አካባቢውንና ምእራብ ኢትዮጵያን ይጠብቅ፤ ብለው፣ እንዲመለሱ ማድረጋቸው በሙዚየሙ ውስጥ ቦታ ሊኖረው እንደሚገባ ነው የገለፁት። አድዋ የዘመተው ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለው ሁሉም ህዝብ ነው። ስለሆነም የተገኘውም ድል የጋራ ነው። ይህም ሆኖ ግን ጭፈራውና ፉከራው ወይም ወኔ ቀስቃሽ ዜማዎች ሁሉ የሁሉንም ብሄረሰብ የሚገልፁ መሆን አለባቸው። ሙዚየሙ አለም አቀፍ ይዘት ያለው እንደመሆኑ መጠን፣ መግለጫዎቹ ላይ የሚፃፉባቸው ቋንቋዎች አገራዊ ብቻ ሳይሆኑ፣ ኢንተርናሽናል ቋንቋዎችም ቢካተቱበት እንደማይከፋ ነው የገለፁት። የአድዋ ታሪክ በሙዚየም እንዲቀመጥ ተደርጎ፣ ጣሊያን ደግሞ ሁለቴ ነው የወረረችን። ታዲያ ሁለተኛውን ምን እናድርገው በአንደኛው ብቻ ይበቃል ብለን እንተወው ወይስ ለሁለተኛውም ወረራ ማሳያ የሚሆን ሌላ ፕሮጀክት እንቀይስ በማለት አስተያየት ሰጪ ጠይቀዋል። የመቀየሱ ጉዳይ ቢታሰብበት ጥሩ ነው፤ ሲሉም አስተያየታቸውን ደምድመዋል። የትልልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅህፈት ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅና የምህንድስና ዘርፉ ሀላፊ ምሬሳ ልኬሳ ኢንጂነር ፣ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት የሆነው የህንፃ ግንባታ ብሎኮች እንዳሉት፣ አጠቃላይ የመሬቱ ስፋት ሄክታር መሬት ሆኖ ህንፃው ያረፈው ደግሞ ሶስት ነጥብ ሶስት ሄክታር መሬት ላይ መሆኑን ነው የተናገሩት። የጋራ የሆነው ታሪካዊ ገድላችንን የምንዘክርበት የአድዋ ሙዚየም፣ ከአገራችን ታሪካዊ ቅርስነት ባሻገር የመላው ጥቁር አፍሪካውያን ንቅናቄ የሚታወስበት ግዙፍ የታሪክ ቅርስ እንደመሆኑ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጎላ ሙያዊ አበርክቶ እንዲያደርጉ ይፈለጋል፤ ብለዋል። አራት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር የተበጀተለትና ግንባታው በመስከረም ሁለት ሺህ አመተ ምህረት የተጀመረውን ይህን ፕሮጀክት በተቋራጭነት ቻይና ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ኩባንያና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ቢሮ በባለቤትነት እያከናወኑት የሚገኝ ሲሆን፣ የቻይናው ተቋራጭ የግንባታ ዲዛይኑንና ግንባታውን በሰባት መቶ ስላሳ ቀናት ውስጥ ሰርቶ በመስከረም ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ለማጠናቀቅ ውል እንደገባ ይታወሳል። የአድዋ ሙዚየም ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ግንባታ ሲጠናቀቅ ከሁለት እስከ አራት ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የህዝብ ቤተ መፃህፍት፣ የተለያዩ ቢሮዎች፣ ካፍቴሪያና የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን የሚሰጡ ክፍሎች፣ የቤት ውስጥ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የአውቶቡስና የታክሲ መናኸርያ፣ እንዲሁም ከህንፃው ውጪ የቴአትርና የአውደ ርእይ ማሳያ ቦታዎች እንደሚኖሩት ተገልጿል።
የአድዋ ሙዚየም ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ይዘት ከስነ ጥበብ አንፃር
ባለፉት አራትና አምስት አመታት በግልፅ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን መብቱንና ነፃነቱን ለማስከበር የሚያደርገዉ ትግል ጫና በፈጠረበት ቁጥር ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የራሱን ህገመንግስት የሚደፈጥጡ ህጎች አርቅቆ አያፀደቀ ሰላማዊ ዜጎችን አስሯል ገድሏል ከአገር እንዲሰደዱም አድርጓል። ለምሳሌ በ አም የኢትዮጵያ ፓርላማ ከቤተመንግሰት የተላለፈለትን ትእዛዝ አክብሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነፃነት መከበር የሚታገለዉን የግንቦት ንቅናቄ ሽብርተኛ አድርጎ ፈርጇል። ይህ ፈር የለቀቀ ፍረጃ ደግሞ ወያኔ የሱን ዘረኛ ስርአት የሚቃወሙ ግለሰቦችን ሀሳባቸዉን በነፃነት የሚገልፁ ዜጎችን ጋዜጠኞችን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ከወያኔ ጋር አናብርም ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዉያንን ግንቦት ሰባቶች ናችሁ እያለ በጅምላ እያሰረ እንዲያሰቃይ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶታል። ለምሳሌ ከፍትህና ከነፃነት ጥማት ዉጭ ከግንቦት ንቅናቄ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለዉን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን አንዱአለም አራጌን ታዋቂዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና መምህርት ርኢዮት አለሙን የግንቦት አባላት ናቸዉ የሚል ሰንካላና መሰረተ ቢስ ክስ መስርቶ ለረጂም ዘመን እስራት ዳርጓቸዋል።ወያኔ እንደ ዛሬዉ ከተማ ዉስጥ ሆኖ ስልጣን ሳይቆጣጠር ገና ጫካ ዉስጥ እያለ ጥርሱን ከነከሰባቸዉና ከተቻለ አጠፋቸዋለሁ ካለዚያም አሽመደምዳቸዋለሁ ብሎ አስራ ሰባት አመት ሙሉ ከተዘጋጀላቸዉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የአማራ ብሄረሰብ ነዉ። በለስ ቀንቶት ስልጣን ከጨበጠ ማግስት ጀምሮም በወሎና በጎንደር በኩል ከትግራይ ጋር የሚያዋሰኑ ሰፊ የሆነ ለም መሬቱን ጠቅልሎ በመውሰድ ዘረኛ ስርአቱን እድሜ ሊያራዝሙልኛል ይችላሉ ብሎ የሚተማመንባቸውን የቀድሞ የትግል አጋሮቹንና ካድሬዎቹን አስፍሮበታል። ይህ በደልና ግፍ አልበቃ ብሎትም ቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዥዎች ለፈፀሙት ግፍና የአስተዳደር በደሎች ሁሉ አማራዉን በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ እነሆ እስከዛሬ በመርጨት ለዘመናት በሰላም ከኖረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ አድርጎታል። በወያኔ አጋፋሪነት በበደኖ በአርሲ በአረካና ሌሎች አካባቢዎች አማራው ላይ በግፍ የተፈፀመው ጭፍጨፋና ከ እስከ አም አማራዉን ከጉራፈርዳና ከቤንሻንጉል ለማፈናቀል የተወሰደው እርምጃ የዚህ የወያኔ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ውጤት መሆኑን የሚስት የለም።ሟቹ መለስ ዜናዊና በህይወት የሚገኙ ቀንደኛ የወያኔ መሪዎች የተጠናወታቸው የአማራ ጥላቻ በፀረ ፋሽስት ዘመቻ ወቅት ባንዳ ከነበሩ አባቶቻቸዉና አያቶቻቸዉ የተወረሰ ፋሽስት ጣሊያን ለደረሰባት ሽንፈት በዘርና በሀይማኖት ተከፋፍለን እርስ በርሳችን እንድንጠፋፋ ተክላብን የሄደቺው ተንኮል አካል ነው ።የዚህ የጥፋት አጀንዳ አስፈፃሚ የሆነው ወያኔ የጀመረውን አገር የማፍረስና ህዝብ የመከፋፈል አጀንዳ ለማሳካት በየክልሉ የተኮለኮሉ ምስሌኔዎች እንወክለዋለን በሚሉት ህዝብና ክልል ላይ እየፈፀሙት ያለው በደልና ሰቆቃ አዲስ ምእራፍ በያዘበት በአሁኑ ወቅት እራሳቸዏን ለባርነት አዋርደው ህዝባቸውን በማዋረድ ላይ የሚገኙት የብአዴኑ አለምነህ መኮንንን የመሳሰሉ ሆድ አደሮች ውርደት በቃን ዘረኝነት በቃን ብለው በተነሱ ዜጎች ላይ እየወሰዱ ያለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እጅግ አሳሳቢ ሆኖአል።ግንቦት የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከሰሞኑ በደረሰው መረጃ ወያኔ ከአማራው ቀምቶ በትግራይ ክልል ባስገባቸው ወረዳዎች ላይ የሚኖሩ ንፁሀን ዜጎች ለምን በወያኔ የግፍ አገዛዝ ትማረራላችሁ እየተባሉ በወያኔ ታማኝ ሚሊሻዎች እስር እንግልትና ድብደባ እየተፈፀመባቸው መሆኑን አረጋግጦአል። በዚህ በአዲስ መልክ በተጀመረዉ የወያኔ የጥቃት ዘመቻ መሳሪያ ያነገቡ የህወሀት ሚሊሻዎች ከክልላቸዉ ዉጭ ወደ ተለያዩ የአማራ ከተማዎችና ወረዳዎች ሰርገዉ እየገቡ የእነሱን ቋንቋ የማይናገረዉን ሁሉ የግንቦት ተላላኪዎች ናችሁ በሚል እያሰሩ በመደብደብ ላይ ናቸዉ።ይህ በመሆኑ ዛሬ አትዮጵያን ከሱዳንና ትግራይን ከጎንደር ጋር በሚያዋስኑ የአማራ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ገበሬዎች እጃቸዉ እርፍ ከሚጨብጥበት ግዜ ይልቅ በወያኔ ሰንሰለት የሚታሽበት ግዜ ይበልጣል የመንግስት ሰራተኛዉና የከተማ ነዋሪዉም ቢሆን አብዛኛዉን ግዜ የሚያጠፋዉ ከወያኔ ካድሬዎች ጋር ግምገማ በመቀመጥ ሲሆን ተማሪዉና ወጣቱ ህብረተሰብ ደግሞ መጡ አልመጡም እያለ ሌሊቱን የሚያሳልፈዉ በየጫካዉ እየተሸሸገ ነዉ።የዚህ አይነት አስከፊ ግፍና መከራ በአፋር በጋምቤላ በኦጋዴንና በኦሮሚያ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ሲፈፀም ቆይቶአል። ወያኔ እራሱ አርቅቆ ባፀደቀውና በሀምሌ ወር አም በስራ ላይ በዋለዉ የወያኔ ህገ መንግስት ኢትዮጵያ በዘጠኝ የፌዴራል ክልሎች መከፈሏንና እያንዳንዱ ክልል እራሱን በእራሱ የማስተዳደር መብቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ይደነግጋል። በዚህ ህገ መንግስት መሰረት እያንዳንዱ ክልል የራሱ ቋንቋ የአስተዳደር ማእከልና እንዲሁም የክልሉን ሰላምና ፀጥታ የሚያስከብር የፖሊስ ሀይል ይኖረዋል ይላል። ታድያ ለምንድነዉ እያንዳንዱ ክልል የራሱ ፖሊስ ሀይል እያለዉ ከትግርኛ ቋንቋ ዉጭ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ የህወሀት ታማኝ ሚሊሻዎች አማራ ክልል ዉስጥ እየገቡ አማራዉን የሚያሰቃዩትመልሱ ቀላል ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝባዊ አምቢተኝነቱ እያየለ በመጣና የነፃነት ሀይሎች ጡንቻ በፈረጠመ ቁጥር ወያኔ አንገቷ ላይ ቃጭል እንደታሰረባት በቅሎ ይደነብራል። የደነበረ ደግሞ መራገጡ አይቀርምና መሳሪያ ያነገቡ ሀይሎችን እንቅስቃሴ እገታለሁ በሚል ከንቱ ጥረት ደንባራዉ ወያኔ የፈሪ ብትሩን በድንበር አካባቢ በሚኖሩ የአማራ ክልል አርሶ አደሮች ወጣቶችና ሰራተኞች ላይ ማሳረፍ ጀምሯል።ወያኔ እንደ ግንቦት ሰባት የኮነነዉና የህዝብና የአገር ጠላት አድርጎ የሳለዉ ድርጅት የለም የወያኔ የዜና ማሰራጫዎችም ይህንን የአገዛዙን አቋም በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ህዝብ አሰምተዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ማን ለመብቱና ለነፃነቱ እንደቆመና ማን መብቱና ነፃነቱ ላይ እንደቆመበት ለይቶ የሚያዉቅ ህዝብ ነዉ። ስለዚህም ግንቦት ሰባት ወያኔዎች አላፊዉንና አግዳሚዉን ግንቦት ሰባት ነህ እያሉ ከሚያሰቃዩ ህዝብንና ግንቦት ሰባትን ያስተሳሰረዉ ነፃነት ፍትህና ዲሞክራሲ ነዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ ቢመልሱ ለእነሱም ለእኛም ለአገርም ይበጃል የሚል የፀና እምነት አለዉ። ወያኔ በኢህአዴግ ስም ያስጠጋቸዉን ምሰለኔዎች ጨምሮ ከራሱ ዉጭ ሌላ ማንንም አያምንም ስለዚህም ነዉ የአገሪቱን የመከላከያ የደህንነትና የፖሊስ ተቋሞች በራሱ ሰዎች ቁጥጥር ስር ያደረገዉ። ዛሬ በግልፅ እንደምንመለከተዉ ወያኔ በጉልበት ለያዘዉ ስልጣን ያሰገኛል ብሎ በሚጠረጥረዉ ቦታ ሁሉ የራሱን ልዩ ሚሊሺያ እየላከ የኢትዮጵያን ህዝብ መኖሪያ ቤቱ ድረስ አየሄደ እያጠቃ ነዉ። ግንቦት ሰባት ወያኔና የፈጠረዉ ዘረኛ ስርአቱ የቆሙት በፍፁም ማንሰራራት የማይችሉበትት የመጨረሻ መቀበሪያ ጉድጓዳቸዉ ጫፍ ላይ ነዉ የሚል ፅኑ እምነት አለዉ። ሆኖም ጉድጓድ ጫፍ ላይ የቆመ ጠላት በራሱ ተወርዉሮ ጉድጓዱ ዉስጥ አይገባምና ይህንን የተዳከመ ጠላት እየተፈራገጠ ጉዳት ከማብዛቱ በፊት ለመደምሰስ ክንዳችንን አጠናክረን በህብረት እንደ አንድ ሰዉ እንነሳ ይላል።ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ወያኔ በግንቦት ስም ሰላማዊ ዜጎችን ማሰቃየቱን ባስቸኳይ ማቆም አለበት
በአንድ ወቅት የምድር አራዊትና የሰማይ አእዋፋት ወገን ለወገንህ ተባባሉና ሁሉም ከእያሉበት ተጠራርተው ሲያበቁ በአንድ ችግር ላይ መወያት ጀመሩ። ይሀውም በአራዊቱ እና በአኢዋፍቱ ዘንድ ችግር እንዳለና እራሳቸውንም ማስከበር እንዳለባቸው ይመክሩ ጀመር ። በአእዋፋቱ ዘንድም አራዊቱ ዘንድ ችግር እንዳለ እና ደኑን ተማምነው ያልተገባ ነገር እያደረጉ እንደሆነ እንደሚጠራጠሩ ለዚህ ደሞ መፍትሄው ጦርነት ብቻ እንደሆነ እየተነጋገሩ እያሉ የለሊት ወፍ መጣች። ሁሉም በድንጋጤ ቢያያትም ቅሉ የማን ወገን ናት በሚል መልኩ እርስ በእርሳቸው ቢተያዩም ደፍሮ ግን ሊጠይቃት የወደደ ግን ስላልነበር እርሷም የማንነቷን ገልፃ አልተናገረችም። ብቻ ግን አንድ ነገር አስባለች ጦርነቱ ሲጀመር ብዙም ወደሰማይ ከፍ ሳትል ብዙም ወደ መሬት ሳትቀርብ በረራዋን ለማድረግ። ይሁን እና በዚህ መሀል ጉባዬው ጋር ለመገኘት የረፈደባቸው ይቅርታ እየጠየቁና ያጋጣማቸውን እየነገሩ ተቀላቀሉ። የእለቱ ፀሀይ በጣም የሚያቃጥል ቢሆንም ከህልውና የሚበልጥ የለም በሚል ይመስላል በሁለቱም ወገን ምክከሩ የአሰላለፍ አካሄዱ የ እለቱን ውሎ በሚመለከት ተነጋገሩ። ከአእዋፍ ወገን እነ እርግብ እነንስር እነ ጥንብ አንሳ እነ አሞራ ብቻ ሁሉም ከያሉበት ተጠራርተው የመገናኘታቸውን ያህልም ጦሩን ማን ይምራ የሚለውም ነገር ብዙ ካነታረካቸው በሀላ በስተመጨረሻ ንስር የጦሩ መሪ ሊሆን ተማምለው ባሉበት ሰኦት የለሊት ወፍ ፈንጠር ብላ ተቀምጣ ነበርና አንቺ የማን ወገን ነሽሲል ንስር በቁጣ ቃል ጥያቄ አቀረበላት። እርሷም ፈጠን ብላ ምን ጥያቄ አለው ክንፌን ስታይ የማን እመስልሀለው ብላ ጥያቄውን በጥያቄ መለሰችለት። በዚህ ሁኔታ እያሉ የአራዊቱን አሰላለፍ ማን ይሰልል እያሉ አእዋፋቱ ሲነጋገሩ ይህቺው የለሊት ወፍ እኔ ብሄድስ ምክንያቱም ጡት ስላለኝ አጥቢ ናት እና ከእኛ ወገን ነች ብለው ስለሚያስቡ ያለውን ነገር ሁሉ በሚገባ አጤነዋለው ብላ እንደጨረሰች የሁሉም ሀሳብ አንድ ሆነና የለሊት ወፍ ተላከች። እዛም እንደደረሰች አራዊቱ በመልክ በመልክ ተሰብስበው ይወያያሉ። ሁሉም አሉ አንበሳ ነብር አያጅቦ ተኩላ እነ ዝሆን ብቻ አራዊቱ ወገን የቀረም የለ። ይሁንና በውይይታቸው መሀል እንዳሉ የለሊት ወፍ ደረሰች ። ሁሉም አፈጠጡ አንበሳ ነበርና የጦሩ አበጋዝ ምን ፈለግሽ ሲል አፈጠጠባት። የለሊት ወፍም ምንም እንዳልተፈጠረ በመቁጠር ለማርፈዷ ይቅርታ ጠይቃ ለመቀላቀል ስትሞክር አንበሳ ጠንከር ባለ ንግግር የማን ወገን ነሽ ሲል አፈጠጠባት። የለሊት ወፍም ፈጠን ብላ ምን ጥያቄ አለው ከአራዊቱ ወገን ለመሆኔ ጡቴን ማየት ብቻ አየበቃም ስትል በማፍጠጥ በመመለሷ ሁሉም በይሁንታ ተቀብሏት። ስለሚያደርጉት ጦርነት እና የቦታ አያያዝ ብሎም ማን ፊት አውራሪ እንደሚሆን እና ማን ጦር መሳሪያ አቀባይ እንደሚሆን ፕላኑን አውጥተው ከጨረሱ በሀላ አንበሳ ወደ ለሊት ወፍ ዞር ብሎ አጅሪት እስቲ ሂጅና ያለውን ነገር ሰልለሽ ያላቸውን ሀይልና እና የታጠቁትን የጦር መሳሪያ አይነቱን ንገሪን አላት። መላኩ ያስደሰታት የለሊት ወፍ ስትበር ሄዳ የአራዊቱን አቅም ምን ያህል ደካማና በአሰላለፍም ከአኢዋፍቱ እንደማይበልጡ አፏን እያጣፈጠች ነገረቻቸው። በሁኔታው የተደሰቱት አእዋፍቱም በፍጥነት ጦርነቱን ቢጀምሩ አራዊቱ ካለቸው ብቃት ማነስ ጋር ተጨምሮ በድንጋጤ ሊረበደበዱ እንደሚችሉ ነግራ ለመጀመር እየተዘጋጁ ባሉበት ሰአት ለፊት አውራሪው ንስር ጠጋ ብላ ምንም እንኳን ሁኔታው ባይመችም ቅሉ ጦርነቱ ባሸናፊነት እንዲወጡ እርሷ ለአስር ደቂቃ ፀሎት አድርጋ መምጣት እንደምትፈልግ አሳምናው በራ ወደ አራዊቱ ዘንድ በመሄድ ለእነኛ የነገረቻቸውን ሁሉ ለእነዚህም ነግራ ጦርነቱን አስጀመረች። በሁለቱም ወገን ከባድ ውጊያ ሆነ። የለሊት ወፍም ከፍ ብላ በበረረች ግዜ አኢዋፍቱን በርቱ እንጂ መጠቃታችን ነው ስትል ዝቅ ብላ አራዊቱን በርቱ እንጂ መጠቃታችን ነው እያለች ቀኑን ስታዋጋ ዋለች። ከሁለቱም በኩል በጣም ብዙ ሰራዊት ወደቀ። ሬሳ በሬሳ ላይ ተደራረበ። የሚገርመው በእለቱ ከሁለቱም ወገን የጦርነቱ ሚስጠር ያልገባቸው እንዲሁ በየወገንህ ሲባል ብቻ ሰምተው የተሰለፉም ነበሩበት። ባላወቁትም የሞት ሰለባ ሆኑ። ግና በዚህ ሁሉ ምሀል ስትሽሎኮለክ የነበረችው የለሊት ወፍ የምታደርገውን ንስር ከሩቅ ሆኖ ይመለከት ነበርና ሳታስበው አደጋ ጥሎ ከሙታን ጋር ቀላለቀላት። በዚህ ሁሉ መሀል አንበሳ በድንገት ዞር ብሎ ቢያይ የለሊት ወፍ የለችም። ከሀላው ይከተለው ለነበረው ወታደር በቁጣ የለሊት ወፍ የታለች ብሎ ጠየቀው። ወታደሩም ፈጠን ብሎ ከንስር በተጣለ ቦንብ ስትጋይ አይቻታለሁ አለ። ለነገሩ እኔም ላጋያት ነበር የፈለኳት ብሎ ጦርነቱ እየመራ ቀጠለ። በዚህ ሁኔታ ሆዱን መሸከም ያቃተው አያ ጅቦ ከሞቱት ወገኖች መሀል የሞተውን እርሙን ሊበላ ወደሀላ ቀረ። ከአእዋፍቱም ወገን እንዲሁ እነ ጥንብ አንሳ ሆን ብሎ እጁን በመስጠት ከተማረከ በሀላ የሞተውን መብላት ጀመረ። በስተመጨረሻ ጦርነቱን የሰሙት የቤት እንሰሳት በገላጋይነት በመግባት ለሊቱን ለአራዊት ቀኑን ለአእዋፋት ብሎ አምላካችሁ ከፍሎ ሰጥቶአችሁ እያለ ውጊያው ምንን በተመለከተ ነው ሲሉ በዝርዘር የውጊያው አላስፈላጊነት አስረዱአቸው። በሆነውም ከልብ እንዳዙኑ ገልፀው ሁሉን አሳምነው ሲያበቁ በጦርነቱ ወቅት ችግር ፈጣሪ እና ታማኝታቸውን በአቅም ማጣት ምክንያት እና በመምሰል ለመሆን የሞከሩትን ጦር ወንወጀለኞች እንደ ለሊት ወፍ ያለው ከሁለቱም ወገን እንዳትገባ ጥንብ አንሳና ጅብ ዜግነታቸው ተነጥቆ በቁም አስር እንዲቆዩ ተወስኖ ከእንግዲህ የሰላም አገር መስርተው ሊኖሩና የጋራ ጠላታቸውን በጋራ እንደሚከላከሉ ተስማምተው ሊስታርቋቸው የመጡትንም አመስገኑ። በስተመጨረሻም ለአስታሪቀነት ከመጡት አንዷ እመት በግ ተነስታ እስቲ የጦርነቱን መንስሄ ከሁለቱም ወገን ብታስረ ዱን ስትል ሁሉንም አይን አይናቸውን እያየች ጠየቀች። በሁለቱም ወገን ይሄ ነው ብሎ ምክንያት የሚሰጣት በመጥፋቱ አፍረው አንገታቸውን በደፉበት ግዜ አሞራ ከሩቅ ሆኖመሳሪያ ሻጮች ናቸው የሚያጣሉን ሲል ሁሉም በምክንያቱ ተገርመው ሳቁ። በግም በነገሩ ተገርማ ስታበቃ ይገርማል የሚያፈስ ጣራ ያላት ሀገር ይዘን ብዙ ግዜ የምንጣላው ለአጥር በሚሆን እንጨት በሚደረገው ፍለጋ ስለሆነ ነው። ነገር ግን መጀመሪያ መቅደም የነበረበት ጣራን መሸፈን ነው ወይስ አጥር ብላ ሁሉንም አፍጣ ጠየቀች። ሁሉም በአንድነት አሱማ ጣራ ይቀድማል አሉ። አዎ አንዲህ ስላችሁ አጥር አትጠሩ ማለቴ ሳይሆን ከጦርነት በፊት ለምን የሚል ቃልና ትርፉስ የሚለውን አስተሳሰብ አትርሱ። በማለት የእለቱን የማስታረቂያ ንግግር ስታደርግ ሁሉም ተመስጠው በመስማት አድንቀው ሲያበቁ ከዚህ በሀላ ስለሁሉም በማሰብ ስልጣኔን አየር እየዛቁ ለሀገር ለወገን በሚሆን ነገር ላይ በማተኮር ዘመናቸውን እንደሚኖሩ ተነጋግረው ተሳስመው ተለያዩ። ቸር እንሰብት
የለሊት ወፍን ማን ገደላት ከደራሲና ገጣሚ መኳንንት ታዬ
አዲስ አበባ፣ የካቲት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአማራ ክልል መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተሀድሶ ስልጠና የወሰዱ የቀድሞ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ምረቃ ስነ ስርአት ተካሄደ። በምረቃ ስነ ስርአቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ በምክትልርእሰ መስተዳድር ማእረግ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፣ የምስራቅ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል መሀመድ ተሰማ፣ የሰሜን ምእራብ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ብርሀኑ በቀለና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን ተገኝተዋል። ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በምርቃት ስነ ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አባላቱ ህዝባዊነትን ተላብሰው ተልእኳቸውን በብቃት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የአማራ ህዝብ ቀደም ሲል በወራሪ ኀይሎች አሁን ደግሞ በክልሉ ውስጥ ባለው ፅንፈኛ ቡድን እንዲሁም ከሀገር ውጭ ባሉ ግብረአበሮቻቸው እየተፈተነ ይገኛል ብለዋል። የቡድኑን እኩይ አላማና ሴራ ለማክሸፍ መጠነ ሰፊ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስራ ተከናውኖ አመርቂ ውጤት መገኘቱን ገልፀዋል። ኮሚሽነር ደስየ ደጀን በበኩላቸው ለአንድ ሀገር ልማትና እድገት መረጋገጥ አስተማማኝ የሰላም ሁኔታ እና የፀጥታ ሀይል የመኖር አስፈላጊነት የሚያጠራጥር አይደለም ብለዋል። የፀጥታ ሀይል ለተሰጠው ተልእኮና ሀላፊነት እንዲሁም ህዝብን ለማገልገል እስከ ህይወት መስእዋትነት መክፈል ይጠበቃል፤ለዚህም ዝግጁ መሆን ይገባል ነው ያሉት። ለስልጠናው መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።
የተሀድሶ ስልጠና የወሰዱ የቀድሞ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ምረቃ ስነ ስርአት ተካሄደ
በኤምባሲዎች የደህንነት አታቼዎች እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት መካከል ስብሰባ እየተካሄደ ነው። ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ ምእራባውያን ዲፕሎማቶች ዘንድ የሚደርሱ እናፈነዳለን መረጃዎች ከፍተኛ የሆነ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኙ እና ለደህንነት አታቼዎች ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልፀዋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎች እንደሚናገሩት መሀል አገርን እና ምስራቅ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪት ክልሎች ይደረጋሉ የተባሉ ፍንዳታዎች ከአልሸባብ የመጡ ማስጠንቀቂያዎች ናቸው ቢባልም በአልሸባብ ውስጥ በተደረገ የመረጃ ማጣራት አልሸባብ ይህንን መረጃ እንዳልበተነ በአዲስ አበባ የአሜሪካን የደህንነት አታቼ ለማረጋገጥ ያደረጉት ሙከራ በከፊል ባይሳካም የሁኔታውን አሳሳቢነት አስመልክቶ በምእራባውያን የኤምባሲ ዲፕሎማቶች የደህንነት አታቼዎች እና በወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል። ከወያኔ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ይደርሳሉ የሚባሉ ፍንዳታዎች ምእራባውያን ላይ ያነታጠሩ በመሆኑ የሰጉት የሀያላኑ ዲፕሎማቶች ሁኔታው ከመከሰቱ በፊት ለመቆጣጠር ሲሉ አስፈላጊውን የዲፕሎማቲክ ሩጫ እያደረጉ መሆኑ ሲታወቅ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ከሆነ ምርጫ እየደረሰ ስለሆነ ተቃዋሚዎችንና ያልያዛቸውን ጠንካራ ሰዎች ለማፈስ ወያኔ የሚጠቀምበት ስልት ነው። ህዝቡን እያስፈራራ የውጭ አገር መንግስታትንም እንዲሁ አሸባሪ ለመዋጋት እያለ እራሱ የቀበራቸውን ፈንጂዎች ያስጮህብናል። የፈለገውንም ይገድላል። ስለዚህ ህዝቡ ነቅቶ መጠበቅ የግድ ይለዋል።
በኢትዮጵያ ተከታታይ ፍንዳታዎች ይደርሳሉ የሚለው ስጋት አይሏል ደህነቶች እና የኢምባሲ አታሼዎች በስብሰባ ተወጥረዋል
ህዝቤ ሆይ መስቀል በራ፤ ሀገሩ ሁሉ ይቀደስ፤ በምድር ሁሉ ሰላም ይስፈን። ክብራችንም ይመለስ። ባህር ዳር፡ መስከረም ሁለት ሺህ አመተ ምህረት አብመድ መስቀል በክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ ታላቅ ክብር የሚሰጠውና የመዳኛ ሀይል እንደሆነ በፅኑ ይታመንበታል። የመስቀል መዳኛነት ከክርስቶስ ስቅለት ጋር የሚያያዝ ነው። የመስቀሉ ክብረ በአል የሚጀምረው ንግስት እሌኒ በጎለጎታ የተቀበረውን መስቀል ቆፍራ ካወጣችበት ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ።የመስቀል በአል በኢትዮጵያውያ ግን ከሀይማኖታዊ ክዋኔው ባለፈ ከሀይማኖቱ ጋር የተሳሰረ ባህላዊ ክዋኔም አለው። መስቀል በኢትዮጵያውያን መስሪያ ቤት ተዘግቶ ህዝቡ ሁሉ በየቤቱ አረፍ ብሎ መስከረም ቀን የሚያከብረው በአል ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መስከረም ደመራ ተደምሮ አመሻሽ ላይ የሚለኮስበት ሁኔታ ያለ ሲሆን በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ደግሞ በ ተደምሮ በ አጥብያ ነው ደመራው የሚለኮሰው።ደመራው ሲደመር የተላጠ እርጥብ እንጨት መሬት ተቆፍሮ ይተከላል። የእርጥቡ እንጨት አንድምታ አመቱን በአዲስ መንፈስ በአዲስ ተስፋ ለመጀመር ምሳሌ እንደሆነ መርጌታ ዮሴፍ ዳኘው ተናግረዋል። በዙሪያውዋ ተደርድረው የሚቆሙት አንጨቶች ወይም ችቦዎች ደግሞ አንድነትን፣ ተደጋግፎ መኖርንና መረዳዳትን የሚያመለክቱ እንደሆነ ነው መርጌታ ዮሴፍ ያስረዱት።በሰሜኑ ክፍል ደመራው ማታ ከተደመረ በኋላ ደመራ የሰሩት የቀዬው ልጆች ደመራውን እዮሀ አበባዬ መስከረም ጠባዬ እያሉ ሶስት ጊዜ ይዞሩታል። ሶስት ጊዜ ከተዞረ በኋላ ሌሊቱ ሳይነጋ ተነስተው ደመራውን ለመለኮስና የመስቀሉን ማብራት ለማብሰር ቀጠሮ ይዘው ይለያያሉ።ሌሊቱ ሊነጋጋ ሲል ዶሮ መጮህ ሲጀምር የቀየው ሰዎች በየቤታቸው የሰቀሉትን ችቦ እያወረዱ የቤታቸውን ጎተራ፣ የሊጥ እቃ፣ እንስራ፣ ጋን፣ የቤቱን በር፣ የበሬውን ሻኛና የበረቱን በር እየተረኮሱ ደመራው ወደ ተሰራበት ስፍራ ይተማሉ። በተለይም የበሬዎቻቸውን ሻኛ ሲተኩሱ በበሬው ሻኛ በላሟ ጉኛ ያለውን አውጣልን፤ ጣልልን ይላሉ።ደመራው ከተሰራበት ስፍራ ሲደርሱ በቀየው ዘንድ የሚከበር መካሪ፣ አስታራቂ፣ ታሪክ ነጋሪ፣ ታላቁ አባት ፊት ለፊት እየመሩ ሌላው የቀየው ሰው ደግሞ ከኋላ ኋላ እየተከተለ ደመራውን ይዞራሉ። የታላቁ አባት መምራትና የሌላው ህዝብ መከተል መከባባርን፣ መሪና ተመሪ መኖሩን ማሳያ እንደሚሆንም መምህር ዮሴፍ ነግረውናል። ደመራውን ከሁሉም ቀድመው የሚለኩሱት ታላቁ አባት ናቸው። እርሳቸው ከለኮሱት በኋላ የተሰበሰበው ህዝብ የያዘውን ችቦ ወደደመራው ይሸጉጣል። ደማራውም ይቀጣጠላል፤ ደስታም ይሆናል።ጨለማው በብርሀን ሲገለጥ የህዝቡ ተስፋም በብርሀኑ ይፈካል። ደመራው ተቀጣጥሎ የቀየው ሰውም በደመራው ዙሪያ ተቀምጦ ስለአዝመራውና ኑሮው እያወጋ ያነጋል። ሌሊቱ ሲነጋ እናቶች በዱባ ዝኩኒ ቅጠል የተጠቀለለ እርሚጦ በሌማት፣ በሰፌድ ወይም በቁና ይዘው ይመጣሉ። የደረሰ በቆሎ ካለም የበቆሎ እሸት ያመጣሉ። እናቶች ይሄን ይዘው ሲመጡ በደመራው የተቀመጡ ሰዎች እንጎሮገባሽ ይሏቸዋል። እንጎሮ ገባሽ ማለት እንኳን ወደ ጓሮ ገባሽ፣ እንኳንም አዲስ እህል ይዘሽ መጣሽ ማለት እንደሆነም መሪጌታ ዮሴፍ አብራርተዋል።
የደመራው ቋሚ እንጨት ወደየትኛው አቅጣጫ ወድቆ ይሆን
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አገሪቱን ስጋት ላይ በጣላት ብሄር ተኮር ግጭትና የፖለቲካ ቀውስ ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማርያም ደሳለኝ ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለፁት፣ የምክር ቤቱ አባላት ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ እስኪገኙ ድረስ መደበኛ ስብሰባዎችን ማካሄድ ተገቢ አይደለም የሚል አቋም ይዘዋል። በርካታ መሆናቸው የተገለፀው የምክር ቤት አባላት ረቡእ ታሀሳስ አራት ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት ፣ በየተወከሉባቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ውይይት ማካሄዳቸውን ምንጮች ገልፀዋል። በዚህም ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል የኦህዴድና የብአዴን አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ተገኝተው ወቅታዊ ግጭቶችንና የፖለቲካ ቀውሱን አስመልክቶ እንዲያብራሩ፣ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችም ዝርዝር ምላሽ እንዲሰጡ አቋም ይዘው ጥያቄ ማቅረባቸውን ለማወቅ ተችሏል። አባላቱ ላቀረቡት ጥያቄ ከምክትል አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ ምላሽ እየተጠበቀ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ሀሙስና ማክሰኞ ታህሳስ አስር ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት መካሄድ የነበረበት የፓርላማው መደበኛ ስብሰባ አለመካሄዱ ታውቋል። ይሁን እንጂ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በፕሮግራማቸው መሰረት ሀላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን ምንጮች አክለው ገልፀዋል። በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ መሰረት የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በወር አንድ ጊዜ ጠርተው ትኩረት ባደረጉበት የስራ አፈፃፀማቸው ላይ ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ፣ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአመት ሁለት ጊዜ ዝርዝር የስራ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ እንዲያቀርቡ ግዴታ ይጥልባቸዋል። ከወር በፊት የምክር ቤቱ አባላት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማው ተገኝተው በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተቀስቅሶ ስለነበረው ግጭትና የፖለቲካ ሁኔታ፣ እንዲሁም ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊነት ለመልቀቅ ጥያቄ ስላቀረቡ ከፍተኛ አመራሮች መነሻ ምክንያት ማብራሪያ መጠየቃቸውና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት፣ ምንም አይነት መረጃ እንደሌለው ለሪፖርተር ገልጿል።
የፓርላማ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እየጠበቁ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በሰው ሀይል ልማት በተለይም ብቁ የሰራዊቱን አመራሮች ለማፍራት ከለውጡ ወዲህ ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገለፁ። የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ከኢፌዴሪ አየር ሀይል የተውጣጡ ሀያ አራት የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በሰርተፊኬት አስመርቋል። ከፍተኛ አመራሮቹ በሀገራዊ፣ አካባቢያዊ እና አለም አቀፋዊ እንዲሁም ጦርነት ጠቅላላ ንድፈ ሀሳቦችን ጨምሮ በመሰል ተዛማጅ ርእሰ ጉዳዮች ላይ መሰልጠናቸው ተገልጿል። በስልጠናው ማጠቃለያ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ አየር ሀይሉ በሰው ሀይል ልማት በተለይም ብቁ የሰራዊቱን አመራሮች ለማፍራት ከለውጡ ወዲህ ውጤታማ ስራ ማከናወኑን ገልፀዋል። ተቋሙ በሁሉም መስክ ላስመዘገበው ስኬት በዋነኝነት የቁርጠኛ አመራር ሚና ወሳኝ ስለመሆኑም ጠቁመዋል። የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ የተካኑ የወደፊቱን የጦር መሪዎችን ለማፍራት የሚያከናውነው ስራ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀው፤ አየር ሀይሉም ከኮሌጁ ጋር ተባብሮ የመስራት ግንኙነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዲዬር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ በበኩላቸው፤ ተቋማቱ ለአንድ አይነት አላማ በጋራ የተሰለፉ መሆናቸውን አንስተዋል። በማስተማር፣ ሀሳብ በመስጠት እና ሁኔታዎችን በማመቻቸትም ጭምር ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን መግለፃቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገፅ መረጃ አመልክቷል። በአየር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ የተሰጠው ስልጠና አመራሮቹ ከስራ ቦታቸው ሳይርቁ በንድፈ ሀሳብና በተግባር ልምምድ የተደገፈ ውጤታማ ስልጠና መሆኑን የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን ኮሎኔል ጥላሁን ታደሰ ገልፀዋል።
አየር ሀይሉ ብቁ የሰራዊቱን አመራሮች ለማፍራት ከለውጡ ወዲህ ውጤታማ ስራ አከናውኗል ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ
መሬታችንን ለምን እንነጠቃለን በማለት የጠየቁ ተገድለዋል። ተገርፈዋል። ታስረዋል። አሁን ድረስ እስር ላይ የሚገኙ አሉ። ባእድ እንኳን ባልሞከረው የከፋ ጭካኔ በከባድ መሳሪያ በተደገፈ የጦር ሀይል የተወለዱበትን መሬት እንዲለቁ የተገደዱ አዛውንቶች ላይ የተፈፀመው ግፍ እስከ ወዲያኛው የሚያሽር አይደለም። በሌሊት እርቃናቸውን ከሚያርፉበት ታዛ ስር ነፍጠኛ ሰራዊት እንዲከባቸው እየተደረገ የተፈፀመው አስነዋሪ ግፍ ጊዜ የሚጠብቅ እንደሆነ በየጊዜው የሚገለፅ ነው።የዘራሁትን ሳላነሳ በዶዘር ማሳዬን ጠረጉት በዶዘር እርሻዬ ውስጥ ገብተው አረሱት መሬቴን ለምን ትወስዳላችሁ የት ልትወስዱኝ ነው ያሸተውን በቆሎዬን መነጠሩት። ምን ላደርግ እችላለሁ። መሳሪያ የያዙ ወታደሮች ከበውኛል ጠዋት ስነሳ ማሳዬ ባዶ ሆኖ አገኘሁት ይህ ሁሉ የበደል ሰቆቃ ነው። በምስል ተደግፎ የቀረበ ህሊናን የሚሰብር መረጃዎች አሉ። አንድ የአካባቢው ነዋሪ ሰላማዊ ህዝብ በቅጡ የሚለብሰው እንኳን የሌለውን ህዝብ አሮጊቶችን አዛውንቶችንና ህፃናትን ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የቆዩት ለዚህ ነው ለዚህ ኢንቨስትመንት ነው ያ ሁሉ የተፈጥሮ ደን ወድሞ ከሰል እንዲሁን የተደረገው ገንዘብ ሳይሆን የከሰል ጆንያ ይዘው ክልሉን እንዲቀራመቱ የሚፈቅዱት ክፍሎች ስለጊዜና ስለዘመን ለምን አያስቡም ሲል ይጠይቃል። በማያያዝም ከመቶ የሚሆኑት ባለሀብቶች የትግራይ ሰዎች መሆናቸውን እናውቃለን። መረጃውም አለን። እባካችሁ የተጨቆናችሁ የትግራይ ወንድምና እህቶች እባካችሁን በስማችሁ እየተፈፀመብን ያለውን በደል ተቃወሙ ሲል ለጎልጉል የድረገፅ ጋዜጣ አስረድቷል።አዛውንቱ ፀሀይ ለመሞቅ ታዛ ስር ቁጭ ባሉበት በፎቶው የሚታዩት አይደሉም ከሙሉ ቤተሰባቸው ጋር የጥይት ራት የተደረጉበት ኢንቨስትመንት አስቀድሞ የተገለፀ ቢሆንም መጨረሻው ሌብነት እንደሆነ ኢህአዴግና ራሱ ድርጅቱ ማመናቸው ተሰማ። አቶ መለስ ሲጀነኑበት የነበረው ኢንቨስትመንት አውላላ ሜዳ ላይ የተደፋ ስለመሆኑ የተጠየቁት አቶ ኦባንግ ሜቶ እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልተሸጠው መሬት ነው በማለት አቶ መለስ የተናገሩትን በማስታወስ ህዝብን የማይሰማ ድርጅት ዞሮ ዞሮ ከውርደት አይድንም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሰሙት ዜና የሚጠበቅ እንደሆነ ያመለከቱት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሚዲያዎች በነካ እጃቸው ስለ ሰለባዎቹም ይተንፍሱ ሲሉ ጠይቀዋል።ኦገስት የታተመው የጎልጉል ዜና የኢትዮጵያን ለም መሬት ከተቀራመቱት ኢንቨስተሮች መካካል አንዱ የሆነው የህንዱ ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ለቅቆ የሚወጣበት ጊዜ መቃረቡን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታወቁ። አበዳሪዎችና ባለ አክሲዮኖች ፊታቸውን እንዳዞሩበትም ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ባዶ ዋይታ የሚያሰማው ኢህአዴግ የያዘው አዲስ አቋም ድርጅቱንና ከድርጅቱ ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው የሚባሉትን ሀሳብ ላይ ጥሏል ሲል መዘገቡ ይታወሳል።በዚሁ ዘገባ ላይ በቦታው ኢህአዴግና ጭፍሮቹ መካከል ሆነው የተካሄደባቸውን የመሬት ነጠቃ በመቃወምና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ጀብድ ለሰሩት በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልፃችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልፁት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችኋልና ክብር ይሁንላችሁ ሲሉ አቶ አባንግ ያስተላለፉት መልክትም ከዜናው ጋር ተካትቶ ነበር።በእውቀት ላይ የተመረኮዘ በእቅድ የተያዘ ትግል እያካሄድን እንደሆነ በገለፅኩበት ወቅት ካሩቱሪ በኪሳራ ከኢትዮጵያ ምድር እንደሚወጣ ተናግሬ ነበር። አሁን ጉዳዩ ያለው የኢትዮጵያን ድንግል መሬት በሳንቲም የቸበቸቡትና ያስቸበቸቡት የጥቅም ተጋሪዎችና ደላሎችን ለይቶ ለፍርድ የሚቀርቡበትን ስራ መስራቱ ላይ ነው። በህንድ ጥሪያችንን ሰምተው ትግላችንን የተቀላቀሉ ፍትህ ወዳድ እህትና ወንድሞች ምስጋና ይገባቸዋል በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለ ካሩቱሪ የተሰማውን ዜና አስመልክተው ተናግረዋል።ሰንደቅ የተሰኘው ጋዜጣ ዜና ባለስልጣኖችንና የካሩቱሪን ሀላፊ አነጋግሮ ይፋ ያደረገው ዜና ኢህአዴግን የሚያሳፍር ከመሆኑም በላይ ከዝርፊያው በስተጀርባ ያሉትን በሙሉ ያስደነገጠ ሆኗል። የጎልጉል ምንጭ እንደሚሉት የጋምቤላ ድንግል መሬት በሳንቲም ሲቸበቸብ ከጀርባ ሆነው ኮሚሽን የተቀበሉና የሚቀበሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ደላሎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የአገሪቱን ሀብት በአይነት ገንዘቧን በብድር ወገኖቻቸውን በጥይት እያስደበደቡ ለባእድ በመስጠት የፈፀሙት ወንጀል መጨረሻ በራሳቸው አንደበት ይፋ ተደርጓል።የአክሲዮን ሽያጩና የብድር ምንጩ የደረቀበት ካሩቱሪ ንብረቱ ለሀራጅ እንዲቀርብ በዝግጅት ላይ ነው። ሰንደቅ
ድሆችን ያፈናቀለው ኢንቨስትመንት እዳ ዋጠው
ከሳኡዲ አረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያንን ለማቋቋም ሰባት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ፣ ከስደት ተመላሾች መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ አስታወቀ። መንግስት በሳኡዲ አረቢያ የነበሩ ስደተኞች ለበርካታ ጊዜያት በእስር ከቆዩ በኋላ ከመጋቢት ሀያ አንድ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ጀምሯል። በሳኡዲ አረቢያ በአጠቃላይ ከሰባት መቶ ሀምሳ ሺህ ዜጎች እንደሚኖሩና አራት መቶ ሀምሳ ሺህ የሚሆኑት በህገወጥ መንገድ የሄዱ መሆናቸውን፣ የአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት አይኦኤም መረጃ ያመለክታል። መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ለመለለስ በእቅድ የያዘው አንድ መቶ ሁለት ሺህ ዜጎችን ሲሆን፣ ይህም ከሰባት እስከ ወራት እንደሚወስድ ተገልጿል። ከስደት ተመላሾቹ ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች የሚቆዩ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ስድስት ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሰባት መጠለያዎች መዘጋጀታቸውን ከስደት ተመላሾች መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ ተጠሪ አቶ ተፈሪ ታደሰ ገልፀዋል። ዜጎቹ ከደረሰባቸው ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሲያገግሙም፣ የራሳቸውን ስራ ለማስጀመር የማቋቋም ስራ እንደሚከናወን አክለዋል። መልሶ ማቋቋሙን ለማከናወን በአጠቃላይ እስከ ሰባት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ ተፈሪ፣ ይህም መንግስትን ጨምሮ ከረጂ ድርጅቶችና ከፋይናንስ ተቋማት ለማግኘት መታቀዱን አርብ መጋቢት ሀያ ሶስት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ከፋይናንስ ተቋማትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በተደረገበት ወቅት ተናግረዋል። ገንዘቡን በብድር መልክ ለማቅረብ ቢታሰብም በተለይም ከፋይናንስ ተቋማት ለሚገኘው ብድር እንደ ችግር የሚነሳው የማስያዣና የወለድ ችግር መሆኑን አስረድተዋል። ለዚህም የፋይናንስ ተቋማት የሚሰጡት ብድር በአነስተኛ ወለድ በአፋጣኝ እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል። የብድር አቅርቦቱን በተመለከተ ለሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጥቃቅንና አነስተኛ ብድር አቅርቦት ዳይሬክተር ወይዘሮ መልካም በለጠ፣ መንግስትም ሆነ ረጂ ድርጅቶች ዋስትና ከገቡ ብድሩን ማቅረብ እንደሚቻል ገልፀዋል። ለዚህም በተለይ ባንኮች እንደ መስፈርት የሚጠይቁት የአዋጭነት ጥናት በመሆኑ፣ ተቀባይነት ያለው የአዋጭነት ጥናት ተደርጎ መቅረብ ይጠበቅበታል ብለዋል። ከስደት ተመላሾችም ሆነ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ብድር ሲጠይቁ ያለ በቂ ጥናት በመሆኑ ባንኮች ብድሩን ለመስጠት እንደሚቸገሩ የገለፁት ወይዘሮ መልካም፣ ለዚህም መንግስትም ሆነ ሌሎች አካላት ደረጃውን የጠበቀ የብድር መጠየቂያ ጥናት በመስራት ሊደግፏቸው ይገባል ብለዋል። የእናት ባንክ የቅርንጫፍ ስራ ማስተባበሪያና ሀብት ማሰባሰብ ዳይሬክተር ወይዘሮ በአለምላይ አየነው በበኩላቸው፣ እናት ባንክ ለሴቶች ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ባንክ ስለሆነ ከስደት ተመላሽ ለሆኑ ሴቶችም ብድር ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆኑን ተናግረዋል። ተቀባይነት ያለው የስራ ምክረ ሀሳብ ለሚያቀርቡም ያለ ማስያዣ እስከ ሶስት መቶ ሺህ ብር ከእናት ባንክ መበደር እንደሚችሉ ገልፀዋል። በተለያየ መንገድም እስከ ሰባ በመቶ የሚሆነውን መጠን ለሚያስይዙ ብድር እንደሚቀርብላቸው አክለዋል። ብድር ከተገኘ በኋላ ወደ ስራ ለሚገቡት የመስሪያ ቦታዎችን ክልሎች እንደሚያቀርቡ አቶ ተፈሪ ገልፀው፣ የመስሪያ ቦታዎችን ሙሉ ለሙሉ ማቅረብ ካልተቻለ ደግሞ በኪራይ እንደሚጠቀሙና ክፍያውንም መንግስት እንዲሸፍን ይደረጋል ብለዋል።
ከስደት ተመላሾችን ለማቋቋም ሰባት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አራት ኪሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጆሊ ባር ኮጆሊ ባር ወደ አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገርያ የሚያገለግል የብረት መሰላል መስራቱ ይታወሳል። ባለስልጣኑ ይህንን መሸጋገሪያ መሰላል የሰራው በአካባቢው የሚተላለፈው የህዝብ ብዛት ከሌሎች አካባቢዎች የበዛ ስለሆነ የትራፊክ መጨናነቅና በየቀኑ በተሽከርካሪ አደጋ እየተቀጠፈ ያለውን የሰው ህይወት ምንም በተባሉት ቦታዎች እስካሁን የከፋ አደጋ ባይደርስም ለመታደግ በሚል መሆኑ ግልፅ ነው። ባለስልጣኑ ሶስተኛ መሸጋገሪያ ድልድይ የሰራው ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ወደ ራስ መኰንን ወደ አዲሱ ገበያና ወደ አፍንጮ በር ውቤ በረሀ በሚወስደው አደባባይ ላይ ነው።ይህ መሰላል አቀማመጡ ወይም የተሰራበት አቅጣጫ ለተጠቃሚው አመች ባለመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ሲጠቀሙበት የሚስተዋሉት የጐዳና ተዳዳሪዎች ናቸው። በአካባቢው የሚኖሩት የጐዳና ተዳዳሪዎችም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥር ስር የሚያድሩና በልመና ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ መሰላሉን መፀዳጃ በማድረጋቸው መተላለፊያነቱ ቀርቶ የበሽታ ማስተላለፊያ እስከመሆን ደርሶ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያሰራው የፒያሳው የመተላለፊያ መሰላል በአካባቢው በሚገነባው የቀላል ባቡር ተርሚናል ምክንያት ሰሞኑን እንዲፈርስ ተደርጓል። የተሰራበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን የሚያስታውሱ የአካባቢው ነዋሪዎች አስተዳደሩ የሚመራው በእቅድና በፕሮግራም ከሆነ ቀላል የባቡር መስመር በቅርብ እንደሚሰራ እያወቀ በዚህን ያህል ወጪ ለምን አሰራው በማለት በትዝብት እየጠየቁ ይገኛሉ። ፎቶና ዜና ሪፖርተር
ጥቅም ላይ ሳይውል የፈረሰው መሸጋገሪያ
አዲስ አበባ፣ ታሀሳስ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የተባበሩት መንግስታት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፈንድ ዩኤንሲኢአርኤፍ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል ሀያ ሶስት ሚሊየን ዶላር መመደቡን አስታወቀ። የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እና አጋር ድርጅቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ አደጋዎች የተጠቁ አካባቢዎች ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ ክፍተት መሙላት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። በውይይቱ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ትብብርና ለማጠናከር መስማማታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል። በተመድ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፈንድም በጎርፍ አደጋ ለተጎዱት ስምንት ሚሊየን ዶላር፣ በወረርሽኝ ለተጠቁ አምስት ሚሊየን ዶላር እንዲሁም በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ደግሞ አስር ሚሊየን ዶላር በአጠቃላይ ሀያ ሶስት ሚሊየን ዶላር መመደቡን በመድረኩ አስታውቋል። የአለም ምግብ ፕሮግራም እና ክሪስቲያን ሪሊፍ ሰርቪስ በበኩላቸው በአማራ፣ ትግራይና አፋር ክልሎች የሰብአዊ ድጋፍ ለማዳረስ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል። የሰብአዊ ድጋፍ ተጠቃሚዎችን ለመለየት የዲጂታል መታወቂያን በመጠቀም ድጋፍን ለማዳረስ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ምክክር ተደርጓል። የአራት ወራት የአፋጣኝ ጊዜ ምላሽ እቅድ ትግበራ ላይም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ጥሪ ቀርቧል። ሰብአዊ ድጋፍ አቅራቢዎች ተረጂዎችን በቤተሰብ ደረጃ ለመለየት የሚያስችል የተናበበ የአሰራር ስርአትን ለመተግበር በምክክሩ ወቅት መስማማታቸው ተጠቁሟል። በውይይት መድረኩ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ ማሪያም ዶክተር እና በተመድ የኢትዮጵያ ዋና ተጠሪ ራሚዝ አላክባሮቭ ዶክተር የተመራ የአጋር ድርጅቶች አመራሮች ልኡካን ተሳትፈዋል።
የተመድ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፈንድ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ሀያ ሶስት ሚሊየን ዶላር መደበ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍቢሲ በሊቢያ በዚህ አመት ቢያንስ ሁለት መቶ ሰማኒያ አራት ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ ባደረገው ሪፓርት በሊቢያ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተባባሰ መሆኑን ነው ያስታወቀው።በተመድ የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሩፔርት ኮልቪል በዚህ አመት የተመዘገበው ሞት ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከአንድ አራተኛ በላይ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል ።በሰላማዊ ሰዎች ፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ፣ የስደተኞች አያያዝ እንዲሁም እስራት አሳሳቢ እንደሆኑ ጠቅሰዋል ።ለበርካታ ሰዎች ህይወት ህልፈት በመሆነው የአየር ጥቃት አንድ መቶ ሰማኒያ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሁለት መቶ ሰዎች ጉዳት እንዳጋጠማቸው ነው የተነገረው።ቃል አቀባዩ እንዳሉት በግጭቱ ምክንያት ሶስት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውና አንድ መቶ ሺህ ዜጎች የመፈናቀል ስጋት እንዳለባቸው አንስተዋል።ምንጭ፣
በዚህ አመት በሊቢያ ቢያንስ ሁለት መቶ ሰማኒያ አራት ዜጎች ሞተዋል ተመድ
ሀምሌ አራት ቀን አመተ ምህረት ኢሳት ዜና የዋግ ነዋሪዎች በከተሞች ዙሪያ በተጠራ ስብሰባ ላይ ድርጅቱ በአካባቢያቸው ተመስርቶ አስፈላጊውን ድጋፍ አድርገውለት ለስልጣን ቢያበቁትም ስልጣን ከያዘ በኋላ ግን እንደጠላቸውና እንደረሳቸው ተናግረዋል። አንዳንድ ጊዜ የትግል ታሪካችንን ለመናገር ስንፈልግ የታላላቅ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ታሪክ እንኳን ለመናገር ስንፈልግ የሚያሸማቅቅ ሁኔታ ነው ያለው በማለት በድርጅቱ እንደሚያፍሩበት ገልፀዋል።ይህ ህዝብ ይህንን ድርጅት ደግፎ እዚህ ያደረሰው ጥቅሜን ያስከብርልኛል ብሎ እንጅ መንግስተ ሰማያት ያስገባኛል ብሎ አልነበረም የሚሉት ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የሚነሱ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች እንኳን የሚመለሱላቸው በለቅሶና በቁዘማ መሆኑን ያስረዳሉ። ልብ ያለው ልብ ይበል ሲሉም ያስጠነቅቃሉ።ብቃት ያለው አመራር የለም ያሉት ሌለው አስተያየት ሰጪ ተሀድሶ ተደረገ ከተባለ በኋላ የተሻሉ የተባሉት ሰዎች ተወግደው ኪራይ ሰብሳቢዎች አሸንፈው ወጥተዋል ይላሉ። እዚህ ያለው ህብረተሰብ እያለቀሰ ለማን መናገር እንዳለበት ግራ ተጋብቶ የሚገኝ ህዝብ ነው ሲሉ ያክላሉ።ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴውን ተከትሎ አገዛዙ ጥልቅ ተሀድሶ በሚል እቅድ ህዝቡን ያረጋጋልኛል በማለት የተለያዩ እርምጃዎችን ቢወስድም ህዝቡ ግን የሚቀበለው አልሆነም።
ብአዴንን ደግፈን በመታገላቸው እንደሚፀፀቱ የሰቆጣ ነዋሪዎች ተናገሩ
ሰሞኑን በዳንኤል ተፈራ ተፅፎ ለገበያ የቀረበው ሀገር የተቀማ ትውልድ የተሰኘው ወጥ የሆነ የፖለቲካ መፅሀፍ እየተነበበ መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ። እንደምንጮቻችን ገለፃ ወጣቱ ደራሲ፣ አርታኢና ፖለቲከኛ ዳንኤል ተፈራ በአጠቃላይ ለአንባቢ ያደረሳቸው መፅሀፎች ሶስት ሲሆኑ ስድስት ለሚሆኑ የፖለቲካ መፅሀፎችም የአርትኦት ስራ ሰርቷል። ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሎ እየተነበበ ካለው ሀገር የተቀማ ትውልድ ከሚለው መፅሀፉ በፊት እጅግ ተነባቢ የሆኑ ሁለት መፅሀፎችን ለአንባቢያን እንዳደረሰም ለማወቅ ተችሏል። የደራሲው ቀዳሚ ስራ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና በኋላም የተቃውሞ ጎራው መሪ የነበሩትን እውቅ ሰው ዶክተር ነጋሶ ጎዳዳ ሶለንን የህይወት ታሪክ የሚዳስስ ዳንዲ የነጋሶ መንገድ የተሰኘው ነው። ይሄ መፅሀፍ በሁለት ሺህ ሶስት አመተ ምህረት ለህትመት የበቃ ሲሆን በአንድ ሳምንት ብቻ ሀያ ሺ ኮፒ በመሸጥ ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው። ከዚያ በኋላም ለአራት ጊዜ እንደታተመ ደራሲው አረጋግጧል። ደራሲው እንደሚገልጠው መፅሀፉ ሶስት መቶ ሰማኒያ አራት ገፆችና አምስት ንኡስ ክፍሎች ያሉት ሲሆን የዶክተሩን ከልጅነት እስከ እውቀት እንዲሁም የፖለቲካ ታሪካቸውን ያካተተ ነው። መፅሀፉን ለማዘጋጀት አመት ከሶስት ወር እንደፈጀ ደራሲው ይናገራል። ቀጣዩ የዳንኤል ስራ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት አመተ ምህረት በኋላ በፓርላማ አባልነታቸው በከፍተኛ ተከራካሪ በነበሩት የተከበሩ አቶ ተመስገን ዘውዴ የፖለቲካ ህይወትና እንዲሁም በፓርላማው ውስጥ ህወሀት ኢህአዴግ ሲፈፅም የነበረውን ሸፍጥ ያጋለጡበት ከፓርላማው በስተጀርባ የተሰኘው መፅሀፉ መሆኑን ለዘጋቢያችን ተናግሯል። ሰሞኑን ገበያ ላይ የዋለው ሀገር የተቀማ ትውልድ ደግሞ የፀሀፊው ወጥ የፖለቲካ ስራ ሲሆን ሁለት መቶ ሀያ አራት ገፅ ያለው ነው። መፅሀፉ በሀያ ሰባት ምእራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በዋናነት በዘመነ ኢህአዴግ ወጣቱ ትውልድ እንዴት የሀገር ፍቅር እንዲያጣ እንደተገረገና ሀገር አልባ ለማድረግ የተከናወኑ የፖለቲካ ሸፍጦችን የሚተርክ መፅሀፍ ነው። ደራሲው እንደገለፀው፡ ስርአቱን በአሽከርነት ካላገለገልክ እጣ ፈንታህ ሀገር መቀማት ነው። ሀገር ማለት ሰው ነው ይሉሀል እንጂ ሀገር ኢህአዴግ ሆኗል። ኢህአዴግ ካልሆንክ ስራ አይኖርህም፣ ኮንዶሚንየም አይደርስህም፣ መነገድ አይፈቀድልህም፣ ደመወዝ አይጨመርልህም፣ ጡረታ አይከበርልህም፣ የትምህርት እድል አይሰጥህም፣ በነፃነት መወዳደርና ጨረታ ማሸነፍ አያስችልህም። ይህ ማለት ሀገር ተቀምተሀል ማለት ነው። ስለዚህ ይህንን ለመፃፍና ትውልዱ ሀገር እንዲቀማ የሰሩ፣ የቀሙ፣ ያስቀሙ፣ ያቀማሙና የተቀሙትን ታሪክ በማንሳት ሀገር ይረከባል የሚባለው ትውልድ እንዲነቃቃና የሀገር ባለቤት እንዲሆን በማሰብ የተፃፈ ነው በማለት ሀሳቡን ገልጧል።
ሀገር የተቀማ ትውልድ የተሰኘው የዳንኤል ተፈራ መፅሀፍ እየተነበበ ነው
አዲስ አበባ፣ታህሳስ ዘጠኝ፣ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ህንድ ኢትዮጵያን በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዘርፍ ልማት ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች።በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ከህንድ የመንገድ ትራንስፖርት እና የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሚኒስትር ሽሪ ኒቲን ጋዲካሪ ጋር ተወያይተዋል።አምባሳደር ትዝታ በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያና ህንድ መካከል በኢንቨስትመንት፣ በንግድ ፣ በአቅም ግንባታ እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለረጅም ጊዜ ለቆየው ግኑኝነታቸው አድናቆታቸውን ገልፀዋል ።የኢትዮጵያ መንግስት በኢኮኖሚ ውስጥ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማስፈን ለሚያግዘው የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቁልፍ ነው ብሎ እንደሚያምን በዚሁ ወቅት አንስተዋል።የህንድ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚቋቋመው ለስራ እድል መፍጠሪያ ማእከል ግንባታ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፥ ይህ ድጋፍ በተለይም ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት ልማት ዘርፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን መልካምና የቆየ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልፀዋል።የጥቃቅንና፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ በህንድ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልፀው፥ የዚህ ክፍል ልማትና እድገት የገንዘብ አቅምን ከማሳደግ ጀምሮ የስራ እድሎችን ለመፍጠር በጣም ወሳኝ ነው ብለዋል።በዘርፉ ኢትዮጵያ ለምታከናወነው ስራዎች የህንድን ልምድና ተሞክሮ ለማጋራት ቃል ገብተዋል።በተጨማሪም ህንድ ለታዳጊ አገራት የሚመች እና አነስተኛ የካፒታል ወጪን በመጠቀም ምቹ የሆነ መንገድ ለመገንባት የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንዳላት ገልፀው፥ በዚህም ዘርፍ በትብብር ለመስራት ሰፊ እድል እንዳለም ጠቁመዋል ።በመጨረሻም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጎልበት በተጠቀሱት ዘርፎች የሚደረገውን ተሳትፎ አጠናክሮ ለመቀጠል ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ደርሰዋል ።
ህንድ ኢትዮጵያን በጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች
የአዲስ አበባ ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ በቡራዩ ከተማና አካባቢዋ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የአካል ጉዳት፣ ዘረፋና ንብረት እጃቸው አለበት ብለው የጠረጠሯቸው ከሁለት መቶ በላይ ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እያከናወነ የሚገኝባቸው ብርሀኑ ታከለ፣ ሸዋንግዛው ሾሺ፣ መሀመድ ሀሰን፣ መኮንን ለገሰ፣ ጫሚሳ አብዲሳ፣ መንግስቱ ዋቁማ እና ገመቺስ አበረ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ከአዲስ አበባ በተሽከርካሪ በመመላለስ የቡራዩ ግጭትን በማስተባበር፣ በማነሳሳት እና ገንዘብ በማከፋፈል መጠርጠራቸውን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።የጀመረውን ምርመራ ተጨማሪ ሰነዶችን ለማሰባሰብ የ ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲልም ጠይቋል።ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው በጨለማ ቤት ተዘግቶብን ነው ያለነው፤ እየተጉላላን ነው በመሆኑም በዋስ ልንወጣ ይገባል ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።ተጠርጣሪዎቹ የቀረቡበት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ዛሬ ከሰአት በኋላ የሁለቱንም ጉዳይ በማየት ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ የ ቀን ጊዜ ፈቅዷል።የኦሮሚያ ፖሊስ በበኩሉ ጠዋት ስላሳ አምስት ተጠርጣሪዎችን በቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት አቅርቦ የ ቀን ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀባቸው ሲሆን፥ ፍርድ ቤቱም እያንዳንዳቸው የፈፀሙትን ድርጊት በተናጠል እና በዝርዝር መርምሮ ለመስከረም ሀያ አምስት እንዲያቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።መርማሪ ፖሊስ ከሰአት በነበረው ችሎትም ሁለት መቶ ተጠርጣሪዎችን ፋይል የከፈተ ሲሆን፥ ችሎቱ ካለው የቦታ ጥበት አንፃር በየተራ እየተመለከተ ይግኛል።የተጠርጣሪዎች የእምነት ክህደት ቃልንም በመቀበል ላይ ይገኛል።ከቡራዩ ግጭት ጋር ተያይዞ ዛሬን ጨምሮ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው የሚገኙ እና የክልሉ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ስልሳ አራት ደርሷል። ኤፍ ቢ ሲ
በቡራዩ ግጭት ህይወት በማጥፋትና ዝርፊያ በመፈፀም የተጠረጠሩ ከሁለት መቶ በላይ ግለሰቦች ዛሬፍርድ ቤት ቀርበዋል
በቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ፅህፈት ቤት የተገነባው የብርሀን ደባርቅ ሁለትኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።ባህር ዳር፡ ጥር አምስት ሁለት ሺህ አመተ ምህረት አብመድ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ነው ትምህርት ቤቱ የተመረቀው።የቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ፅህፈት ቤት የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማሳደግ በሚያደረገዉ ጥረት በፅህፈት ቤቱ ግንባታቸው ከተጠናቅቁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነዉን በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ያስገነባዉን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬዉ እለት አስመርቋል።ትምህርት ቤቱ በዉስጡ የአስተዳደር ህንፃ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የቤተ መፅሀፍ ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመፀዳጃ ህንፃዎችን ያካተተ ሲሆን ግንባታዉ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።ፅህፈት ቤቱ በዛሬዉ እለት ያስመረቀዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታቸዉ ተጠናቆ ከተመረቁት ስድስተኛው ሲሆን ቀሪዎቹ በቅርብ ቀን በሁሉም ክልሎች እንደሚያስመርቅም ታውቋል።
በቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ፅህፈት ቤት የተገነባው የብርሀን ደባርቅ ሁለትኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
ቮክስ ዋገን በጀርመንኛ የህዝብ መኪና ማለት እንደሆነ ይወሳል። በኢትዮጵያ አገልግሎት በመስጠት አያሌ ዘመናትን አስቆጥራለች። ቅዳሜ ታሀሳስ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ነባሮቹ ጀርመን ሰራሽ አንድ መቶ ሀምሳ የቮክስ ዋገን መኪናዎች ለትርኢት አደባባይ ላይ ወጥተው ነበር። የበርካቶችን ቀልብ ቀልብ ከመግዛት ባለፈ አንዳንዶቹ ከአውቶሞቢሎቹ ጋር ፎቶ ሲነሱም ታይተዋል። የትርኢቱ አካል ከነበሩት ውስጥ፣ ከአርባ አምስት አመታት በፊት መስከረም ሁለት ቀን አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሰባት አመተ ምህረት ከዙፋናቸው የወረዱት ቀዳማዊ አፄ ሀይለ ስላሴ ወደ አራተኛ ክፍለ ጦር የተጓዙባት ቮክስ የተመልካቹን ልዩ ትኩረት አግኝታለች።
የቮክስ ዋገን ትርኢት በአዲስ አበባ
ዘ ሀበሻ በኦስሎ ኖርዌይ ከኦክቶበር ሀያ ሁለት እስከ ኦክቶበር ሀያ ሶስት ሁለት ሺህ አመተ ምህረት በተደረገ የጋራ ጉባኤ አምስት የኢትዮጵያ የብሄር ድርጅቶች በጋራ ለመታገል አዲስ ንቅናቄ መመስረታቸውን ለዘ ሀበሻ በላኩት መግለጫ አስታወቁ። ጥምረቱን የመሰረቱት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሄራዊ ነፃነት ግምባር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ያለውን ስርአት በጋራ ጥለው የሁሉንም ብሄሮች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የሚያከብርና የአንድን ቡድን የበላይነት እንዲያበቃ የሚያደርግ ስርአት ለመፍጠር እንደሚታገሉ በመስራች ጉባኤያቸው መጨረሻ ላይ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ሀገሪቱን ወደ ተሻለ የፖለቲካ ሽግግር ቀርፀው ለመንቀሳቀስ የተሰማሙት እነዚሁ አምስት ድርጅቶች የአዲሱ ጥምረታቸው መጠሪያ የህዝቦች ጥምረት ለነፃነትና ለዴሞክራሲ ተብሎ ተሰይሟል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተሰጠውን መግለጫውን ለማንብብ እዚህ ይጫኑ አርበኞች ግንቦት በቅርቡ ከአማራው ንቅናቋ ከአፋር ንቅናቄና ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጋር በጋራ ለመታገል ጥምረት መፍጠሩ ይታወሳል። ትናንት በኖርዌይ ጥምረታቸውን ያወጁት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሄራዊ ነፃነት ግምባር ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ወደፊት ስለሚፈጥሩት የጋራ ጥምረት ወይም ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው የተገለፀ ነገር ባይኖርም በቅርቡ ወደ ሚኒሶታ የመጡት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ሀላፊ አቶ ነአምን ዘለቀ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንዳለች እስካመኑ ድረስ ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት እንችላለን። ማለታቸውን ዘ ሀበሻ መዘገቧ አይዘነጋም።
አምስት ብሄር ተኮር ነፃ አውጪ ግምባሮች በጋራ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሰረቱ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ ጋር በመተባበር ለእግር ኳስ ዳኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እየሰጠ ነው። ስልጠናው አርብ ሀምሌ ቀን አመተ ምህረት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተነግሯል።ከሰኔ እስከ ሀምሌ ቀን በካፒታል ሆቴል እየተሰጠ የሚገኘው ከፍተኛ የእግር ኳስ ዳኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ላይ ዳኞች ተካፋይ ናቸው። ፌዴሬሽኑ የላከው መግለጫ እንደሚያስረዳው ከሆነ ስልጠናው በየጊዜው እያደገ የመጣውን እግር ኳስ የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ እንዲቀጥል የእግር ኳስ ዳኞች ሚና ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ለዚህም በሙያው ውስጥ የሚገኙ ዳኞች ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተጣጥመው እንዲቀጥሉ በየጊዜው የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ የግድ መሆኑን ይጠቀሳል።በዚሁ መሰረት ስልጠናው በተለያዩ የፅሁፍና የምስል መረጃዎች እንዲሁም በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ እንዲሆን በሙያው ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የፊፋ ባለሙያ በሄንሪኩሰን ካርሎስና በአፍሪካ የደቡብ ዞን የዳኞች ኦፊሰር ማርክ አማካይነት እየተሰጠ ይገኛል። ከአገር ውስጥ ደግሞ የካፍ ኢንስትራክተር አቶ ይግዛው ብዟየሁ በአቶ ግዛቴ አለሙና በአቶ ፈቃዱ ግርማ በረዳት አሰልጣኝነት መካተታቸው ተገልጿል።
ለእግር ኳስ ዳኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና እየተሰጠ ነው
ግዙፉ የውበት እቃዎች አምራች ዩኒሊቨር በመላው አለም ተወዳጅ የሆኑለትን ፌይር ኤንድ ላቭሊ ስምና የማስታወቂያ ሀሳብ ሊቀይር እንደሆነ ይፋ አድርጓል። የምርቱን ስም ለመቀየር የተገደደው በደረሰበት ተቃውሞ ነው። ኩባንያው ከምርቱ ስም ጀምሮ ፌይር ኤንድ ላቭሊ የተሰኙ ምርቶቹ ላይ ቆዳዎ ፈካ እንዲልልዎ የሚለው አባባል ዘረኝነት ነው በሚል ተቃውሞ ቀርቦበለታል። ማስታወቂያው ውስጠ ወይራ ነው። ጥቁር ቆዳ አስቀያሚ፣ ነጣ ያለ ቆዳ ደግሞ የውበት አክሊል ተደርጎ እንዲታሰብ የሚያበረታታ ነው በሚል ነው ቀይር የተባለው። በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የፈረሙበት የተቃውሞ ሰነድ የደረሰው ይህ ግዙፍ ኩባንያ ተወዳጅ የሆኑለትንና ሰፊ ገበያ የነበራቸውን የፌይር ኤንድ ላቭሊ ምርቶቹን ስም ለማስተካከል ቃል ገብቷል። ከምርቶቹ ስም ባሻገር ነጣና ፈካ ያለ ቆዳ የሚለውን አባባል በኢሲያና በአፍሪካ ገበያዎች ላይጠቀም ቃል ገብቷል። እውነት ነው፣ ማስታወቂያዬ ዉበት ፈካ ያለ ቆዳ ብቻ እንደሆነ የሚያመላክት መንፈስ አለው፤ ስለዚህ እቀይራለሁ ብሏል። ኩባንያውን ይህን እርምጃ እንዲወስድ ሺህ ሰዎች የተቃውሞ ፊርማ አኑረዋል። ከተቃዋሚዎች አንዷ ለሚዲያ እንደተናገረችው ይህ ኩባንያ በዘረኝነት ውስጥ ገንዘብ ሲያጋብስ ነው የኖረው፤ ጥቁር ቀለምን ሲያንኳስስ ነው የኖረው፣ ዉበት ቅላት ብቻ እንደሆነ ውስጥ ውስጡን ሲሰብከን ነው የኖረው ብላለች። ሌላ ተቃዋሚ ደግሞ ድርጅቱ ጥቁር በመሆናችን ውብ ለመሆን እንደማንመጥን ነበር ለዘመናት የሚነግረን ብላለች። የዩኒሊቨር ፕሬዝዳንት ሰኒ ጄን ከዚህ በኋላ ምርቶቻችን ሁሉንም የቆዳ ቀለም ያማከሉና አካታች እንዲሆኑ እንጥራለን፤ የቆዳ ቀለም ብዝሀነትን እናደንቃለን ብለዋል። እውቋ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና የመብት ታጋይ ፑርና ቤል ታዲያ ይህ የኩባንያው ምላሽ አስቆጥቷታል። ፑርና ዩኒሊቨር በይቅርታ ብቻ ነገሩን አድበስብሶ ማለፉ የሚያንገበግብ ነው ብላለች። እንደርሷ አመለካከት ኩባንያው ያጋበሰው ትርፍ ከዘረኝነት የተገኘ በመሆኑ ካሳ መክፈል ይኖርበታል። ምርቶቹም ከእንግዲህ በጭራሽ ወደ ገበያ መውጣት የለባቸውም። ኩባንያው በዘመናት ያደረሰው ጉዳት ቁሳዊ አይደለም። የሚሊዮን ጥቁሮችን ስሜት ጎድቶታል፤ ይቅርታ ብቻ ብሎ ማለፉ ያንገበግበኛል ብላለች ፑርና ቤል። የጆርጅ ፍሎይድ በነጭ ፖሊስ የግፍ መገደልን ተከትሎ በተቀጣጠለ የፀረ ዘረኝነት ተቃውሞ በርካታ ግዙፍ ኩባንያዎች ለነበራቸው መጥፎ የረዘኝነት ታሪክ ሳይቀር ይቅርታ እየጠየቁ ነው። ከዚህ ቀደም ሁለት የእንግሊዝ ግዙፍ ኩባንያዎች ከባሪያ ንግድ ጋር በተሳሰረ መጥፎ ታሪካቸው ጥቁሮችን ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ደግሞ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ስመ ጥር ትምህርት ቤቶች አንዱ የሆነው ኢትን ኮሌጅ የመጀመርያውን የትምህርት ቤቱን ጥቁር ተመራቂ ናይጄሪያዊ ደራሲ ላይ ላደረሰው ስውር የዘር ጥቃት በይፋ ይቀርታ መጠየቁ አይዘነጋም።
ግዙፉ የቆዳ ቅባት አምራች ዩኒሊቨር ጥቁር ቆዳዎ ፈካ እንዲልልዎ የሚለው ማስታወቂያው ተቃውሞ ገጠመው
ጥር ፲፭ አስራ አምስት ቀን ፳፻፮ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና ኮሚሽኑ ተጠርጣሪዎቹ የተሳሩት በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለከተሞች በመኪና ስርቆት፣ ማጅራት በመምታትና ሌሎች ወንጀሎች መፈፀማቸውን ጥናት ካካሄድኩ በኋላ ነው ብሎአል። ተያዙ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ፍድር ቤት ስለመቅረባቸው ኮሚሽኑ ያስታወቀው ነገር የለም። በአዲስ አበባ ውስጥ ከጊዜወደ ጊዜ ሚታየው ስርቆት ነዋሪዎች ማስመረሩን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በከተማዋ ውስጥ ዘመናዊ ስለኮችን በአደባባይ መያዝ፣ ውድ ጌጣጌጦችን አድርጎ መጓዝ አደጋ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ፖሊስ እስከዛሬ ዝም ብሎ ቆይቶ አሁን አርምጃ መውሰዱን ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር ሲያይዙት ሌሎች ግን ቢረፍድም ይሻላል ይላሉ። ዘጋቢያችን እንደሚለው አንድአንድ አስተያየት ሰጪውም መንግስት በመጪው ምርጫ ሁከት ይፈጥራሉ ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች በወንጀለኛ ስም ማሰር መጀመሩም ሊሆን ይችላል በማለት አስተያየት ይሰጣሉ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሁለት መቶ ሀምሳ በላይ ሰዎችን አሰረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት አራት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሩሲያ የቀድሞው የማረሚያ ቤት አገልግሎት ሀላፊ ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን ማጥፋቱ ተነግሯል። ቪክቶር ስቪሪዶቭ የተባለው ግለሰብ የሩሲያ ማረሚያ ቤት አገልግሎት የሞተር ትራንስፖርት ክፍል ሀላፊ ሆኖ በሚያገለግልበት ወቅት አንድ መቶ ሀያ አምስት ሺህ ዶላር ከምክትል ዳይሬክተሩ ተቀብሏል በሚል ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል። ይህን ተከትሎም በተላለፈበት የሶስት አመት የእስር ቅጣት ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን አጥፍቷል። የፍርድ ቤቱ ዳኛ ግለሰቡ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወሰድ ትእዛዝ ባስተላለፉበት ቅፅበት ግለሰቡ በግንባሩ ላይ በመተኮስ ራሱን ማጥፋቱ ተገልጿል። የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ ራሱ ያጠፋበትን የጦር መሳሪያ ወደ ፍርድ ቤት ይዞ ሳይመጣ አይቀርም ብለዋል። ፖሊስም ግለሰቡ ራሱን ማጥፋቱን ተከትሎ በፍርድ ቤቱ የፀጥታ አካላት ላይ ምርምራ መጀመሩ ተጠቁሟል። የካንሰር ህመምተኛ እንደሆነ የተነገረው ግለሰብ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት በቤት ውስጥ እስር ላይ እንደነበረ ነው የተነገረው። ምንጭ፡ ቢቢሲ ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የሩሲያ የቀድሞው የማረሚያ ቤት ሀላፊ ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን አጠፋ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ሀያ ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ ። በዛሬው እለት የአርባ ምንጭ፣ የሀዋሳ፣ የወላይታ ሶዶ፣ የዲላ፣ የጂንካ፣ የአዲግራት፣ወራቤ፣ ወሎ፣ ደብረ ብርሀን፣ ወልድያ እና እንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን የቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል። በዚህም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሀ ግብር በተለያዩ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ስምንት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ተማሪዎችን አስመርቋል። ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ከአራትሺህ ስምንት መቶ በላይ ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል። ዲላ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛ ቅድመ ምረቃ መርሀ ግብር ያሰለጠኗቸውን ሁለትሺህ ሶስት መቶ ሀምሳ ስድስት ተማሪዎችን ማስመረቁን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ። እንዲሁም አዲ ግራት ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና ድህረ ምራቃ ያሰለጠናቸውን ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል። በተመሳሳይ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያስተምራቸው የቆዩ አንድሺህ አንድ መቶ ተማሪዎችን አስመርቋል። በተጨማሪም በአማራ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ወሎ፣ደብረ ብርሀን፣ወልድያ እና እንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮችያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል። እንዲሁም አምቦ እና ሀረማያ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ማስመረቃቸውን ዘገባው አመላክቷል። ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የሙያ መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ሁለትሺህ አንድ መቶ ተማሪዎች አስመርቋል። በጎህ ንጉሱ ፣ማቲዎስ ፈለቀ፣ ኢብራሂም ባዲና ኤርሚያስ ቦጋለ
ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት አንድ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የችግኝ ዝግጅት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ። በግብርና ሚኒስቴር ብሄራዊ የአረንጓዴ አሻራ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አደፍርስ ወርቁ ዶክተር እንደገለፁት በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ስድስት ነጥብ አምስት ቢሊየን ችግኞችን ለማዘጋጀት ርብርብ እየተደረገ ነው። የዝግጅቱ ስልሳ በመቶ ለፍራፍሬ፣ ለመኖና ለአፈር ለምነት ጥበቃ ጠቀሜታ ባላቸው ችግኞች ላይ ሲሆን አርባ በመቶው ዝግጅት ደግሞ ለውበትና ለደን ልማት አገልግሎት በሚውሉ ችግኞች ላይ ትኩረቱን ማድረጉን ገልፀዋል። በእስከ አሁኑ ሂደትም በአንድ መቶ ሁለት ሺህ የመንግስት፣ የግልና የህብረት ስራ ማህበራት የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል። እየተዘጋጁ ከሚገኙ ችግኞች መካከል ስድስት ነጥብ ሶስት ቢሊየን የሚሆነው ተቆጥሮ ለተከላ እየተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት ሰብሳቢው ይህም በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከታቀደው በላይ ችግኝ እንደሚዘጋጅ አመለካች መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም ለችግኝ ተከላ የሚውል አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊየን ሄክታር መሬት ለመለየት የታቅዶ እስከ አሁን ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ሄክታር መሬት መለየቱን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል። በአጠቃላይ የችግኝ ዝግጅቱና የተከላ ቦታ ልየታ ከዘጠና በመቶ በላይ መጠናቀቁንም አመልክተዋል።
ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የችግኝ ዝግጅት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ
በአማራ ክልል የሚገኙ አራት ዞኖች የመሰረተ ልማት አውታሮች ችግሮች እንዳለባቸው አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማርያም ደሳለኝ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች ባወያዩበት ወቅት፣ ነዋሪዎቹ በዋናነት የመንገድ፣ የኤሌክትሪክና የትምህርት ተቋማት ችግሮች እንዳሉባቸው ገልፀዋል። የካቲት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት በኮምቦልቻ ከተማ በተካሄደው ውይይት ላይ ከሰሜን ሸዋ፣ ከደቡብ ወሎ፣ ከሰሜን ወሎና ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የተወከሉ ነዋሪዎች፣ የመሰረተ ልማት አለመሟላት ኑሮአቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። ከደቡብ ወሎ ባሉካ ወረዳ ተወካይ የሆኑት አቶ ሀይለ ማርያም አሰፋ በግብርናና በንግድ ስራ ይተዳደራሉ። አቶ ሀይለ ማርያም እንዳሉት፣ ለወፍጮ ቤታቸው የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለማስገባት ክፍያ የፈፀሙት በሁለት ሺህ ሶስት አመተ ምህረት ነው። ነገር ግን ባለፉት አራት አመታት ቆጣሪው አልገባላቸውም። ገንዘቡም ያለ ወለድ ታስሮ ቀረብኝ ብለዋል። አቶ ሀይለ ማርያም ከእሳቸው በተጨማሪ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎችም ይህ ችግር ገጥሟቸዋል ብለዋል። አንድ ወዳጃቸው ትራንስፎርመር ለማስገባት ሁለት መቶ ሺህ ብር ከፍሎ ቢጠብቅም ትራንስፎርመሩ የውሀ ሽታ ሆኖ መቅረቱን አስረድተዋል። ከብዙ ቆይታ በኋላ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ሀላፊዎች እቃዎቹ በቀድሞ ዋጋ ስለማይገኙ ገንዘብ ጨምሩ ብለዋል ሲሉ አቶ ሀይለ ማርያም ተናግረዋል። እኔ ተጨማሪ ስልሳ ሺህ ብር፣ ወዳጄ ተጨማሪ አንድ መቶ ስላሳ ሺህ ብር እንድንከፍል ተጠይቀናል። ይህ ችግር የተፈጠረው በመንግስት ሆኖ እያለ ለምን እኛ እንጠየቃለን በማለት አቶ ሀይለ ማርያም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል። ከአራቱም ክልሎች የመጡ ተወካዮች ተመሳሳይ የኤሌክትሪክ ችግር እንዳለባቸው ጠቅሰው፣ በተጨማሪም የሀይል አቅርቦት ችግር እንደገጠማቸው ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ጎልተው ከተነሱ ችግሮች መካከል የገጠር መንገዶች ለረዥም ጊዜ በማገልገላቸው ምክንያት፣ ከጥቅም ውጪ መሆናቸውንና በአንዳንድ ቦታዎች መንገዶች በክረምት ተሽከርካሪዎችን የማያስተናግዱ በመሆኑ፣ እንዲሁም ጭራሹኑ የመንገድ አውታር የሌላቸው የምስራቅ አማራ አካባቢዎች እንዳሉ ተጠቁሟል። ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ከሚሴ ከተማ የተወከሉት ግለሰብ እንዳሉት፣ ዞኑ ሰባት ወረዳዎች አሉት። እነዚህ ወረዳዎች በሙሉ ከአፋር ብሄራዊ ክልል ጋር ይጎራበታሉ። በእነዚህ አካባቢዎች ያሉት መንገዶች በክረምት ጥቅም የማይሰጡ በመሆናቸው፣ ከባድ ችግር እንደሆነባቸው ጠቁመዋል። አካባቢው በአሁኑ ወቅት ከምንጊዜውም የተሻለ ፀጥታ ቢኖረውም፣ ምናልባት የፀጥታ ችግር ቢነሳ ችግሩን ለመፍታት አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጠር በመሆኑ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪ የአፋርና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች አብረው እንደሚማሩ፣ ወደፊት መጋባት ሊኖር ስለሚችልና ይህም የአካባቢውን ሰላም የሚያሳድግ በመሆኑ፣ ለማሀበራዊ ግንኙነቱም ቢሆን የመንገዶቹ መገንባት ጠቃሚ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሁለት ሺህ አንድ አመተ ምህረት አካባቢውን በጎበኙበት ወቅት ከጎንጎፍቱ፣ መራኛ፣ አለም ከተማ ደጎሎ ድረስ ያለው መንገድ እንደሚገነባ ተስፋ ሰጥተው እንደነበር ያስታወሱት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ መንገዱ እስካሁን አለመገንባቱን ተናግረዋል። ከእነዚህ ችግሮች በተጨማሪ አንዳንድ ዞኖች ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገነቡላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። ከነዋሪዎች የተነሱትን ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበጎ መመልከታቸውን ጠቅሰው ምላሽ ሰጥተዋል። የመንገድ ግንባታን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፣ የመጀመሪያው የገጠር ቀበሌዎችን ማገናኘት ነው ብለው፣ ይህ ፕሮጀክት በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በመቶ ቢሊዮን ብር ወጪ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ኪሎ ሜትር ለመገንባት መታቀዱን ገልፀዋል። በዚህ እቅድ አማራ ክልል እስካሁን ሰባት ሺህ ኪሎ ሜትር መንገድ መገንባቱን፣ ሁሉንም መንገዶች በአንድ ጊዜ በአስፓልት ደረጃ ማሳደግ የማይቻል በመሆኑ በሂደት ወደ አስፓልት ደረጃ እንደሚያድግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል። ቃል ተገብተው ያልተገነቡ መንገዶችን በሚመለከትም፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የመዘገበው በመሆኑ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ እንዲካተት በቅርብ እንደሚከታተሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ገብተዋል። ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎችን በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ፣ የኮሌጆችን ግንባታ የሚመለከታቸው ክልሎች ናቸው ብለዋል። ዩኒቨርሲቲዎችን በሚመለከት ኢትዮጵያ ብዙ ዩኒቨርሲቲዎችን በፍጥነት በመገንባት የሚተካከላት የለም። ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ አገሪቱን ሲቆጣጠር አንደኛውን ኮሌጅ ማለት ይቀላል ሀሮማያ ግብርና ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ይሰየም እንጂ፣ ግብርና የሚያስተምር ኮሌጅ ነበር። ከዚያ ተነስቶ መንግስት በአስር አመት ውስጥ ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች አደራጀ። ከዚያም ባለው አምስት አመት ዩኒቨርሲቲዎች አደራጀ። ከዚያ ቀጥሎ ባለው ወሎ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በአገር ደረጃ አስር ዩኒቨርሲቲዎች አደራጀ። በሚቀጥለው አምስት አመት ደግሞ ዩኒቨርሲቲዎችን ለማደራጀት አቅዷል። ቀደም ሲል አንድ ዩኒቨርሲቲ ለአምስት ሚሊዮን ሰው ነበር። ሁለተኛው ዙር ሲጀመር አንድ ዩኒቨርሲቲ ለሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሰው ነበር፣ ሶስተኛው ዙር ላይ አንድ ዩኒቨርሲቲ ለሶስት ሚሊዮን ነበር። ከአምስት አመት በኋላ አንድ ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሰው እንዲደርስ እናደርጋለን። በዚህ መሰረት ነው የምንጓዘው፤ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ምስራቅ አማራም የዚሁ እቅድ አባል ከመሆኑም በተጨማሪ ለዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎለታል። ሌላው የኤሌክትሪክ ጥያቄ ነው። የኤሌክትሪክ ጉዳይ የትራንስፎርመርና የቆጣሪ ብቻ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በእርግጥ እናንተ የሚመለከታችሁ የትራንስፎርመርና የቆጣሪ ነው፤ ብለዋል። እንደ ተጠቃሚ ነዋሪዎቹ ጥያቄው ትክክል መሆኑን አቶ ሀይለ ማርያም ገልፀው፣ ጉዳዩ እንደ መንግስት ሲታይ ዋናው ችግር እስካሁን የተዘረጉት መስመሮች እነዚህን ቆጣሪዎችና ትራንስፎርመሮች የመጠቀም አቅም በውስጣቸው ስለሌለ ነው ብለዋል። የመጀመሪያው ስራ ትራንስፎርመሩ ዝም ብሎ ቢተከል ስራችሁን ይረብሻል። እንዲሁም ከእናንተ ጋር የበለጠ እንጣላለን። ቆጣሪ ተክለን ኤሌክትሪክ ካልሰጠን የበለጠ እንጣላለን፤ ሲሉ አቶ ሀይለ ማርያም ለነዋሪዎቹ ተወካዮች አስረድተዋል። አሁን እያደረግን ያለነው ሰብስቴሽኖችን በፍጥነት መስራት ነው። ህዝብ እየታገሰን፣ ሰብስቴሽኖችን እንስራ ብለን ከውጭ እቃ እያመጣን ነው፤ በማለት አስረድተዋል። ነገር ግን እነዚህ ችግሮች በሌሉባቸው አካባቢዎች ትራንስፎርመርና ቆጣሪ ያልገጠሙ እንዳሉ ደርሰንበታል። ይኼ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት መስሪያ ቤት ችግር ነው። ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር እንፈታለን፤ በማለት ችግሩን ለመፍታት ከአዲስ አበባ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ሀይለ ማርያም፣ በቀጣይነት ወደ ክልልና ዞን ከተሞች እንደሚሸጋገር አስታውቀዋል።
የአማራ ክልል ነዋሪዎች የመሰረተ ልማት ችግሮች ኑሮአችንን አክብደውታል አሉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት ሀያ ሶስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ በአንድ መቶ ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በ ኮካ ኮላ መጠጦች አፍሪካ ኢትዮጵያ ኩባንያ የተገነባው የኮካኮላ ምርት ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ። ፋብሪካው የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የተቋሙ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው። ኩባንያው ላለፉት ስድስት አስርት አመታት በኢትዮጵያ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከስላሳ ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ የስራ እድል መፍጠሩም ተመላክቷል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ ባለፉት ስልሳ ሁለት አመታት በኢንዱስትሪ ዘርፍ የማይተካ ሚና አበርክቷል ብለዋል። መንግስት በኢንዱስትሪ ዘርፍ ያሉ ማነቆዎችን በመፍታት ዘርፉን ለማጎልበት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው በክልሉ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የተሰሩ ስራዎች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ገልፀዋል። ክልሉ ኩባንያው እያከናወናቸው ላሉ የልማት ስራዎች የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ የኮካኮላ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳሬል ዊልሰን ድርጅቱ ባለፉት አምስት አመታት ከሶስት መቶ ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ በመመደብ የተለያዩ የማስፋፋፊያ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ የተመረቀው ፕሮጀክትም የዚሁ አካል መሆኑን አመላክተዋል። በሰበታ ከተማ የተመረቀው ፋብሪካ ኮካኮላ ምርት ከሚያመርትባቸው ፋብሪካዎች አምስትኛው ቅርንጫፍ መሆኑም ተገልጿል። በዛሬው እለት የተመረቀው የኮካ ኮላ ማምረቻ ፋብሪካ ኮካ ኮላ ቢቭሬጅስ አፍሪካ ኢትዮጵያን በአመት ከአንድ መቶ ሚሊየን በላይ እሽግ ለስላሳ ለማምረት ያስችለዋል ተብሏል። በተጨማሪም የማምረቻ ግብአቶችን እንደ የፕላስቲክ ጠርሙስ እና ክዳን እንዲሁም ሌሎች የምርት ግብአቶችን በማምረት ከውጪ ወደ ሀገሪቷ የሚገቡ ምርቶችን በመቀነስ እንደሚኒት ሜዲ ጁስ የመሳሰሉ አዳዲስ ምርቶችን ሀገር ውስጥ በማምረት ጠቅላላ ምርት ለመጨመር እንደሚረዳም ነው የተገለፀው። ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን ይመልከቱ ፡ የሚመረቱት የግብአት ምርቶቹ የሲ ሲ ቢ ኤን ፍላጎት ከማሳካት በተጨማሪ ለውጪ ገበያ በማቅረብ የውጨ ምንዛሬን ሀገሪቷ እንድታገኝ እና በዘርፉ ያለውን የምርት እጥረት ለመፍታት ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብም ፋብሪካው እቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል ተብሏል። በሀብታሙ ተ ስላሴ
በሰበታ በአንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው የኮካ ኮላ ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ
ሰሞኑን በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የሱርማ ብሄረሰብ አባላት በፖሊስ እስርና እንግልት እንደደረሰባቸው የሚያመለክቱ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲሰራጭ የሰነበተ ሲሆን የክልሉ መንግስት ጉዳዩን በስፋት ማጣራቱን ጠቁሞ የተባለው ኢ ሰብአዊ ድርጊት አለመፈፀሙን አረጋግጫለሁ ብሏል። በዞኑ ተፈፅሟል ተብሎ ሲናፈስ የነበረውን ኢ ሰብአዊ ድርጊት በተመለከተ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እስከ ስር አመራር ድረስ የዘለቀ ፍተሻና ግምገማ ማካሄዱን ለአዲስ አድማስ የገለፁት የክልሉ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን፤ በተደረገው ማጣራትም መረጃው ትክክል አለመሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል። እንዲህ ያለውን ድርጊት የፈፀመ የፖሊስ አባል እንደሌለ አረጋግጠናል ያሉት የክልሉ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ፤ አርብቶ አደሮቹ ለስኳር ፕሮጀክት የመሬት ማስፋፊያ በሚል መሬታቸው መነጠቁን በመቃወማቸው ኢ ሰብአዊ ድርጊቱ ተፈፅሞባቸዋል የሚለውም ፈፅሞ ሀሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል። በዞኑ እየተሰራ ያለው የ ኩራዝ ስኳር ፕሮጀክት ሰማኒያ አምስት በመቶ መጠናቀቁን በመግለፅም በአሁን ወቅት ምንም አይነት የመሬት ማስፋፋትም ሆነ የመሬት ጥያቄ እንደሌለ ጠቁመዋል። ፕሮጀክቱ ሲጀመር አርብቶ ስለጉዳዩ ሰፊ ግንዛቤ እንዲይዝ መደረጉንና ለፋብሪካው ግብአት የሚሆን የአገዳ ልማት ላይ እንዲሰማራ መደረጉን የጠቆሙት ሀላፊዋ፤ እንደውም የመስኖም ሆነ የውሀ ተጠቃሚ ለመሆን ችሏል፤ በዚህም ህይወቱ እየተቀየረ ነው ሲሉ አስረድተዋል። የመከላከያ ሀይሉም ሆነ የክልሉ ልዩ ሀይል በተባለው ድርጊት ውስጥ አልተሳተፉም፣ የመሬት ጥያቄም አልተነሳም ብለዋል ሀላፊዋ።
ክልሉ በሱርማዎች ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ኢ ሰብአዊ ድርጊት አስተባበለ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር ሀያ አንድ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ መንግስት አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ለመድረስ ከአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በሶስት አቅጣጫ ኮሪደር ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ እያጓጓዘ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስትና በህወሀት መካከል በፕሪቶሪያ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ መንግስት ቃል የገባውን በትግራይ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትና የመልሶ ግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛልም ነው ያለው። ባለፉት አራት ቀናትም ዋና ዋና የሰብአዊ ድጋፍ በተለያየ አቅጣጫ እያቀረብ እንደሚገኝም ነው የገለፀው። በዚህም በጎንደር ኮሪደር ህዳር ከጎንደር በሁመራ በኩል ወደ ሽረ አንድ ሺህ አንድ መቶ ስላሳ ሰባት ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል የጫኑ ስላሳ የአለም ምግብ ፕሮግራም የጭነት መኪኖች የተላኩ ሲሆን፥ በተጨማሪም ሁለት መቶ ሜትሪክ ቶን እህል የጫኑ አስር የጭነት መኪኖች ከጎንደር ወደ ማይፀብሪ መጓዛቸውንም አስታወቋል። ከዚህ ባለፈም ህዳር ቀን የአለም ምግብ ፕሮግራም በሀያ አራት መኪኖች አንድ ሺህ አርባ ሶስት ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል ከጎንደር ወደ ሽረ ሲላክ፥ ህዳር ቀን ከሽረ ወደ ማይፀብሪ የእርዳታ እህል የሚያጓጉዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች እየተጫኑ መሆኑንም ገልጿል። ህዳር ሀያ ቀን ሶስት መቶ ሰማኒያ ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍ የጫኑ የአለም ምግብ ፕሮግራም የጭነት መኪኖች ከጎንደር ወደ ማይፀብሪ ዲማ መላካቸውን በመጥቀስም፥ ከጎንደር ወደ ሽረ የምግብ ድጋፍ ያደረሱ ዘጠኝ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ጎንደር ተምለሰዋልም ነው ያለው። እንዲሁም በኮምቦልቻ ኮሪደር ህዳር ቀን ከኮምቦልቻ የተነሱ ስድስት መቶ ሀያ ስድስት ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍን የጫኑ ሀያ ሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎች ዛታ የደረሱ ሲሆን፥ ህዳር ቀን የአለም ምግብ ድርጅት ሀምሳ አራት የምግብ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከኮምቦልቻ ተነስተው ወደ ኦፍላ፤ ራያ አላማጣ መድረሳቸውም ተገልጿል። ህዳር ቀን በደቡባዊ ዞን ውስጥ ለሚገኙት ባላ፣ ኮረምና ሌሎችም ወረዳዎች የሚላክ የምግብ እህል ጭነት እየተካሄደ መሆኑንም ነው አገልግሎቱ የጠቀሰው። በሰመራ ኮሪደርም ህዳር ቀን ስላሳ አራት የተለያየ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቐለ የደረሱ ሲሆን፥ ሰባ ሰባት ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ፣ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሀያ ሶስት ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል እንዲሁም ዘጠና አምስት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሁለት ሊትር ነዳጅ መቐለ ደርሰዋል ብሏል። ህዳር ቀን በካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ በኩል የተላኩ በድምሩ አንድ መቶ ሰባ አምስት መኪኖች መቐለ ሲደርሱ፥ ህዳር ሀያ ቀን የምግብ ድጋፍ የጫኑ አንድ መቶ አርባ ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ መቐለ ጉዞ መጀመራቸውንም ነው ያስታወቀው። ከዚህ በተጨማሪም ህዳር ሀያ ቀን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ የአየር በረራ አገልግሎት በኩል ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የመንገደኞች የአውሮፕላን በረራ መከናወኑንም በመግለጫው አመላክቷል። ህዳር ሀያ አንድ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት አዲስ አበባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
በሶስት አቅጣጫ ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ እየተጓጓዘ ነው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የአዲስ አበባ ከተማ የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ አንድ አመት ሙሉ ሲያጨቃጭቅ የነበረውን ሁለት መቶ ሀያ ሺህ ሜትሪክ ቶን አርማታ ብረት ግዥ ጨረታ፣ እንዲሁም ለአቅራቢዎች ሰጥቶት የነበረውን የሶስት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለውን አቅርቦት መሰረዙን አስታወቀ።በሀምሌ ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት ኢንተርፕራይዙ ሶስት የአገር ውስጥ አምራቾች ሶስት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር የሚያወጣ የአርማታ ብረት ለሚገነባቸው የአርባ ስልሳ ቤቶች እንዲያቀርቡለት ተስማምቶ ነበር።በዚህም መሰረት መጀመርያ ጨረታውን ላሸነፉ አቅራቢዎች እገዛዋለሁ ብሎ ተዋውሎት የነበረውን ሁለት መቶ ሀያ ሺህ ሜትሪክ ቶን ብረት መጠን ዘጠና በመቶ በመቀነስ ወደ ሀያ ሺህ ሜትሪክ ቶን ማድረሱ ታውቋል። በተጨማሪም እነዚህን አቅራቢዎች ከአመት በፊት በሰጡት ዋጋ ብረቶቹን እንዲያቀርቡ ኢንተርፕራይዙ ማሳወቁን፣ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢንተርፕራይዙ ሀላፊዎች ተናግረዋል።ነገር ግን አቅራቢዎቹ መልስ ባለመስጠታቸው ኢንተርፕራይዙ ጨረታውንም ሆነ እንዲያቀርቡ ሰጥቷቸው የነበረውን እድል መሰረዙን አሳውቋል። ብዙ ውጣ ውረዶችን ያለፈው ይህ የጨረታ ሂደት በርካታ ማስተካከያዎችና ማሻሻያዎች እንደተደረጉበት ይታወሳል።በግንቦት ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት ወጥቶ በነበረው በዚህ ጨረታ ወደ አምስት የሚጠጉ የአገር ውስጥ የአርማታ ብረት አምራቾች ተሳትፈው የነበረ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ሶስት የአገር ውስጥ አምራቾች በተለያየ መጠን ወጥቶ የነበረውን የብረት ግዥ ለማቅረብ ተስማምተው ነበር።በዚሁ ጨረታ ላይ ማስተካከያ ሲደረግ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በመጀመሪያ ኢንተርፕራይዙ አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ቶን ለመግዛት ጨረታ አውጥቶ ተመሳሳይ የአገር ውስጥ አምራቾች ተሳትፈው የነበረ ሲሆን፣ የሚያቀርቡበትንም ዋጋ በማሳወቅ በኢንተርፕራይዙ የጨረታ ኮሚቴ የተገመገመ ቢሆንም፣ ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በመሰረዝ አሻሽሎ አውጥቶታል።በመጨረሻ ኢንተርፕራይዙ ሁለት መቶ ሀያ ሺህ ሜትሪክ ቶን ለመግዛት እንደሚፈልግ አሳውቆ ነበር። በዚህም መሰረት ሲኤንድኢ ወንድማማቾች የብረት ፋብሪካ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሀበር ለአብዛኞቹ የብረት መጠኖች ዝቅተኛውን ዋጋ አቅርቧል። ለ ፣ ለ ፣ ለ እንዲሁም ለሀያ ሚሊ ሜትር ብረቶች ለእያንዳንዱ ኪሎ ግራም ነጥብ ሰባትአንድ ብር፣ ነጥብ አንድአንድ ብር፣ ነጥብ አንድአንድ ብር እንዲሁም ነጥብ ሁለትአራት ብር ዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ ጨረታውን አሸንፏል። በአጠቃላይ ኩባንያው ወደ ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ዋጋ አቅርቦ ጨረታውን አሸንፎ ነበር።በመቀጠል ኢስት ስቲል የተባለው ፋብሪካ ከተወዳደረባቸው የብረት መጠኖች ወደ ስላሳ ዘጠኝ ነጥብ አራት ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚመዝኑ የስምንትና የአስር ሚሊ ሜትር ብረቶችን ለማቅረብ፣ ሰባት መቶ ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር በማቅረብ አሸንፎ ነበር።ሌላው ሶስተኛው አሸናፊ ስቲሊ አርኤምአይ ሲሆን፣ ይህ አቅራቢ አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ኪሎ ግራም አጠቃላይ ክብደት ያላቸውን አርማታ ብረቶች እያንዳንዱን ኪሎ ግራም በሀያ ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ብር ለማቅረብ ተስማምቶ ነበር።ይህ አንድ አመት የፈጀው ጨረታ በወቅቱ ግንባታ ላይ ለነበሩ ስላሳ ስምንት ሰባት መቶ ዘጠና ቤቶች፣ እንዲሁም አዲስ ይጀመራሉ ተብለው ለሚጠበቁ ቤቶች ታስቦ የተደረገ ግዥ ነበር።ነገር ግን በወቅቱ ኢንተርፕራይዙ ባጋጠመው የበጀት እጥረትና ቀድሞ የነበረው ለተቋራጮች ሲደረግ የነበረው የአከፋፈል ስርአት በመቀየሩ፣ የአርማታ ብረቱን አሸናፊዎቹ እንዲያቀርቡ ስምምነት ከተደረገ በኋላ ሳይፈፀም ቀርቷል።በተቃራኒው ኢንተርፕራይዙ የአርማታ ብረቶቹን ማስረከቢያ ጊዜ እስከ ሰኔ ስላሳ ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ማራዘሙ ይታወሳል። ነገር ግን አሁን ይህን ውሳኔ ኢንተርፕራይዙ በመከለስ፣ ውሳኔውን ካሁን ቀደም ጨረታውን ላሸነፉት ኩባንያዎች አሳውቋል። አሁን ያለን ፍላጎትም ሆነ የገንዘብ አቅም እስከ ሀያ ሺህ ቶን አርማታ ብረት ብቻ ለመረከብ የሚያስችለን ነው፤ ሲሉ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢንተርፕራይዙ ሀላፊ ተናግረዋል። ከአሁን በኋላ ያለን አማራጭ አዲስ ጨረታ ማውጣት ነው፤ ሲሉ ሀላፊው አክለዋል። ኢንተርፕራይዙ አቅራቢዎቹ ከአመት በፊት ሰጥተውት በነበረው ተመሳሳይ ዋጋ እንዲያቀርቡ ቢፈልግም፣ በአለም አቀፍ ደረጀ የአርማታ ብረት ዋጋ መጨመሩ ይታወቃል። በዚህም መሰረት እንደ ለንደን ሜታል ኤክስቼንጅ አይነት የብረትን ዋጋ በአለም አቀፍ ደረጃ በመተንተንና በመተንበይ፣ እንዲሁም በማገበያየት የሚታወቁ ተቋማት የአርማታ ብረት ካለፈው አመት የተወሰነ ጭማሪ እንዳሳየ ያመለክታሉ።በዚህም መሰረት እ ኤ አ በሁለት ሺህ በኪሎ ከዘጠኝ ነጥብ አንድአራት ብር እስከ አስር ነጥብ አንድ ብር ሲሸጥ የነበረው፣ በዚህ አመት እ ኤ አ እስከ ግንቦት ሁለት ሺህ ድረስ እስከ አስር ነጥብ ሰባትአምስት ብር በኪሎ እየተሸጠ ነው።በአሁኑ ወቅት በአርባ ስልሳ ፕሮጀክት ከሚሰሩ ቤቶቸ አንድ ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ቤቶች መጠናቀቃቸው ቢነገርም፣ እስካሁን ወደ ቆጣቢዎች አልተላለፉም። ወደ አንድ መቶ ስልሳ አራት ሺህ የሚሆኑ ቤት ፈላጊዎች በዚህ ፕሮግራም ተመዝግበው ይገኛሉ። ለቀጣይ በጀት አመት አዳዲስ ቤቶች ይገነባሉ ወይ የሚለው ገና እንዳልተወሰነበት ሀላፊው ለሪፖርተር ገልፀዋል።
ለአንድ አመት ሲያጨቃጭቅ የቆየው የሶስት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር አርማታ ብረት የጨረታ ግዥ ተሰረዘ
በምእራብ ወለጋ እንዲሁም በምስራቅ ጉጂ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እርምጃ በመወሰድ ላይ ነው። ኢሳት ዜና ጥቅምት ቀን አመተ ምህረት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለፁት ካለፈው አርብ ጀምሮ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ላይ የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በብዙ ታጣቂዎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሷል። የኦነግ ወታደሮችን ትጥቅ መፍታት የተቃወሙ ወጣቶች በየአካባቢው የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያደርጉ ሰንብተዋል። በምእራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውጥረቱ ዛሬም ድረስ መቀጠሉን ያነጋጋርናቸው የአይን እማኞች ገልፀዋል።በምእራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ እና ዱጋ ዳዋ ወረዳዎች የኦነግ ደጋፊ ቄሮዎችና የመንግስት ወታደሮች የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውንና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኦነግ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን እንዲሁም ከመከላከያም የተጎዱ ወታደሮች እንዳሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።ሁኔታው ያሳዘናቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ የወጣቶች ድርጊት በጣም እንዳሳዘናቸው ወጣቶቹ የመረጡት የትግል ስልት ስህተት መሆኑንና ጫካ የገቡ ወጣቶች እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።በጉዳዩ ዙሪያ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የክልሉ ምክትል የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ እንደሚሉት ትጥቃቸውን ያልፈቱ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተጀመረው እንቅስቃሴ መቀጠሉን ገልፀው ከዚህ ውጭ ግን በክልሉ ከኦነግ ሰራዊት ጋር ጦርነት እየተካሄደ እንደሆነ የሚዘገበው ትክክል አይደለም ብለዋል።
በምእራብ ወለጋ እንዲሁም በምስራቅ ጉጂ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እርምጃ በመወሰድ ላይ ነው።
ከፍተኛ የአመራር አባሉ አቶ አብረሀ ደስታ ባለፈው ሳምንት መቀሌ ውስጥ ተይዘው በፖሊስ ከተወሰዱ በኋላ የተወሰዱበትን ማወቅ አለመቻሉን አረና ትግራይ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር።አባሉ የተያዙበትን እስር ቤት ሰሞኑን ማረጋገጡን የገለጠው አረና ጠበቃ የማማከር ህገመንግስታዊ መብታቸው ግን ተነፍጓል ሲል ፖሊስን ከስሷል።በሌላ በኩል ደግሞ ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ ሁኔታ የተሰሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች የአንድነቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊው አቶ ዳንኤል ሺበሺና የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ እስከአሁን ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውን ድርጅቶቹ አስታውቀዋል።ተከሳሾች በአርባ ስምንት ሰአታት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ ህገመንግስታዊ መብታቸው ያለመከበሩን መሰረት ያደረገው የተከሳሾች ጠበቃ በበኩሉ በመሰረተው አካልን ነፃ የማድረግ አቤቱታ ወይም ሀቢየስ ኮርፐስ የህግ ሂደት የያዛቸው ክፍል ቀርቦ መልስ እንዲሰጥ ለነገ፣ ማክሰኞ ሀምሌ ስምንት ሁለት ሺህ ስድስት አመተ ምህረት አዝዟል።ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፖለቲካ መሪዎች እስርና ይዞታ ፓርቲዎቹን እያሳሰበ ነው
ዜና ሚያዚያ የወልቃይትን ማንነት በተመለከተ በተነሳው ጥያቄ ዙሪያ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት ከትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ጋር ፀብ ውስጥ መሆናቸው ተገለጠ። ይህንን የተናገሩት ራሳቸው የአማራ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሲሆኑ የአማራ ምሁራን ከሩቅ ሆነው ከሚቃወሙ እንደ ትግራይ ተወላጆች ሀብት እንዲሰበስቡም ጥሪ ማቅረባቸው ምንጮች ለኢሳት ገልፀዋል።በዩናይትድ ስቴትስ በህክምና ላይ የሚገኙትን ባለቤታቸውን ለመጎብኘት በአሜሪካ የሚገኙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የወልቃይት ህዝብን የማንነት ጥያቄ በተመለከተ በርሳቸውና በድርጅታቸው በኩል የተያዘው አቋም የትግራይ ክልል መንግስትንና ህወሀት እንዳላስደሰተ ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ በርሳቸውና በትግራይ ፕሬዚደንት አቶ አባይ ወልዱ መካከል በግልፅ ፀብ መኖሩንም አመልክተዋል።በዩኤስ አሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ራክቪል እና ቤተሳዳ በተባለው አካባቢ በሚገኘው ሰብኧርባን ሆስፒታል ባለቤታቸውን ለመጎበኘት የመጡት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከተለያዩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር በግል መወያየታቸው የታወቀ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚሰጡት አስተያየት እየተምታታ መገኘቱ በሰላም በኩል እዚህ ከምትቃወሙ ሀገር ቤት ገብታችሁ እንደትግራዋይ ሀብት ሰብስቡ የሚል ጥሪ በማድረጋቸው ቅንነታቸውን የጠረጠሩ መኖራቸውም መረዳት ተችሏል።እዚህ ሀገር የመንግስት ባለስልጣናት ሲመጡ የሚቃወሙ ሰዎች እንዳይደርሱብኝ በሚል አንድ የአሜሪካ ወታደር ከነበረ ኢትዮጵያዊ ጋር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውንም ለሚያገኙት ሁሉ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።ሀብት ይዘው ሀገር ቤት የገቢ ሀብታቸውን እጥተው እየተሰደዱና እየታሰሩ ባለበት እንዲሁም የፖለቲካ ስልጣንኑ በህወሀት ቁጥጥር ስር በቀጠለበት ሀገር ቤት ገብታችሁ ሀብት ሰብስቡ የሚለው ጥሪ የተቀነባበረ ዲያስፖራውን የመቅረብ ዘመቻ ሳይሆን እንዳልቀረ ተመልክቷል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባለቤታቸውን ከመጠየቅ ጎን ለጎን ድርጅታዊ ስራ ደርበው መምጣታቸውም ተሰምቷል።አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በቅርቡ ለተመሳሳይ ተልእኮ በተባበሩት አረብ ኤመሬትስ ዱባይ ቆታ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።አጎ ገዱ አንዳርጋቸው በወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ላይ ከትግራይ ክልላዊ መንግስት የተለይ አቋም ይዣለሁ ከአባይ ወልዱ ጋርም ተጣልቻለሁ ቢሉም የወልቃይት መብት ተሟጋቾች ሲታሰሩ እንዲሁም ጥያቄያቸው ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ሲመለስና የትግራይ ክልልም አልቀበልም ሲል ርሳቸውና የክልሉ መንግስት እንዲሁም ብአዴን ከዝምታ በቀር የወሰዱት እርምጃ የለም።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአቶ አባይ ወልዱ ጋር በወልቃይት ጉዳይ ፀብ ውስጥ ነኝ አሉ
እሁድ መጋቢት ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት አርማ የሌለው ሰንደቅ አላማ በመጠቀማቸው ምክንያት በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌና ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ ግለሰቦች በዋስትና እንዲፈቱ ቢፈቀድላቸውም፣ እስካሁን እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸው ለሪፖርተር ገለፁ። ከጀሞ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አንዱ በሆነው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት ተሰባስበው ለአመታት በእስር ላይ ስለከረሙበትና ስላሳለፉት ጊዜያት እያወጉ ሻይ እየጠጡ ሳለ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ፣ ጦማሪ ማህሌት ፈንራሁን፣ ጦማሪ ዘለአለም ወርቅ አገኘሁ፣ ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበሩ ፣ አቶ ይድነቃቸው አዲስ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ ተፈራ ተስፋዬና አቶ አዲሱ ጌታነህ ናቸው።በዋስትና እንዲፈቱ የተባሉት ተከሳሾች እርስ በእርሳቸው ዋስ በመሆን እንዲለቀቁ ሰኞ መጋቢት ሀያ አራት ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት ቅፅ ሞልተው ሲጠሩ እንዲገኙ የተነገራቸው ቢሆንም፣ እስካሁን እንዳልተፈቱ ለማወቅ ተችሏል።በሌላ ዜና መጋቢት ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት በባህር ዳር ከተማ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት ቅድመ ስብሰባ አድርገው እራት በመብላት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ከ በላይ ግለሰቦች ዛሬ መፈታታቸው ታውቋል። በባህር ዳር የታሰሩት ግለሰቦች የተፈቱት በመታወቂያ ዋስ እንደሆነም ሪፖርተር አረጋግጧል።
እነ እስክንድር ነጋ የዋስትና መብት ቢከበርላቸውም አልተፈቱም
በህወሀትና ብአዴን የተዘጋጀውንና ቅማንትን በአዲስ አስተዳደር ለመከለል የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ የፌደሬሽን ምክር ቤት ማፅደቁ ተሰማ። ያለህዝበ ውሳኔ በህወሀት ቀድመው የተካለሉት የአርባ ሁለት ቀበሌዎች ጉዳይ አሁንም የህዝብ ጥያቄ ማስነሳቱ ታውቋል። የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ያፀደቀበት ምክንያት ያለህዝብ ፍቃድ የተካለሉትን አርባ ሁለት ቀበሌዎች ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይገልፃሉ። የጎንደርን ህዝብ ለመከፋፈል የሚደረገውን የስርአቱን ማንኛውንም አይነት እርምጃ ህዝቡ በንቃት እየተከታተለ እንዲታገለው የጎንደር ህብረት ጥሪ አድርጓል። መስከረም ሰባት ሁለት ሺህ አስር ህወሀት የፈለገውና የፈቀደው ህዝበ ውሳኔ ሲካሄድ ውጤቱ ቀድሞም ይታወቅ ነበር። ለዘመናት ሳይለያዩ የኖሩትን የጎንደርና የቅማንት ማህበረሰብ በአስተዳደር ወሰን ለይቶ ለማካለል በሚል የልዩነት ምርጫ ይዞ የመጣው የህወሀት መንግስት ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ አድርጓል። በ ቀበሌዎች ታስቦ የነበረው ይህው ህዝበ ውሳኔ አራትቱ ቀበሌዎች በእኛ ምርጫ ሊደረግ አይገባም በማለታቸው በስምንትቱ ብቻ እንዲደረግ ተወሰነ። ህዝበ ውሳኔውም ተካሄደ። ከዘጠና አምስት በመቶ በላይ የሚሆኑትና በሰባት ቀበሌዎች የሚገኙት መራጮች በነበረው አስተዳደር ስር መቆየትን ሲመርጡ አንድ ቀበሌ ግን በህወሀት እንዲካለል በተፈለገው የቅማንት አስተዳደር ስር መሆንን መረጠ። ሆኖም በዚህም ቀበሌ የነበረው ድምፅ በህወሀት ሰርጎ ገብ ካድሬዎች በመጭበርበሩ መሆኑ ተጠቅሶ ተቃውሞ ቀርቦበታል። እስካሁንም የቀበሌዋ ነዋሪዎች ድምፃችን አልተከበረም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። ሆነም ቀረም የስምንትቱ ቀበሌዎች ውጤት በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መላኩ ተገለፀ። ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህዝበ ውሳኔውን ውጤት ማፅደቁን አስታዉቋል። በዚህም መሰረት ሰባቱ ቀበሌዎች በነበረው አስተዳደር ስር ለመቆየት መወሰናቸውን ተቀብሎታል። አንደኛው ቀበሌ በአዲሱ የቅማንት አስተዳደር ስር እንዲሆን በውጤቱ መሰረት ማፅደቁንም ገልጿል። የጎንደር ህብረት አመራር አቶ አበበ ንጋቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን የዛሬ ውሳኔ ብዙም ቦታ የሚሰጠው አይደለም ይላሉ። ቀድሞውኑ ማህበረሰቡ የማይቀበለው ነበር።ያንንም ነው በህዝበ ውሳኔው ያረገገጠው ብለዋል አቶ አበበ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የግጨውን ህዝበ ውሳኔ ውጤት ከአስር አመታት በላይ በመዝገብ ቤት ውስጥ ቆልፎበት ከቆየ በኋላ በዚህ አመት መግቢያ ላይ ህወሀት የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን እጅ በመጠምዘዝ ግጨውን መውሰዱ የሚታወስ ነው። ባለፈው መስከረም ሰባት የተደረገው ህዝበ ውሳኔ ውጤት የግጨው እጣ ፈንታ እንዳይገጥመው የሰጉ ወገኖች ቢኖሩም ፌዴሬሽን ምክር ቤት ውጤቱን ሊያፀድቀው ችሏል። አቶ አበበ ንጋቱም ሆኑ አንዳንድ የአካባቢውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚከታተሉ ወገኖች የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ በአርባ ሁለት ቀበሌዎች የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ለማድበስበስ ታልሞ የተደረገ ነው። ያለህዝብ ፈቃድ አርባ ሁለት ቀበሌዎች በቅማንት አስተዳደር ስር እንዲሆኑ ህወሀት ቀደም ብሎ ውሳኔ ላይ የደረሰ ሲሆን ህዝቡ ድምፁን እንዳይሰጥ መገደቡ ታውቋል።
ቅማንትን በአዲስ አስተዳደር ለመከለል የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ የፌደሬሽን ምክር ቤት ማፅደቁ ተሰማ
ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስተርኒስትሩ ነው በኛ ክፍል የመልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ላይ የተፈጠረውን ችግር የሚያጣራ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆነ ኮሚቴ መቋቋሙ የተገለፀ ሲሆን ኮሚቴው በጥቂት ቀናት ውስጥ ችግሩን አጣርቶ ውጤቱን እንዲያሳውቅ መመሪያ ተላልፏል። የትምህርት ሚኒስቴር ረቡእ እለት በሰጠው መግለጫ ሰኔ እና ቀን አመተ ምህረት የተሰጡ የአራት ፈተናዎች ውጤት ብቻ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ እንደ መመዘኛ እንደሚያገለግሉ ያስታወቀ ሲሆን ከሰኔ እስከ የተሰጡ ፈተናዎች የተማሪዎቹን ብቃት መለካት የሚያስችሉ አይደሉም ብሏል። በዚህ መሰረት ለዩኒቨርስቲ መግቢያነት መመዘኛ የሚያገለግሉት እንግሊዝኛ ሂሳብ ስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ የጂኦግራፊ ትምህርት ውጤት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የመግቢያ ነጥቡም በቀጣይ ይገለፃል ተብሏል። ይህን መግለጫ ተከትሎ ምሁራንና ተማሪዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰማቸውን ቅሬታ እየገለፁ ሲሆን ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ አካል ሊኖር ይገባል የሚሉ ድምፆችም በብዛት ተንፀባርቀዋል። ችግሩ በማንና እንዴት ተፈጠረ ማንስ ሀላፊነት ይወስዳል የሚለውን የሚያጣራ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆነ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የኮሚቴው ሰብሳቢም የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ጌታሁን ጋረደው መሆናቸው ታውቋል። በአገር አቀፍ ፈተና እንዲህ ያለው ስህተት ሲያጋጥም ይህ የመጀመሪያው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ለችግሩ መከሰት ተጠያቂ የሚሆኑ አካላት በህግ እንዲጠየቁም ከህብረተሰቡ ግፊት እየተደረገ ነው።
በኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተፈጠረውን ችግር የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቋመ
አዲስ አበባ፣ ጥር አንድ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንደሚያሸጋግረው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ተናገሩ። አምባሳደሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ግብዣ ከነገ ጀምሮ በሀገሪቱ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ። አምባሳደሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመሪዎች ደረጃ እና ከተለያዩ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። በተጨማሪም በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚወያዩም አምባሳደር ሽፈራው አንስተዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች የደቡብ አፍሪካ መንግስት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ጥረት ያደርጋሉም ነው ያሉት። አምባሳደሩ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አህመድ በስቴዲየም ከህዝቡ ጋር እንዲገናኙ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። በሀይለየሱስ መኮንን
የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ የደቡብ አፍሪካ ጉብኝት የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንደሚያሸጋግር ተገለፀ
በሻሸመኔ ከተማና አቅራቢያዋ ኪነጥበብ አፍቃሪዎች የተቋቋመው ከአድማስ ፊት የኪነጥበብ ማህበር አርባ አምስትኛ ዝግጅቱን ነገ ከቀኑ ሰባት ሰአት በሻሸመኔ የባህል አዳራሽ እንደሚያቀርብ አስታወቀ። የእለቱ የክብር እንግዳ በ ትናንሽ ፀሀዮች እማ ጨቤን ሆና የምትተውነው አርቲስት ሰብለ ተፈራ ነች። በነገው ዝግጅት የጭውውት፣ የግጥም፣ የዘፈን፣ የመነባንብ ስራዎች ይቀርባሉ። ማህበሩ ካሁን በኋላ በየወሩ በተለያዩ የጥበብ ዘርፎች ውድድር እያካሄደ ለአሸናፊዎች የሚሸልም ሲሆን የነገው ውድድርም በኮሜዲ ዘርፍ እንደሚሆን ማህበሩ ለአዲስ አድማስ ገልጿል። ከ አድማስ ፊት የተመሰረተበትን ስድስትኛ አመት በሀምሳኛ ዝግጅቱ በመጪው ሰኔ ለማክበር እየተዘጋጀ መሆኑንም አስታውቋል።
ከአድማስ ፊት ነገ ኪነጥበባዊ ዝግጅቱን ያቀርባል
ሱር ኮንስትራክሽን የጣና በለስ ነው ይመለስ በወታደራዊው ደርግ ዘመን መንግስት በ ተጀምሮ ወንበዴዎች እስከመጡበት ቆይቷል። ይህ ትልቅ ፕሮጀክት በጎጃም ክፍለሀገር በመተከል አውራጃ የሚገኝ ሲሆን ስኬር ኪሎሜትር ያጠቃልላል ሲጠናቀቅም ከ ሺህ በላይ የሆኑ ህዝቦችን እንዲጠቅም ሆኖ የተጀመረ አገራዊ ፋይዳ ያለው ፕሮጀችት ነበር። የጣና በለስ ፕሮጀክት ዋና ገፅታው ከሞላ ጎደል ይሄን ይመስል ነበር ሜትር ከፍታ ያለውና ከፍተኛ የሆነ የውሀ መጠን የሚይዝ በጣም ትልቅ ግድብበየቀኑ ሜትር ኪውብ ፍሳሽ የሚያስወግድ ፕላንት ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው እርስበርስ የተገናኙ መንገዶች ድልድዮች ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የገጠር መንገዶች ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የተፋሰስ ጉድጓዶች ቀላል መንገዶች እና ውሀ ማቆሪያዎች ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የቀላል አውሮፕላኖች ማረፊያና መንደርደሪያ መንደሮች አልጋዎች ያሉት ሆስፒታል ሺህ ሄክታር የሚሸፍን የእርሻ መሬት ሺህ ሜትር ስኴር ቦታ ላይ ያረፈ የእርሻ ምርቶች ማከማቺያ መጋዝኖችየአግሮ ኢንዳስትሪ ማቀነባበሪያ የሩዝ መፈልፈያ የምርጥ ዘር መምረጫና ዳቦ መጋገሪያየከብት የፍየልና የዶሮ ማርቢያበወር ኪሎሜትር የሚሸፍን ቱቦና ታንከር የሚያመርት ፋብሪካ ሺህ ሜትር ስኴር የሚሸፍን የፕሮጀክቱ ማእከል በጣና በለስና በአዲስ አበባ ውስጥ ነበረው። ከፎቶዎች እንደምትመለከቱት ስራው በከፊል ተጠናቆ ወደ ምርት በመግባት ለተጠቃሚዎች ማድረስ ችሎ ነበር ሆኖም ግን የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዚደንት ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ሲሉ የሰሙት ወንበዴዎች ከድል በዃላ እነሱ ደግሞ በተራቸው ሁሉም ነገር ወደመቀሌ በማለት እንደ ጠላት ንብረት ሁሉንም ነገር ዘረፉት።የውጭ ጠላት ያወደመው እንጂ የሚመስለው በእነዚህ አገራዊ ወንበዴዎች የፈረሰ አይመስልም።ጣና በለስን የማየት እድል የገጠማቸው ሰዎች ሁሉ እንደዛ ሆኖ መቅረቱን ሲያስቡ ያለቅሳሉ። ወንበዴዎች ጣና በለስን በመዝረፍ ሱር ኮንስትራክሽንን በማቋቋም ያንን ሁሉ ህልም ባዶ አስቀሩት።ሰው እንዴት ተስፋን ይሰርቃል ሰው እንዴት የህዝብን ነገ ሆን ብሎ ይቀማልየወያኔ ሱር ኮንስትራክሽን ለመመስረት ሺ የአማራ ህዝብ መስዋት መሆን ነበረበት ያን ሁሉ በደል ችለን በኖርን አሁን ደግሞ ሌላ በደል በወያኔ ተጠነሰሰ የጣና በለስ ፕሮጀክት በዲሳ ለሚባል የቱርክ ድርጅት ተሰጠ ይለናል የወያኔው መንግስት።በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቱ ያቅፋቸው ለዘመናት መሬቱ ላይ የኖሩ አባዉራዎች እንደ መሬት ወራሪ ተቆጥረው በግዳጅ እንዲነሱ እየተደረገ ነው። አሁን ግን ወራጅ አለ ከዚህ በዃላ የአማራን መሬት እንደናትህ እንጀራ ቆርሰህ የምትሰጠበት ጊዜ ላይ አይደለህም። እንዲያውም ጥያቄያችን ተቀይሯል።ሱር ኮንስትራክሽን ፈርሶ ጣና በለስ ይሰራል።ሱር ኮንስትራክሽን የጣና በለስ ንብረት ነውና ይመለስ የአማራው ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ሰዎች ለቱርኩ ባዲሳ ይሄንን የመሬት ቅርምት እንዲያቆም በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች ልትነግሩት ይገባችዃል።አለበለዛ መላው የአማራ ህዝብ ለወልቃይት ጠገዴ እንደተነሳው ሁሉ ለጣና በለስም ይነሳል። ሱር ኮንስትራክሽን የጣና በለስ ነው ይመለስ
የአማራው ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ሰዎች ጣና በለስ ሌላኛዋ ወልቃይት ጠገዴ ሱር ኮንስትራክሽን የጣና በለስ ነው ይመለስ
ሰፋፊ እርሻዎች ባሉባቸው አካባቢዎች በየጊዜው እያጋጠመ ያለው የፀጥታ መደፍረስ በፈጠረው ስጋት፣ ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን የሚሰበስብ የሰው ሀይል ማግኘት እንዳይችሉ እንዳደረገ ገለፁ። በተለይ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በጋምቤላና በአፋር ክልሎች ምርት መሰብሰብ በነበረበት ጊዜ እያጋጠመ ያለው ደም አፋሳሽ ግጭት፣ የሰው ሀይል ወደ ስፍራው እንዳይንቀሳቀስ አድርጓል ተብሏል። በተለይ በዚህ ወቅት በእነዚህ አካባቢዎች የተመረቱትን ጥጥና ሰሊጥ የሚሰበስብ የሰው ሀይል በመጥፋቱ፣ ሊከሰት የሚችለው ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ከወዲሁ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተመልክቷል።የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የጥጥ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ መሰለ መኩሪያ ለሪፖርተር እንደገለፁት፣ በተለይ በአማራ ክልል መተማ አካባቢ መንገድ በመዘጋቱ ጥጥና ሰሊጥ የሚሰበስቡ ሰራተኞችን ማግኘት አልተቻለም።አቶ መሰለ ጨምረው እንደገለፁት፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በተከሰተው ግጭት ጥጥና ሰሊጥ የሚሰበስቡ ሰራተኞችን ማግኘት አልተቻለም። ብዙም ባይሆን የተከሰተው ችግር በአገር ደረጃ ችግር የሚፈጥር እንደመሆኑ መጠን በጋምቤላና በአፋርም የሰራተኞች እጥረት ተከስቷል፤ ሲሉ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪም በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በአፋር ክልል የቀን ስራ ያልተለመደ በመሆኑ ነዋሪዎች ተሳታፊ አለመሆናቸውን፣ አሁን ግን ነዋሪዎቹን አሰልጥኖ ለማሰማራት እየተሞከረ መሆኑን አቶ መሰለ ጠቁመዋል። ምርት በሚሰበሰብበት በዚህ ጊዜ አንድ እርሻ ብቻ ከሁለት እስከ ሶስት ሺህ ሰራተኞች እንደሚፈለግ፣ አብዛኛውን ጊዜ ሰራተኛ የሚገኘው ከአማራ ክልል ከጎጃም አካባቢና ከደቡብ ክልል ከወላይታ አካባቢ እንደሆነ ይነገራል።ከአማራ ክልል የሚገኙት ሰራተኞች ብዙ ጊዜ ምርት የሚሰበስቡት መተማ፣ ቋራና ቤንሻንጉል ጉምዝ አካባቢ ተጉዘው ሲሆን፣ ከወላይታ የሚነሱት ሰራተኞች ደግሞ ጋምቤላና አፋር ክልሎች በመጓዝ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ያስረዳሉ።በጋምቤላ ክልል የተሰማራው የእርሻ ልማት ድርጅት ባለቤት አቶ አብርሀሌ ይደግ ለሪፖርተር እንደገለፁት፣ በዚህ አመት በአንድ ሁለት መቶ ሄክታር መሬት ላይ ጥጥ አልምተዋል። ነገር ግን ዘንድሮ የተሻለ ምርት እንደሚያገኙ ቢያስቡም፣ ከሌላው ጊዜ በተለየ የሰው ሀይል እጥረት ገጥሟቸዋል። ሶስት ካምፖች አሉን። በአንደኛው ካምፕ አምስት መቶ ስላሳ ሄክታር መሬት ላይ ጥጥ አልምተናል። ከዚህ እርሻ ብቻ እስከ ሀያ ሺህ ኩንታል ጥጥ ይገኛል። ነገር ግን እስካሁን የተሰበሰበው ሰባት መቶ ኩንታል ብቻ ነው፤ በማለት የሚናገሩት አቶ አብርሀሌ፣ በአጠቃላይ ካለሙት አንድ ሁለት መቶ ሄክታር መሬት እስካሁን ድረስ ሀምሳ በመቶ መሰብሰብ የነበረበት ቢሆንም፣ መሰብሰብ የተቻለው ግን አስር በመቶ ብቻ ነው ሲሉ፣ የችግሩን ስፋትና እያንዣበበ ያለውን ውድመት ያስረዳሉ። አብርሀሌ ይደግ እርሻ ልማት ድርጅት በአሁኑ ወቅት ሁለት ሰራተኛ ይፈልግ ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ሰራተኛ ባለማግኘቱ ድርጅቱ ከፍተኛ ስጋት ተጋርጦበታል፤ ብለዋል። የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ መንግስት ባስቀመጠው እቅድ፣ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በመመደብ ልማቱን አካሂደን ነበር። ነገር ግን ምርት የሚሰበስብ ሰራተኛ በመጥፋቱ ከፍተኛ የአገር ሀብት ለውድመት ተዘጋጅቷል፤ ሲሉ አቶ አብርሀሌ መንግስት በፍጥነት ለዘርፉ እንዲደርስ ጠይቀዋል። በዚህ አመት ለኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ሀምሳ ስምንት ሺህ ሜትሪክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ ይገኛል ተብሎ ታቅዶ ነበር። ጥጥ ከእርሻ ላይ በወቅቱ የሚነሳበት እድል በመጥበቡና ከሚቀጥለው ወር በኋላ ዝናብ ይጥላል ተብሎ ስለሚገመት፣ የምርት ውድመት ያጋጥማል ተብሎ ተሰግቷል።አቶ መሰለ እንደሚሉት፣ ይህንን አሳሳቢ ችግር ለመፍታት ኢንስቲትዩቱ ከክልል መንግስታትና ከፀጥታ መዋቅሮች ጋር እየተነጋገረና መፍትሄ ለማበጀት ጥረት እያደረገ ነው።
በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የግብርና ምርቶችን የሚሰበስብ የሰው ሀይል እጥረት ተከሰተ
የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው ቋንቋዎች ውስጥ የብራይሌና ባጫ ቋንቋዎችን ለመታደግና መልሶ እንዲያገግሙ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለፀ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሁለት ሺህ በጀት አመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ባቀረበበት ወቅት እንደተገለፀው፣ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸውን ቋንቋዎች ለመታደግ በሚል ሀያ ሁለት ቋንቋዎችን የመሰነድ ስራዎች በመስራት በዘጠኝ ወራት ውስጥ የብራይሌና ባጫ ቋንቋዎች መልሶ እንዲያገግሙ ለማስቻል፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከሌሎች ባለድርሻ አካለት ጋር ምክረ ሀሳብና ግብአት ማሰባሰብ የሚያስችል የምክክር መድረክ መካሄዱን ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ ተናግረዋል። የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ቋንቋዎች በድጋሚ ለመመለስ በተደረገው ጥረት በደቡብ ኢትዮጵያ ኦሞ ዞን ብራይሌ፣ መዊ፣ አንጉታና ባጫ ቋንቋዎች የተገኙ ሲሆን አንድ መቶ አርባ አምስት አመታት ያስቆጠረው የብራይሌ ቋንቋ አምስት ተናጋሪ ብቻ በማግኘት ከእነዚህም ውስጥ ብራይሌ የተባለውን ትክክለኛ ቋንቋ የሚናገረው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን በማረጋገጥ የቀሩት ሰዎች ከተለያዩ ቋንቋዎች ጋር በመደባለቅ የሚናገሩ መሆናቸው በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል። ሊጠፉ የተቃረቡ ቋንቋዎችን የሚናገሩትን አምስቱ ሰዎች በእድሜ የገፉ በመሆናቸው፣ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር ቋንቋውን ማስቀጠል የሚቻልበት መንገድ እየተሞከረ ነው ብለዋል። ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማሀበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ከምክር ቤቱ አባላት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥያቄዎች የቀረበ ሲሆን፣ ከጥያቄዎቹ መካከል እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የአገሪቱን የቋንቋዎች ብዛት በጥናት ለይቶ የማወቅ ሀላፊነት ያለበት ቢሆንም ከሰማኒያ በላይ ቋንቋዎች በማለት ለምን እንደሚጠቀም ተጠይቋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለዚህ በሰጠው ምላሽ በውል የሚታወቁ የቋንቋዎች ብዛትን በመለየት በቁጥር ለመግለፅ ጥናት የሚፈልግ በመሆኑ በሂደት ላይ ያለው ጥናትም ቢሆን በአንዳንድ ቋንቋዎች ላይ ያሉ ተመሳሳይነት ወደ አንድ ለማምጣት በሚመከርበት ወቅት የቋንቋው ተናጋሪ ክፍል የሚወክለው መሆን አለመሆኑን እንዲሁም ሀብረተሰቡ ላይ ጥያቄ በማይፈጥር መልኩ ለመሰነድ እየተሰራ መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀላፊዎች አብራርተዋል። የጥናቱን ውጤትም በቅርቡ ይፋ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ቋንቋዎችን በማበልፀግ የኢኮኖሚው፣ ማሀበራዊና ፖለቲካዊ ማስተሳሰሪያ ገመድ በማድረግ የአገሪቱን እድገት ለማረጋገጥ በዘርፉ ትክክለኛ፣ የሰለጠነና ፕሮፌሽናል የሆነ የሰው ሀይል ለማፍራት ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በመስራት የቋንቋ ልማት አጠቃቀምን ለማሳደግ የቋንቋ ልማት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ሀብረተሰቡን በቋንቋው ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ልዩ ልዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ተብሏል። በተያያዘም በሁለት ሺህ በጀት አመት ፀድቆ ስራ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ የቋንቋ ልማት ፖሊሲ፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋዎች ፊደል ተቀርፆላቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለትምህርት መስጫነት እንዲውሉ አቅጣጫ ከተቀመጠ በኋላ ተጨማሪ ስድስት የብሄር ብሄረሰብ ቋንቋዎች ሀረሪ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ትግርኛ ኦሮምኛና ሲዳሚኛ የክልል የስራ ቋንቋ በመሆን እያገለገሉ እንደሚገኙ ይታወሳል። ከአማርኛ በተጨማሪ ለፌዴራል የስራ ቋንቋነት እንዲውሉ እውቅና የተሰጣቸው አራት ቋንቋዎች ማለትም ኦሮምኛ፣ ሶማሌኛ፣ አፋርኛና ትግርኛ ቋንቋዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ተከታታይ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል። በፖሊሲው ከተካተቱ ጉዳዮች አንዱ የሆነው የቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲትዩት ማቋቋም ሲሆን ይህን በተመለከተ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በቻይና ቤጂንግ የውጭ ጉዳይ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ጥናት ማእከል ማቋቋሚያ ረቂቅ ሰነድ ቀርቦ በሰነዱ ላይ አቅጣጫ መሰጠቱን ሪፖርቱ ጠቅሷል። ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የትርጉምና አስተርጓሚነት ሙያ ስራ ላይ እንዲውል ስርአተ ትምህርት በማዘጋጀት ተግባራዊ ለማድረግ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም፣ በአገሪቱ ባሉ ሁለት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የትርጉምና አስተርጓሚነት ፕሮግራም ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል። ብዝሀ ቋንቋን መልቲ ሊንጓሊዝም ለማበረታታት በአገሪቱ የሚገኙ አስር ቋንቋዎችን በዲጂታል ስርአት እንዲሰነዱ ለማድረግ ማስተባበር፣ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ታቅዶ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንሲ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ሁሉንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዲጂታል ቴክኖሎጅ በአንድ ቋት ስር ሰንዶ በማደራጅት ተጠቃሚ ለማድረግ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።
የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው ቋንቋዎች ውስጥ ሁለቱ በድጋሚ እንዲያገግሙ እንደሚደረግ ተገለፀ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የቢሾፍቱ ጨፌ ዶንሳ ሰንዳፋ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ የአፈር ቆረጣ እና የውሀ መፋሰሻ ቱቦ የማምረት ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል። መንገዱ የምስራቅ እና የሰሜን ሸዋን የሀገራችን ክፍሎችን በአቋራጭ የሚያስተሳስር ይሆናል። ፕሮጀክቱን በዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘው ሀገር በቀሉ ራማ ኮንስትራክሽን ነው። የትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ እንዲሁም የተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የመስክ የስራ ቅኘት አካሂዷል። ፐሮጀክቱ በሀምሳ አምስት ኪ ሜትር ርዝመት ቢሾፍቱ ጨፌ ዶንሳ ሰንዳፋን ያገናኛል። ዲዛይን እና ግንባታን በጋራ አካቶ የያዘው ፕሮጀክቱ በእስካሁኑ አፈፃፃም የተሰሩ ስራዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ቀጣይ የስራ እቅዶችን በተመለከተ ለተቋማቱ የስራ ሀላፊዎች ገለፃ ተደርጎላቸዋል። በእስካሁኑ ክንውንም የካምፕ ግንባታ የመሬት ጠረጋ የአፈር ሙሌት ድልዳሎ ስራዎች እየተከናወኑ ነው። የአፈር ቆረጣ እና የውሀ መፋሰሻ ቱቦ የማምረት ስራዎችም እየተከናወነ ይገኛል። የግንባታ ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈነው ይኸው ፕሮጀክት በርካታ እስትራቴጂካዊ ጠቄሜታዎች ያሉት በመሆኑ በሁለት ሺህ በጀት አመት በወርሀ ህዳር በጊዜ ገድብ እንዲጠናቀቅ የስራ ሀላፊዎቹ አሳስበዋል። የመንገዱን ግንባታ ጥራት በመቆጣጠር ረገድ ሲ ደብሊው ሲ ኢ እና ጂ ኤንድ ዋይ የተባሉ አማካሪ ድርጅቶች ዮአሺን ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ከተባለ የኮርያ ድርጅት ጋር በጥምረት የሚሰሩት ሲሆን ጥራትን በማስጠበቅ መንገዱ በተባለው ጊዜ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ መቀመጡን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። የመንገዱ የጎን ስፋት በወረዳ ከተማ ሀያ አንድ ነጥብ አምስት ሜትር ፣ በቀበሌ ሜትር እንዲሁም በገጠር አስር ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው እየተገነባ የሚገኘው።
ለቢሾፍቱ ጨፌ ዶንሳ ሰንዳፋ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ የአፈር ቆረጣ እና የውሀ መፋሰሻ ቱቦ የማምረት ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል
በየአመቱ በነሀሴ ወር የሚዘጋጀው የሸራተን የስእል አውደ ርእይ ሊቀርብ ነው። በሚል ርእስ የሚቀርበው አውደ ርእይ በኢትዮጵያ ያሉ የጥበቡ ፈርጀ ብዙ ገፅታዎችን የሚያሳዩ ያህል ስእሎች ይቀርቡበታል ተብሎ ይጠበቃል። ከነዚህ ስራዎች ከመቶ አስር እጅ በቅርፃ ቅርፅ ላይ ያተኩራል የተባለለት ትልቅ አውደ ርእይ በሚቀጥለው አርብ ነሀሴ ቀን አመተ ምህረት ተከፍቶ እስከ ነሀሴ በየእለቱ ከቀኑ ሰአት እስከ ምሽቱ ሰአት ለህዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል። በዝግጅቱ ሰአሊዎች ስራዎቻቸውን እንዲታይላቸው አቅርበው የምርጦቹ ምርጥ ለአውደርእዩ መቅረቡንና ከነዚህም ሩቡ እጅ የሴት ሰአሊያን ስራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ሸራተን አዲስ ላለፉት አምስት አመታት በየአመቱ ታላቅ የስእል አውደርእይ እያሳየ ይገኛል። አውደርእዩ በአዲስ አበባ የሚገኙ የስእል ትምህርት ቤቶችን ለማጠናከር ያለመ ነው።
አመታዊው የሸራተን የስእል አውደ ርእይ ይቀርባል
የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ አምባገነን አገዛዝ መሸጋገር አለመሆኑን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ገለፁ። ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት የምንታገልለት ለውጥ የኢትዮጵያን ህዝብ ይሁንታ ያገኘ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል። በለውጡ ሂደት ስልጣን ሀላፊነት በሌላቸው እጅ እንዳይገባ በከፍተኛ የሀላፊነትና የአጣዳፊነት ሁኔታ መታገል አለብን ሲሉም ገልፀዋል። ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ የወቅቱን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት የህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ ለብሄራዊ እርቅ ደንታ እንደሌለው በአሁኑ ጊዜ የደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አመላካች ነው ብለዋል። ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቀባይነት የሌለውና እንደ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የሚቆጠር ነው ባይ ናቸው። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ። እንደ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ገለፃ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ አምባገነን አገዛዝ መሸጋገር አይደለም። እናም ህዝቡ ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይሰብረዋል ነው ያሉት። ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በቪዲዮ በተለቀቀ መልእክታቸው እንዳሉት የህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ እየተፍረከረከና እያከተመለት መሆኑን የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶች መታየት ጀምረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ፣ በኢህአዴግ ውስጥ ባሉ አባል ድርጅቶች የለውጥ ፍላጎት ያላቸው ሀይሎች መፈጠር መጀመራቸው፣ የትግሉ ውጤት ስኬታማ መሆኑን እንደሚያመለክትም ገልፀዋል። በዚህ የለውጥ ሂደት ወገኖቻችን የታሰሩበት፣የተገረፉበትና የተገደሉበት ትግል ሀላፊነት በሌላቸው ሀይሎች እጅ እንዳይገባም ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል ብለዋል። እናም የምንታገልለት ለውጥ የኢትዮጵያን ህዝብ ይሁንታ ባገኘበት ሁኔታ የሽግግር መንግስት የሚፈጥር መሆን አለበትም ነው ያሉት።ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ። ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ዋናው የትግል ስልታችን ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው ሲሉም ገልፀዋል። በዚሁ ትግል ታዲያ በኑሮ ውድነት እየተንገላታ ያለው የአዲስ አበባ ህዝብም ዝምታውን ሰብሮ ትግሉን እንዲቀላቀል ጠይቀዋል። ለመከላከያ፣ለኢህአዴግ አባላትና ለትግራይ ህዝብም አገዛዙ እያከተመለት በመሆኑ ከአገዛዙ መደበቂያነት ወጥተው የህዝቡን ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ አምባገነን መሸጋገር አይደለም ተባለ
ሰኞ ነሀሴ ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞችን ለማደራደር በተደረገው ጥረት ውጥረት በተፈጠረበት ሰአት፣ ከግራ ወደ ቀኝ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ አምባሳደር ማህቡብ ማእሊም፣ የኢጋድ ምክትል ሊቀመንበር ኡሁሩ ኬንያታ፣ የኢጋድ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማርያም ደሳለኝና የአፍሪካ ሀብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ በዋና አደራዳሪው አምባሳደር ስዩም መስፍን የሚደረግላቸውን ገላፀ በዚህ ሁኔታ ነበር በትኩረት ሲያዳምጡ የነበሩት። ፍቅር መጨረሻ አንቺ ከፍ ብለሽ ቀና ብዬ ሳይሽ ያመኛል አንገቴን አዘቅዝቄ ልይሽ አውቃለሁ አትችይም አንቺም ማለት ቀና እኔን ዝቅዝቅ ማየት ታልሚያለሽና ጐረቤቶቻችን አይወዱም ግልፅ ነው እኛ ከፍ ብለን ሊያዩን ቀና ብለው እኛም አንወድም ለቅፅበት ላንዳፍታ ቀና ብሎ ማየት የነሱን ከፍታ ማንም ቀና እንዳይል እንዳይዝል አንገቱ ማንም እንዳይወጣ ከዝቅጠት ኡደቱ አንዱ አልፎለት ሌላው እንዳይግል ቅናቱ እንዳይናጋብን ማጣት አንድነቱ አንድ ላይ እንነስ ባንዴ እንስነፍና አብረን እንቆርቁዝ አብረን እንተኛና ከዛሬ ጀምሮ ቃል ገባሁኝ ግቢ ዘመድ አዝማድ ልጥራ ጐረቤት ሰብስቢ ሁላችን በአንድነት ሁነን በጉባኤ ከዚህ ድንበር ላናልፍ እንግባ ሱባኤ ተስፋ ያደረገ ተስፋው እንዲጠፋ ፈጥኖ የተራመደ ተፋጥኖ እንዲደፋ አንዳችን ላንዲችን ጠባቂ ሁነነው አብረን እንቀመጥ እንዲሁ እንዳለነው የአብሮ መኖራችን ዋናው መሰረቱ ከፍ ዝቅ አይልም እኩል ነው ፍጥረቱ መዘወት ይሻላል ፊት ለፊት ተፋጦ እንዳንረባበሽ አንዱ ካንዱ በልጦ ዛዲያ እንዴት ይደረግ ምንድነው ብልሀቱ ፍቅርን ለመጨረስ ይህ ነው አብነቱ ጁን ሀያ ዘጠኝ ፓሪስ ተፈሪ አለሙ ተፈሪ አለሙ፣ የካፊያ ምች ሁለት ሺህ ሰባት ሰባ አንድ ሊሆነኝ ነው የሚሰማኝ ግን ስላሳ እንደሆንኩ ነው በመጭው ወር ሰባ አንድ አመት የሚሆናቸው የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ምንም እንኳ እድሜአቸው እየገፋ ቢሆንም፣ አቋማቸውና ጤናቸው የስላሳ አመት ወጣት እንደሚመስል ባለፈው ሳምንት በካዮንጋ ከተማ መናገራቸውን ዘኒው ቪዥንና ዴይሊ ሞኒተር ዘግበዋል። ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ይህ የሆነው አኗኗራቸው ጤናማ በመሆኑና ጤናቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ እንደ አልኮልና ዘማዊነት ያሉ ነገሮች ራሳቸውን በማቀባቸው እንደሆነ አስረድተዋል። ጤናዬን በጣም እጠብቃለሁ። አልኮል አልጠጣም ለዚህም ነው አሁንም ጠንካራና ሀይለኛ የሆንኩት። የእናንተም ጤና ሀብት በመሆኑ ጤናችሁን ልትጠብቁ ይገባል። ኦቦቴን፣ ኢዲያሚንን፣ ኦኬሎንና ጆሴፍ ኮኒን ተዋግቻለሁ አሁንም ግን ጠንካራ ነኝ ብለዋል። የጤናማ አኗኗር አቀንቃኝ የሆኑት ሙሴቬኔ፣ ከዚህ ቀደም ቢቢሲ ሀርድ ቶክ ላይ አሳ፣ ዶሮና የአሳማ ስጋ እንደማይበሉ ተናግረው ነበር። ብዙ ጊዜ ዩጋንዳውያን ጤናማ ባልሆነ የኑሮ ዘዬ ህይወታቸውን እንደሚያጡ ሲናገሩም ይደመጣሉ። ብሽቅ ኤደንብራ ውስጥ የሚገኙት የዊቨርሊ ደረጃዎች ነፋስ ይበዛባቸዋል። ካመት አመት ያለማቋረጥ ሀይለኛ ነፋስ እንደነፋስ ነው። ታዲያ አንድ ቀን አንዷ ሴት ወይዘሮ ባቡር ልትሳፈር ተቻኩላ ደረረጃዎቹን እየሮጠች ወጥታ ስትጨርስ ነፋሱ ገለባት። ተናዳ ያያት ሰው መኖሩን ለማወቅ ዞር ብላ ስትመለከት አንዱ ከታች ያጮልቃል። ወደ ስራህ ብትሄድ አይሻልም አለችው በተግሳፅ። እሺ፣ እሄዳለሁ፤ ግን ትላንትም የለበሽው ይህንኑ የውስጥ ሱሪ ነበር አይደል አላት። ፖሊሲ ጣቢያ ሰውየው በመርሴዲስ መኪና ስርቆት ቢወነጀልም ድርጊቱን አለመፈፀሙን አምርሮ በመግለፁና በጠበቃውም ብርታት ነፃ ይዋጣል። ሪገር ግን በማግስቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ገስግሳ ይሄድና፣ ያአ ጠበቃዬን እንድትይዙልኝ ላመለክት ነው የመጣሁት ይላል። የጣቢያው ሀላፊ ተገርመው፣ ለምን ነፃ ያወጣህ እሱ አልነበረም እንዴ አሉት። እሱማ ነው ሆኖም ያገልግሎቱን ዋጋ ልከፍለው ስላልቻልሁ የሰረቅኳትን መርሴዲስ መኪና ነጥቆኝ ስለተወሰረ ነው የከሰስኩት። አረፈአይኔ ሀጐስ የስኮትላንዳውያን ቀልዶች ሁለት ሺህ አምስት ሂላሪ ክሊንተንን እንዳትመርጡ የሚል መልእክት የሀዘን መግለጫ ላይ ወጣ በኒው ጀርሲ የስልሳ ሶስት አመት አዛውንት ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ባለቤታቸው የሀዘን መግለጫ ሲያወጡ መልእክቱ ሂላሪ ክሊንተንን እንዳትመርጡ የሚል እንዲሆን በመጠየቃቸው የሀዘን መግለጫው በመጨረሻ ክሊንተንን እንዳትመርጡ የሚል መሆኑን አሶሽዬትድ ፕሬስ ዘግቧል። የአዛውንቷ ባለቤት ኢሌን ፋይድሪክ ሚስታቸው ፖለቲከኛ እንዳልነበሩ ነገር ግን እ ኤ አ የሁለት ሺህ የቤንጋዚውን የአሜሪካ ኤምባሲ ጥቃትን ተከትሎ ሂላሪ ክሊንተንን መጥላት መጀመራቸውን ተናግረዋል። እሳቸው እንደገለፁት ሚስታቸው ህይወታቸው ከማለፉ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ምንም እንኳ የመጨረሻው ውሳኔ የእሳቸው ቢሆንም የሀዘን መግለጫው ላይ እባካችሁ ለሂላሪ ክሊንተን ድምፃችሁን አትስጡ የሚል መልእክት እንዲሰፍር ጠይቀዋቸዋል። እሳቸውም የሚስታቸውን ቃል ጠብቀዋል።
ሰኞ ነሀሴ ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞችን ለማደራደር በተደረገው ጥረት ውጥረት በተፈጠረበት ሰአት፣
አንድ መቶ ዘጠና ስድስት አርአያ ጌታቸው የዘንደሮ ክረምት ከቀደምቶቹ በጥቂቱ ጠንከር ያለና ብዙዎችን በተለይም አዲስ አበቤዎችን እያማረረ ነው። ሌላው በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሚያስብለው ደግሞ የከተማዋ መንገዶች በአብዛኛው ጥገና ላይ መሆናቸውና በዚህም ሳቢያ የበርካቶች መኖርያና የንግድ ሱቆቻቸው መፍረሳቸው ነው። ይህንን ሁኔታ በምናብ ለማየት ለምትፈልጉ ቅዳሜ ነሀሴ አራት ቀን ሁለት ሺህ አምስትአመተ ምህረት በወጣቺው ፋክት መፅሄት ላይ ፕሮፌሰር መስፍን እንዲህ ሲሉ ገልፀዋታል አዲስ አበባ በመሬት መናወጥ ፈራርሳ በመጠገን ላይ ያለች ከተማ ትመስል የለም እንዴ ። ብቻ ክረምቱም ወደማለፉ እየተቃረበ አዲሱንም ዘመን ለመቀበል ሽርጉዱ ሳይጀመር አይቀርም። ምን ክረምቱ ብቻ ፖለቲካውም ክረምቱን ተከትሎ ከስምንት አመታት በኋላ እሱም ጠንከር ያለ ይመስላል። ላለፉት ጥቂት አመታት በሀገር ውስጥ ሲደረጉ የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴዎች በአመት ውስጥ እንኳ አንድ የሚረባ ለዜና የሚሆን ስራ ሳይሰሩ በውስጥ ጉዳያቸው ተጠምደው፤ የሀገሪቷን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ እኩል ተመልካች መስለው ነበር። ምንም እንኳ የአሁኑ የፖለቲካ ጡዘት መነቃቃት የፈጠረው ግንቦት ሀያ አምስት በአዲስ አበባ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ነው ብንልም፤ ላለፉት ሁለት አመታት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሰላማዊ ትግሉን በፅናት ሲያካሄዱ የቆዩት የሙስሊሞቹን እንቅስቃሴ ለአፍታም ሳንዘነጋ መሆን ይኖርበታል። ወዷናው የፅሁፌ አላማ ስመለስ የፊታችን ነሀሴ ሀያ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ አምስትአመተ ምህረት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ከመድረሱ በፊት ከኛ ምን ይጠበቃል የሚለውን መነሻ ሀሳብ ለማቅረብ ነው። ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ አንድነት ፓርቲ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚያደርጋቸውን በርካት ሰላማዊ ሰልፎችን እና ስብሰባዎችን ሳልዘነጋ ነው። ይህ የነሀሴ ሀያ ስድስት ግን በይዘቱም በጥያቄዎቹም እንዲሁም በቦታውም ለየት ያለ በመሆኑ የተለየ ትኩረት ይሻል። በመጀመሪያ በፓርቲው የተነሱት ጥያቄዎች በቀጥታ ከድርጅቱ የተገኛኙ ሳይሆኑ አጠቃላይ ድርጅቱ እታገልለታለሁ ያለውን ህብረተሰብ የሚወክሉ በመሆናቸውም ጭምር ነው። የተነሱት አራት መሰረታዊ ጥያቄዎች ለማስታወስ ያህል፡ የመጀመሪያው ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርአት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን አጥብቀን የምንቃወም መሆኑንና እስረኞችንም እንዲፈታ በሁለተኛ ደረጃ የተነሳው ደግሞ የዜጎችን ሰብአዊና ህገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብአዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ሀይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስትም ሆነ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ሶስተኛው ጥያቄ መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርአታችንና የሀይማኖት መሪዎቻችንን እምነታችን በሚፈቅደው ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብአዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ እንዲቆምና ያነሷቸውም የእምነት ነፃነት ጥያቄዎቻቸው እንዲከበር በአራተኛነት የተነሳው የኑሮ ዉድነትን፣ የስራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን መንገዶችና ፖሊሲዎች በማዉጣት ሀገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ የሚል ነው ይህ ጥያቄ በአብዛኛው የስርአቱ ተቃዋሚዎችን የሚወክል በመሆኑ እንዲሁም ይህንን ጥያቄ ለመደገፍ እና ለዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ድጋፍ ለማድረግ የማንንም የፖለቲካ ፍልስፍና ወይም አቋም የማይፃረር እና ሰማያዊ ፓርቲም የራሱን የፖለቲካ ፍልስፍናም ሆነ አቋም ለመጫን ያልሞከረበት በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው ብዬ ስለማምን ነው። ምንም እንኳ ፓርቲው ለነዚህ ጥያቄዎች ከመንግስት መልስ እንዲሰጠው ለሶስት ወር ጊዜ የሰጠው ቢሆንም፤ ስርአቱ ግን ይባስ ብሎ አፈናውን በማጠናከር ከማሰርና ከማፈናቀል በዘለለ ንፁሀን ዜጎችን አንድ ተራ ሽፍታ እንኳ የማይፈፅማቸውን በህፃናት እና በእናቶች ላይ ተኩስ መክፈትና መግደል ጀምሯል። ይህ ምናልባት ለኢህአዴግ መራሹ መንግስት አዲስ ታሪኩ ባይሆንም ከሀያ አመታት በላይ ድርጅቱን በፍፁም አምባገነናዊነት የመሩት አቶ መለስ ሞትን ተከትሎ ተስፋ ላደረጉ ጥቂቶች የስርአቱን መበስበስና የማይቀየር መሆኑን አሳይቷቸዋል። ይህንን ስርአት ከህብረተሰቡ ጫንቃ ላይ ለማንሳት የሚደረገው የሰላማዊ ትግልም ከዚህ የስርአቱ ባህሪ አንፃር ፍፁም መራርና ከባድ መስዋእቶችን ሊያስከፍን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ከነዚህ የሰላማዊ ትግሎች ውስጥ ግንቦት ሀያ አምስት ቀን ሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት የተጀመረው የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ አንዱ ነው። ፓርቲው ከሰልፉ በኋላ ሲያደርጋቸው የነበሩት እንቅስቃሴዎችም የሚቀጥለው እንቅስቃሴው ከሰልፍ በዘለለ የሰላማዊ ትግል መርሆችን እየተከተለ መሆኑን ያሳያል። ከዚሁ ጋርም ተያይዞ ነሀሴ ሀያ ስድስት የሚደረገው ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ መሆኑ የሰልፉ ስኬታማነት አንድነት ፓርቲ በክልሎች ከጀመረው የማንቃት ስራ ጋር ተዳምሮ ለመላዊ የሀገሪቱ ህዝብ ትልቅ መነቃቃትንና ቁርጠኝነት ሊፈጥር ይችላል አዲስ አበባ ላይ ያካፋው ክልል ላይ ይዘንባል እንዲሉ ። እንግዲህ ለዚህ ሰልፍ ወደ ያህል ቀናት ይቀሩታል። በነዚህ በተቀሩት ቀናቶች የዚች ሀገር የቁልቁለት ጉዞ የሚያሳስባችሁ በተለይ ለኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች፤ ለድረ ገፅ ባለቤቶች እና ለማህበረ ድረ ገፅ አክቲቪስቶች ይህንን የነሀሴ ሀያ ስድስት ሰልፍ ከቀደመው ግንቦት ሀያ አምስት ሰልፍ ላቅ ባለና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ያካተተ ይሆን ዘንድ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በተለየ መልኩ ያለባችሁን ሀላፊነት ከቡድናዊ ስሜት ወጥታችሁ በሀገራችን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሚዲያ ክፍተት በመሙላት የተጀመረውን ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት እንድትገፉ በኢትዮጵያዊ ዜግነቴ እጠይቃለሁ። እንደምታውቁት በአዲስ አበባ ከሌሎቹ ከተሞች በተለየ የተሻለ የኢንተርኔት ስርጭት ያለበት በመሆኑ በዚህ ከተማ የሚገኘውን ማህበረሰብ ለመቀስቀስና ለማስተማር ማህበራዊ ድረ ገፆች የፈረጠመ አቅም አላቸው። የዚህን ክረምት ድብታ ከፖለቲካ ድብታችን ጋር ነሀሴ ሀያ ስድስት ሸኝተን የሚቀጥለውን ሁለት ሺህ ስድስት አመተ ምህረት በተስፋ እና በመነቃቃት እንጀምረው ዘንድ የሁላችንንም ያላሰለሰ ጥረት ይጠይቃል። በድጋሚ የሚቀጥሉትን ቀናት ሁላችንም በትጋት እንስራ። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ነሀሴ ሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት
ነሀሴ ሀያ ስድስትን በደቦ ሸኝተን ሁለት ሺህ ስድስት አመተ ምህረትን በተስፋ
አስራ አንድ ክለቦችን የሚያሳትፈው የሁለት ሺህ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ነገ በሚደረግ አንድ መርሀ ግብር ጅማሮውን ያደርጋል።ነገ በብቸኝነት የሚደረገው ዲላ ላይ በዘጠኝ ጌዴኦ ዲላ ከ አርባምንጭ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ነው።የስድስት ወራት ደመወዝ ክፍያን ለቀድሞ አሰልጣኙ እየሩሳሌም ነጋሽ ባለመክፈሉ ምክንያት አዲስ ያስፈረማቸውን ተጫዋቾችን በፌድሬሽኑ ማፀደቅ ያልቻለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በመርሀ ግብሩ መሰረት ድሬዳዋ ከተማን በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚገጥም የሚጠበቅ ቢሆንም ለአሰልጣኟ ክፍያን መፈፀም ካልቻለ በውድድሩ እንደማይሳተፍ ፌዴሬሽኑ ለክለቡ ማሳወቁን ሰምተናል።መቐለ ሰባ እንደርታን አራፊ ቡድን የሚያደርገው ይህ ሳምንት በማድረግ እሁድ በዘጠኝ ሲቀጥል የአምናው ቻምፒዮን አዳማ ከተማን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ካጠናቀቀው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ላይ የሚያገናኘው ጨዋታ የዚህ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ነው።የጥሎ ማለፉ ቻምፒዮን ሀዋሳ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም የፊታችን ማክሰኞ አቃቂ ቃሊቲን ይገጥማል። ረቡእ ደግሞ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የይራዘምልኝ ደብዳቤ አስገብቶ ተቀባይነት ያላገኘው እና ከመፍረስ ተርፎ በቅርቡ ዝግጅቱን የጀመረው አዲስ አበባ ከተማ መከላከያን ይገጥማል።የዘንድሮው ውድድር በ ክለቦች መካአል ለማካሄድ ታስቦ ነበረ ቢሆንም አምና በውድድሩ ላይ ሲሳተፍ የነበረው ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ በሁለተኛው ውድድር ለመሳተፍ በመወሰኑ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዝዮን በማምራቱ እንዲሁም ጥረት ኮርፖሬት በመፍረሱ በ ክለቦች መካከል የሚካሄድ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ነገ ይጀመራል
በመተከል ዞን የንፁሀን ዜጎችን ህይወት የሚቀጥፉትን ፀረ ሰላም ሀይሎች እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ እየተሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት አስታወቀ።ባህር ዳር፡ ሀዳር አስር ሁለት ሺህ አመተ ምህረት አብመድ በመተከል ዞን በሚደርሰው ተደጋጋሚ ግድያ ዜጎች ህይዎታቸውን እያጡ ነው። ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ ነው፤ በክልሉ ለአመታት የቀጠለው ሞት አሁንም መቋጫ አልተገኘለትም። በአካባቢው በታጠቁ ሀይሎች የሚገደሉ ንፁሀን ዜጎች እየተበራከቱ መጥተዋል።የአካባቢው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ለመንግስት አቤቱታ ቢያቀርቡም እስካሁን ድረስ ዘላቂ መፍትሄ የሰጣቸው አካል ግን አልተገኜም። በአካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት እርምጃዎችን አጠናክሮ ቢወስድም ሰው በላዎቹ አሁንም በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚያደርሱትን ግድያ አላቆሙም።በመተከል ወቅታዊ ጉዳይ ከኢቲቪ ጋር ቆይታ ያደረጉት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በመተከል ዞን ተደጋጋሚ ግድያ ይደርሳል ብለዋል። ባለፉት ጊዜያት የተከሰቱትን ችግሮች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአጎራባች ክልሎችና ከፌደራል መንግስት በሚደረገው እገዛ ሽፍቶችንም ሆነ አስተባበሪዎችን ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን ተናግረዋል።በየደረጃው ባለው መዋቅር ሀላፊነት የማይወጡትንና በወረዳና በየቀበሌ የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ሀይሎች ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጄት ወደ ህግ ለማቅረብ ተከታታይ የሆነ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል።በአካባቢው ያለው ሁኔታ በጣም ውስብስብ ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን አስታውቀዋል። በዞኑ በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ከአንድ መቶ በላይ ፀረ ሰላም ሀይሎች ተደምስሰዋልም ብለዋል። በየደረጃው ካለው የስራ ሀላፊ፣ የፀጥታ ሀይልና ተባባሪ ግለሰቦችንም በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል።በአካባቢው ያለው የፀረ ሰላም ሀይል ከትህነግ ጁንታና ከውጭ ሀገር ከሚኖሩ ፀረ ሰላም ሀይሎች ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን የተናገሩት ርእሰ መስተዳድሩ በቅርብ ጊዜም ሰላማዊ ዜጎችን ዘግናኝ በሆነ መንገድ ግድያ ፈፅሞባቸዋል ነው ያሉት።
በመተከል ዞን የንፁሀን ዜጎችን ህይወት የሚቀጥፉትን ፀረ ሰላም ሀይሎች እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ እየተሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት አስታወቀ።